በምድሪቱ ላለህ የሰው ዘር በሙሉ
ተጻፈ ግንቦት 27 ቀን 2000 ዓ. ም. እ. ኢ. አ. ይህ ሁለተኛ የፈጣሪ ውሳኔ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
ወይም ቀይ መብራት የታየበት ሊባል ይችላል፡፡
ማስታወሻ
.. መልእክቱን በጥንቃቄ ያንብቡ
.. ለሌሎች ሲሰጡ ሁሉንም ገጾች ይስጡ፡፡ አይጨምሩ፣ አይቀንሱ፣
አያሻሽሉ፣ ይህን የሚያደርጉ አለቅጣት አይታለፉምና !
.. እኔ በነጻ እንደሰጠኁአችሁ እናንተም በነጻ ስጡ ፈቅዶ ወዶ ከሰጡአችሁ ተቀበሉ፡፡
በረከቱ ይበልጥብናል
ካላችሁ አትቀበሉ፡፡
.. ፋከስ አድርጉት፣ ኢሜይል አድርጉት፣ በድረገጾቻችሁ ልቀቁት፣ በፖስታም ላኩ፡፡
.. በጋዜጣ በመጽሔት አትሙት፣ አሰራጩት በሬድዮን፣ በቴሌቪዥን ልቀቁት
.. እንደ ትዕዛዙና ምክሩ ለማያደርጉ በትዕዛዙ ውሰጥ የሚገጥማቸውን ያንብቡ፡፡
.. በጎ ለመስራት ማንም አይከለከልም፡፡
.. መሪም ሆነ ተመሪ ሁሉም የሚመዘነው እንደመጸጸቱና እንደቅን ተግባሩ ነው፡፡
.. በጎ ሥራም የሚጀመረው ከትንሹ ነው፡፡
መልካም የመረዳት ንባብ ይሁንልዎ !
ግንቦት 27/2000 ዓ. ም ተጻፈ
በምድራችን ሁሉ ፊት ተበትኖ ለሚኖር መላው የአዳም ዘር በሙሉ
ሁለተኛውና የመጨረሻው መልእክት ነው ሌላ የሚመጣ የለም፡፡ የተወሰነውን ወደ ተግባር ከሚለውጥ በስተቀር፡፡
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን !
ትእዛዝህን ፈልጌአለሁና
አስፍቼ እሄዳለሁ በነገስታት ፊት ምስክርህን እናገራለሁ አላፍርምም እጅግ በወደድኁአቸው በትእዛዛትህ ደስ ይለኛል እጆቼንም ወደ ወደድኁአቸው ወደ ትእዛዛትህ አነሳለሁ ስርአትህንም አሰላስላለሁ መዝ. 118 ( 119 ) 44 – 48 እንዳለው ዳዊት ለሁሉም የሰው ዘር ! የፈጣሪን የፍርድ ውሳኔና ሂደት እንድታደምጡ እነሆ ታዘዝሁ፡፡ ትእዛዜንም ያለአንዳች ፍረሃት እነሆ የሰው ዘር በሙሉ አድምጥ፣ ጆሮህን፣አይንህን ክፈት ብዬ እናገራለሁ፡፡ በአእምሮአችን የሚታወቀውንም፣ የማይታሰበውንም፣ የማይደረስበትን፣ የረቀቀውን፣
ተገለጸውንም፣ የገዘፈውን፣
ያነሰውንም፣ ሁሉንም የፈጠረ አምላካችን ስሙ ይባረክ ! ያለ የሚኖር የዘመንም የጊዜም የሁሉ ነገር ፈጠሪ አምላክ ለስሙ ክብር ይሁን፡፡ የብርሃን ፈጣሪና ጌታ እግዚአብሄር ማንም በማይቀርበው ብርሃን ውስጥ ዙፋኑን የዘረጋ አምላካችን የተመሰገነ ይሁን፡፡ ሰውን ለክብሩ፣ ሊመሰገንበት፣ በራሱ አምሳል አክብሮ የፈጠረ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ ለዘላለም
እስከዘላለም ሊመሰገን ይገባዋል፡፡ ልንከብር፣ ልንድን፣ የዘላለም ህይወት ልንወርስ፣ የወደደን ቸሩ ፈጠሪ ይመስገን፡፡ ማንም የማይመክረው ፣ ማነም የማያዘው፣ ፈቃዱ የወደደችውን ሁሉ የሚያደርግ አምላክ ይክበር ይመስገን፡፡ በባህርዩ እውነትን፣ ፍቅርን፣ ቸርነትን፣ ፈጹምነትን የለበሰ፣ ፍጹም የሆነ ጌታ ለክብሩ ስለ ፈጠረን ልናመሰግነው ይገባል፡፡ የዘላለም ህይወት ልንወርስ ከመንግስቱ ሙላት በደስታ ልንቦርቅ ፍጹም የወደደን ማንም በማያልፈው መከራ ስጋውን በጣጥሶ ደሙን ዘርቶ በታላቅ ሰቆቃ ሞትን ጨልጦ በ 3 ቀን የሞትን ጀግንነት በትኖ ( ድል ነስቶ ) እሰከ ምን ርቀት እንደሚወደን አሳይቶን በክብሩና በዙፋኑ ላይ ያለ ጌታ የተመሰገነ ይሁን !!
መዝሙረ ዳዊት 103 ( 104 )
ከእናታችን ከድንግል ማርያም ስጋዋን ቆርሶ ደምዋን ወርሶ ፍጹም ሰው ሆኖ፣ የኛ ህመም ህመሙ፣ ቁስላችንን፣ መሰበር፣ መጎሳቆል፣ መድቀቅን ሁሉ ገንዘቡ አድርጎ ልናልፍበት ልንከፍለው የሚገባንን የሃጢያት ዋጋ ሁሉ ራሱን ሰውቶ ፍጹም ዋጋ ከፍሎ ላዳነን፣ ለክብሩ ላበቃን፣ የገሃነም ደጆች ሊያጠፏት የልቻሏትን፣ የተዋህዶ ኦርቶዶክስን እምነት በዚህ ሁሉ የጥፋት ማእበል ውስጥ አጽንቶ ላቆመልን፣ አምላካችን ክብር ምስጋና ውዳሴ በፍጹም ነፍሳችን ከፍጹም ሃሳባችንና ከፍጹም ልባችን ለሱ ይፍሰስ ! ስሙ ይባረክ አሜን !! የዛሬው መልእክቴ የመጨረሻና ማሳረጊያዬ ነው ደግሜ እላለሁ የመጨረሻው መልእክት ነው የመልእክቱ ጭብጥ በሁለት ይከፈላል፡፡ 1ኛው መልክት በመላው አለም ያሉ አገራትንና ህዝባቸውን የሚመለከት ሲሆን፡፡ 2ኛው የአገሬን የኢትዮጵያን ሁኔታ ይመለከታል፡፡ ከትእቢትና ንቀት ርቃችሁ ልብ ብላችሁ አድምጡ ! የፍርድ ቃልና ውሳኔ
ሊፈጸምባቸው የተዘጋጀና በየደጃችሁ መቆሙን እንድታውቁት የታዘዘ ቃል ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ውጭ ላሉ የአለም ህዝብ በሙሉ እንዲዳረስ በእንግሊዝኛ ይሄው መልእክትና የፍርድ ቃል ቀርቧል፡፡ ሰው ሆይ አድምጥ
መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 1 ፡ ም 2 ፡ 1 – 10
መዝሙረ ዳዊት 18 ( 19 )
መዝሙረ ዳዊት 32 ( 33 ) 16 – 22
ፈጣሪውን ለናቀ ትእዛዙንና ፈቀዱን ላቃለለና በፍጹም የዲያብሎስ ተገዥ ለሆነ ህዝብ የግድ ፍርዱን ሊያገኝ የገባል፤ ቢወቀስ ቢገሰጽ ቢገረፍ በፍጹም የማይሰማ ፤ ከአንዱ ጥፋት ወደ ሌላው የሚሸጋገር የፈጠረውን አምላክ ትእግስት የሚፈታተን፣ አልፎም የሚሳደብ፣ በያዘው እውቀት የሚታበይና እራሱን ከፈጠረው ጌታ በላይ ያደረገ፣ የዘመኑ ሰው የግድ የፈለገውን እሬቱን ሊጋተው ይገባል፡፡
መዝሙረ ዳዊት 10
ከሌሎች ፍጥረቶች ሁሉ ትለያለህና በፈጣሪ አምሳል የተፈጠርክ ሰው ነህና እንደ ስብእናህ አስብና አድምጥ፤ጆሮህን ክፈት፣ አይንህም ይገለጥ፤ በገደል ጫፍ ላይ ቆመሃል፣ ልትተፋ ልትጣል ነው፡፡ የዘላለምን ጨለማ የዚችንም አለም እንግድነት በውርደት ልትጨልጥ ነው፡፡ አስተውል፣ አስብ፣ ፈጥነህ አድምጥ ይህ መልዕክት የኖቤል ፕራይዝ እያልክ የምትሸላለምበት ድርሰት፣ ልብወለድ እንዳይመስልህ፡፡ ይህ መልእክት የፍርድ ነው፡፡ ሰማይና ምድርን የፈጠረና የዘረጋ አንተንም ፈቅዶ የፈጠረ አምላክ ውሳኔ ነው፡፡ ከአፉ ወጣ ቃሉ፤ የታዘዘውን ሰይፈጽም አይመለስም፡፡ ቃሉ ከሚታጎል ምድርና ሰማይ ቢያልፉ ይቀላልና !
