ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን - የኢትዮጵያ ትንሳኤ!!


ወገኔ የኢትዮጵያ ህዝብ በፈጣሪህ እጅግ የተወደድክ ህዝብ እኮ ነህ እጅግ ላከበራት ለእናቱ ለእናታችን ለድንግል ማርያም ልጅ አድርጎ የሰጠህ ለማንም ያልሰጠውን በረከትና ህይወት ያዘዘልህ እኮ ነህ!! የእምዩ (የድንግል) ልጆች ለመሆኑ እንዲህ ለወደዳችሁ አምላክ ምን ትከፍላላችሁ!! አለምን ሁሉ ለእናንተ እንዲገዛ እንዲታዘዝ ወሰነ፡፡ እስቲ ወገኔ አስተውል! ያለፉት ለዚች የተባረከች ምድር የደከሙት አባቶቻችንን ድካም 7000 (ሰባት ) ዘመን ሲመዝን፣ ሲለካ፣ሲመዘግብ ኖሮ ቃሉን በፍጹም የማያጥፍ ጌታ ለኔና ላንተ ላንቺ ብድራትን ሊከፍል መጣ!! ለመሆኑ ምንስ ትከፍለዋለህ!! ጌታ ሌላ አይጠይቅም ከልብህ የሚመነጨውን ምስጋና ብቻ ነው፡፡

በፈጣሪ ፊት ያለህን ክብር አላወከውም! አሁን ግን ልታውቀው ይገባሃል፡፡ በስራህ አይደለም የወደደህ አያት ቅድመ አያቶችህ በእምነታቸው ቆመው በጸጋው ያፈሱት በረከት ነው፡፡ ለዚህም የትንሳኤ ዘመን ያደረሰህ የታመነ አምላካችን ሁሌም የታመነ ነው፡፡ ከቃሉ የሚጨመር የሚቀነስ የለም፡፡

አድምጥ ደስም ይበልህ!! በአለም የሚያበራ ክብር ለኢትዮጵያ ተሰቶአታል!! በበረከቱና በቸርነቱ በፍጹም ፍቅሩም የምትሞላው ኢትዮጵያ በእመቤቴ የእናትነት እቅፍ እና በረከት ታኖርሃለች፡፡ ከእንግዲህ አገርህ ኢትዮጵያ ወደውርደት አትመለስም ለበረከት የታደልከው ወገኔ እንደ አሁኑ ክፉ ትውልድ ፈጣሪህን እንዳታስከፋው እነግርሃለሁ፡፡ አሁን ቁጣውንም ጥፋቱንም ታየዋለህና ከፈጣሪህ ፈቀቅ እንዳትል ከዚህ ጥፋት በኃዋላ በበረከቱና በቸርነቱ ብዛት ደስታህ እጅግ ስለሚበዛ በስጋ ምቾት ተጠልፈህ ከፍቅሩና ከቸረህ ጸጋው እንዳትኮበልል ተጠንቀቅ!!

የተባረከው ወገኔ አንተ መልካሙን ታያለህ ልጆችህም እንዲያዩና ለትውልድ እንዲያዘልቁ አብረን ታምነንና ለአምላካችን ቃልና ትእዛዙ ተግተን አገራችን በፈጣሪ ፊት እንደታመንች፣ እንደተወደደች፣ እንድትዘልቅ የሚያደርገውን ስራ እንስራ!!

