ኢትዮጵያ አውታር በሳምንታት በፊት ስለ ቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫና የዐቢይ አሕመድ የ666 ሴራ ሰፊ ዘገባ አቅርባ ነበር። አሁን ደግሞ ሴራዊ ተግባራዊ ለማድረግ እየተጣደፉ መሆኑ የሚገልጽ መረጃ ሪፖርተር ጦማረ ህዝብ አስነብቧል። የኢትዮጵያ አውታር ዘጋባ ተከታዩ አስፈንጣሪ በመጫን ያንቡቡት። ቀጣዩ የሪፖርተር ዘገባ ነው።
በሚቀጥለው ዓመት ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀውን አገር አቀፍ ምርጫ አፈጻጸም፣ በከፊል ኤሌክትሮኒክስ ሒደትን የተደገፈ ለማድረግ ፕሮጀክት መጀመሩ ታወቀ፡፡
ፕሮጀክቱን ዕውን ለማድረግም የሚጠይቀውን የቴክኖሎጂ ዕውቀት ያካበቱ ባለሙያዎች ቡድን ተደራጅቶ ሥራውን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ውስጥ ሆኖ ማከናወን ከጀመረ፣ ከአንድ ወር በላይ እንደሆነው የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡
የፕሮጀክቱ ዓላማ ከመጪው ምርጫ ጀምሮ የአገሪቱ የምርጫ ሒደትና ሥርዓት፣ በከፊል በቴክኖሎጂ የታገዘ እንዲሆን ለማድረግ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል፡፡
በዚህ ዕቅድ መሠረት የመራጮች ምዝገባና የተመዘገቡ መራጮች መሆናቸውን የማረጋገጫ ሥርዓቱ በጣት አሻራ ቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን፣ በተጨማሪም በየምርጫ ጣቢያዎቹ መራጮች የሚሰጡት የድምፅ ቆጠራና የውጤት ማስተላለፊያ ሥርዓቱ በቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ ይሁን እንጂ የድምፅ አሰጣጥ ሥርዓቱን አያካትትም፡፡ በመሆኑም የድምፅ አሰጣጡ ከዚህ ቀደም በነበረው አሠራር መሠረት በድምፅ መስጫ ወረቀትና በኮሮጆ ሆኖ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሏል፡፡
ለዚህ ፕሮጀክት የሚያስፈልገው አጠቃላይ በጀት በመንግሥት ያልተያዘ ቢሆንም፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ የፋይናንስ ድጋፍ የሚያደርጉ በአዲስ አበባ የሚገኙ የውጭ መንግሥታት ወኪሎችን ድጋፍ በመጠየቅ ይሁንታ ማግኘቱንም ለማወቅ ተችሏል፡፡
ይኼንን ፕሮጀክት በተመለከተ ዝርዝር መረጃ እንዲሰጡ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ ለሆኑት ወ/ሮ ደሚቱ ሃምቢሳ ሪፖርተር ጥያቄ ያቀረበ ቢሆንም፣ ‹‹እኛ በዚህ ጉዳይ ላይ ለሚዲያ መግለጫ አልሰጠንም፣ ሰዎች ዝም ብለው ነው ፍላጎታቸውን የሚያወሩት፤›› ብለዋል፡፡
ይኼንኑ ጉዳይ በተመለከተ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳን ለማነጋገር የተደረገው ሙከራ አልተሳካም፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሳምንት በፊት ባካሄደው ስብሰባ፣ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን በድጋሚ ለማቋቋም የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ ተመልክቶ ለዝርዝር ዕይታ ለሕግ፣ ፍትሕና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መምራቱ ይታወሳል፡፡
በጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የተቋቋመው የሕግ ማሻሻያ ምክር ቤት አማካይነት ማሻሻያ ይደረግባቸዋል ተብለው ከሚጠበቁ አዋጆች መካከል የምርጫ አፈጻጸም ሥርዓቱና የዕጩዎችና የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጆች ይገኙበታል፡፡
እነዚህን ሕጎች የሚያሻሽሉ ረቂቅ አዋጆች በዝግጅት ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ የምርጫ ሥርዓቱ አፈጻጸምን በቴክኖሎጂ ለማገዝ የተጀመረው ፕሮጀክትም በእነዚህ የሕግ ማዕቀፎች ማሻሻያ ውስጥ ሊካተት የሚችል ቢሆንም፣ ሕጎቹን ለማሻሻል የተቋቋመው ንዑስ ኮሚቴ ከባለድርሻዎች ጋር ባካሄዳቸው የውይይት መድረኮች፣ የምርጫ ሥርዓቱን በቴክኖሎጂ የመደገፍ ጉዳይ የመወያያ አጀንዳ አልነበረም፡፡
የምርጫ አፈጻጸም ሥርዓትን በቴክኖሎጂ የመደገፍ ሒደት በበርካታ አገሮች እየተለመደ የመጣ ሲሆን፣ ከሰሃራ በታች ብቻ 25 አገሮች የምርጫ ሥርዓታቸውን በከፊል በቴክኖሎጂ መደገፋቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

Blogger Comment
Facebook Comment