በምድርም ከንቱ በመጭውም ዓለም ውዳቂ ለምትሆን ላንተ መጥቶብሃልና፤ ምጥ ጀምረሃል፡፡ ረሃብ፣ ጦርነት፣ አውሎ ንፋስ፣ ማእበል፣ እሳተ ገሞራ ሁሉም የፈጠራቸውን የአምላካቸውን ትእዛዝ ለመፈጸም ተጠንቀቅ ቆመዋል፡፡ መንግስት ነኝ፣ ድርጅት ነኝ፣ መሪ ነኝ፣ ካቶሊክ ነኝ፣ እስላም ነኝ፣ ፕሮቴስታነት ነኝ፣ አለም አቀፍ ድርጅት ነኝ፣ፕሮፌሰር ነኝ፣ ዶክተር ነኝ፣ ጀነራል ነኝ፣ ሊቅ ነኝ፣ ባለ ታንክ፣ ባለ ጀት፣ ባለ ኒውክሊየር፣ ብዙ ሃብት አለኝ፤ ለምትል በንቀት፣ በትእቢት፣ በአውቀለሁ ባይነት ለተሞላህ፤ ውሸትን እንደጥበብ ለለበስክ ጨካኝ ነፍስ ገዳይ ለሆንክ ሁሉ ትቢያ ነህ አትጠራጠር፤ ወደ ትቢያ ትመለሳለህ፣ መና ነህ፣ እንደ ጢስ ትበናለህ፤ የፈጣሪን ቁጣ የቀሰቀሰው አመፅህ የሚበላህን እሳት ወልዱአል፡፡ ይበላሃል አታመልጥም፡፡ የሰራዊት ጊታ እግዚአብሄር ይህን አስቡአል የሚያስጥለውስ ማነው? እጁ ተዘርግታለች የሚመልሳትስ ማነው? ኢሳኢያስ
14፡ 27 ማንኛውም ይህ መልእክት የደረሰው ሰው ለሌላው ወገኑ ሳያጎል ሳይጨምር ሊያደርስ ይገባዋል፡፡ ለሁሉም እንዲደርሰው አቅምህ የፈቀደውን ሁሉ አድርግ፤ ለፈጣሪ መታዘዝ ማለት፣ ሌላው ወንድምህና እህትህ የሚድኑበትን፣ ከሞት አደጋ የሚያመልጡበትን ሁሉ ማድረግ ነው፡፡ በቅንነት በየዋህነት የፈጠሪውን ትእዛዝ በማክበር ለሚለፋ ዋጋው ይከፈለዋል፡፡ ይህ መልእክት ለሁሉም የሰው ዘር ሊደርሰው ይገባዋል፤ ቢቀበልም ባይቀበልም፣ ቢሰማም ባይሰማም፣ አንተ ፈጣሪ የጣለብህን አደራ ተወጣ፡፡ ንገረው አልሰማ ካለ እጅህን አጨብጭበህ የእግርህን ትቢያ አራግፈህ ፤ አንተ እንዳራገፍከው ሁሉ የሰረዊት ጌታ እግዚአብሄርም እንደዚሁ እንደ ትቢያም ይበትነዋል፡፡ ስለዚህ አንተ መልእክቱን አድርስ፤ ቢፈልግ ይጣለው፣ ይቅደደው፣ ይተችም፣ ይመጻደቅም፣ እንደለመደም፣ የክርክር፣ የፍልስፍና አጀንዳም ይክፈትበት፣ ያሻውንም ይበል፣ የሚከፈለው ዋጋ በእግዚአብሄር እጅ ነው፡፡ በመሆኑም ሳይውል ሳያድር ዋጋውን ይቀበላል፡፡ አላግጦ ንቆ አሹፎ የሚኖርበት ዘመን አልቆአልና ! ማንኛውም ሰው ይህን መልእክት ካነበበ በኋላ ቀድሞ እራሱን ቢያይ መልካም ነው፡፡
ብዙዎች እንደ ህይወታቸው ልምድና እንደ እውቀታቸው፣ እንደ ተግባራቸው ሊያዩና ሊተረጉሙ ይችላሉ፡፡ ይህ በዚህ ገሃድ አለም በሚፈጠር የስጋ ጭቅጭቅ የሚፈቀድና የተለመደ ነው፡፡ ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ ድካማችሁ በጌታ እግዚአብሄር ከንቱ እንዳይሆን አውቃችሁ የምትደላደሉ ፣ የማትነቃነቁም፣ የጌታ ስራ ