ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ ፡ ከ7000 ዓመታት በላይ በዲያብሎስ አይነ ቁራኛ ክትትል ውስጥ ነች። የዚኽ ምክንያትም የአዳምና ሔዋን ጥንታዊት መኖሪያ የግዕዝ መነሻ በመሆንዎ ነው። ኢትዮጵያን ለመቆጣጠርና ለማጥፋት ዲያብሎስ የተለያዮ አገልጋዮች ተጠቅሟል። የተለያዮ ሙከራዎቹ ባይሣካለትም ከ123 ዓመታት በፊት በጀግኖች ኢትዮጵያውያን አያቶቻችን በቅድስ ጊዮርጊስ አምላክ ተረዳኢነት በዓድዋ የደረሠበት ሽንፈት ግን ለመቀበል የከበደበት ይመሥላል። በዓድዋ የተሸነፈው የፀረ ክርስቶስዎ ካቶሊክ (ጣልያን) መንፈሥ ነው።
ይህንን ሽንፈት ለመበቀል ነበር ዲያብሎስ በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊ በሆኑ ነገሮች የውሸት ትርክቶች በመፍጠር መሥራት የጀመረው። በቀሉ የጀመረው ኢትዮጵያዊ የሆኑ ግን ኢትዮጵያዊነታቸው በመካድ ፀረ ኢትዮጵያ እንዲሠለፉ ነበር ያደረጋቸው። ውጊያው ከዚህ ይጀምራል፡
፩፦ በዓድዋ የቅድስ ጊዮርጊስ አምላክ በመተማመን ኢትዮጵያን ለመቆጣጠር የመጣው ባዕድ ወራሪ በጀግንነት ያባረሩት ጥቁር ኢትዮጵያዊ ንጉሥ ምንይልክ ላይ የውሸት ታሪኮች በኦሮሞና ህወሓት ሰዎች በማስነገር ማጥላላት።
፪፦ የመጀመርያውና የአዳምና ሔዋን ቋንቋ ወይም ልሣንና የምሥጢራት ቁልፍ የሆነው ግዕዝ በህወሓት ፊታውራሪነት በሀገረ ጀርመን ተረዳኢነት ከኦሮሚያ ክልል በማጥፊት በካቶሊክ ቤተክርስትያን የቅዳሴ ቋንቋ ላቲን ፊደሎች እንዲተኩና የግዕዝ ፊደላት ጥቅም ላይ እንዳይውል መደረጉ።
፫፦ ከ ፶ ጊዜ በላይ በቅድሱ መፅሐፍ የተጠራቺው ኢትዮጵያ በወልደ ካቶሊክ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮችና በሀገረ ጀርመን ደጋፊነት የኦሮሞ ፖስተሮች "ኢትዮጵያ" የሚለው የመፅሐፍ ቅድስ ቃል በ"ኩሽ"ለመተካት መጣራቸው። ከሦስት ሣምንታት በፊት የሀገረ ጀርመን ውጭ ጉዳይ ምኒስተር ኢትዮጵያ መጥተው በነ ለማ ቡድን እየተደረገ ያለ ለውጥ አስደሣች መሆኑ መግለጣቸው ልብ ይሏል?
፬፦ የአንግሎ አመሪካውያን አገልጋይ ህወሓትና የኦሮሞ ሰዎች ኢትዮጵያውያን በምዕራባውያን የተሠጣቸው ኢትዮጵያን ወደ ፻ ሀገራት የመበታተን ፅንሰ ሓሳብ የሆነው ፌደራሊዝም ቀንደኛ ተሟጋች መሆናቸው።
አስደሣቹ ነገር ኢትዮጵያን ለማጥፊት መጥቶ የተሣካለት የለም። ጠባቂዎ የድንግል ማርያም ልጅ ኢትዮጵያዊው ክርስቶስ ነውና።
ኢትዮጵያዊነት ታላቅ ክብር ነው!!!

Blogger Comment
Facebook Comment