በፍቅሩ ኑሩ የሚጠላውን ጥላ፣ የሚወደውን ውደድ አሁን የምታየውን ዲያቢሎስ የዘራውን አመጽና የጥፋት አዝመራ ከምድርህ አጥፋ፣ እውነትን ብቻ አንግስ፡፡
ሙሴ በእስራኤላውያን ክህደት ሲበሳጭ እግዚአብሄር ያለውን ልታስብ ይገባሃል፡፡ ጌታእንዲህ ነበር ያለው፣ ሙሴ ባሪያው ይህንን ልቡ ጠማማ ህዝብ ላጥፋው ተወኝ አንተንም ለታላቅ ህዝብ መሪ ላድርግህ ነው ያለው፣ ያታላቅ ህዝብ ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው፡፡ ሙሴ አስተዳደርን የተማረው ከኢትዮጵያዊው የሚስቱ አባት ከዮቶር ነበር፡፡ ኢትዮጵያበህገ ልቦና፣ በህገ ኦሪት፣ ዛሬም በህገ ወንጌል ያለውን ስርአት ሳታፋልስ ትውፊቱን ጠብቃ መጥታለች፡፡ እግዚአብሄር አምላካችን በባሮቹ በኩል ያስተላለፈውን ቅዱስ ቃሉን፣ በጥንቃቄ ጠብቃ ላንተ ለዛሬው ትውልድ አድርሳለች፡፡ ሌላው የናቀውን የጣለውን የደለዘውን የቀነሰውን ተግባር ሳትከተል በትክክል እንደነበር እንደቃሉ ጠብቃ አኑራለች፡፡ ከአለም ሁሉ በሚለየው የእምነት ስርአትዋ ዛሬም ሁሌም እንደ ጠል በሚንጠባጠብና እንደ ምንጭ ውሃ በሚንቆረቆር ዜማዋ
ፈጣሪን ታመሰግናለች፡፡
ታላላቅ መሪዎችን እግዚአብሄር ሰጥቶአት ነበር፡፡ እነ ካሌብን፣ እነ ኢዛናን፣እነ አብርሃ ወአጽብሃ፣ እነላሊበላን እነ ዘርአያእቆብን ወዘተበእምነቱም በስጋውም አገዛዛቸው የገነኑትን አሳልፋለች፡፡ ግዛትዋም እጅግ የሰፋና እስከ የመን የዘለቀ ነበር፡፡ በየዘመኑ የተነሱ ጠላቶች ሲቀንስዋት ሲሸርፍዋት መጡ፣ መሪዎቹም በታሪክ እያነሱ መጡ፣ የቅርቡን ብናነሳ ከዘመነ መሳፈንት ጀምሮ በኢትዮጵያ ታሪክ በድንበር ጉዳይ ብዙ የተወሳሰበ ሁኔታ ተፈጥሮና እስከዘሬ ተወሳስቦ እንደቀጠለ እናያለን፡፡ በታሪክ ያነሱና አገራቸውን እየሸረፉ ለጠላት በመስጠት ለስልጣናቸው መደላደል ብቻ የሚደክሙ መሪዎች እነሆ ቆመን እያየን ነው! የታሪክ ድንኽነት
ፈጽሞ የማያማቸው ናቸው፡፡ ይሁንና ወገኔ አትጨነቅበት ጠላት በየአቅጣጫው በቃኘው በነደፈው አካሄድ ሁሉ ኢትዮጵያን ከምድረ ገጽ አጥፍቶአል፡፡ ዛሬም የሚችለውን እያደረገ ነው፡፡ ይሁንና ፈጣሪ ሁለንተናዊ ጥበቃ ስላደረገ እዚህ ደርሳለች፡፡
ከአሁን በህዋላ ግን ይህ ታሪክ ይቀየራል፡፡ ሃፍረትም መሸማቀቅም ለጠላቶች ይሆናል፡፡ የጠበበው የተሸረፈው ወደነበረበት ብቻ ሳይሆን እጅግ በማትገምተው ሁኔታ ሰፍቶ ይንሰራፋል፡፡ በነካሌብ ዘመን የነበረው ብቻ ሳይሆን ከዚያም በላይ ይሆናል፡፡ ወገኔ! ይግረምህ አምላክህ ይህንን ያደርጋል፤ ከዚህም አልፎ የሌሎች አገሮች ሁሉ እድልና እጣፈንታ በሙሉ የሚወሰነው እዚህ በታላቋ ኢትዮጵያ ይሆናል፡፡ አለምም የኢትዮጵያ ምርኮና በረከት ይሆናል፡፡
መዝሙር ዳዊት 36 ( 37 ) 9 ትንቢተ ሶፎኒያስ ምእራፍ 3
ኢሳኢያስ ምእራፍ 57 ኢሳኢያስ ምእ 62 1 - 5
መዝሙር ዳዊት 57 ( 58 ) መዝሙር ዳዊት 56
ወገኔ ልብ ብለህ አስተውል ፈጣሪህ ለክብሩ ሊመሰገንበት በእውነት ወዶሃል ቅን ፍርዱንም እንደጸሃይ ሊያወጣ ወስኗል፡፡ ስለዚህም እኔ ወንድምህ የምመክርህን ታናሽ ምክር አድምጥ!! ለሰው ልጅ ሁሉ ፍቅር ይኑርህ ክፋትን፣ ጭካኔን፣ ስስትን፣ ምንዝርናን፣ ሌብነትን፣ መልካም ያልሆነውን ሁሉ ፈጽሞ ከራስህ አርቅ በእምነት ወንድምህ እህትህ ለሆኑ ለአገርህም መታመን ይኑርህ ከዚህ ሁሉ በላይ ፈጣሪ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ሃሳብህ በፍጹም ነፍስህ ውደደው!!!



Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment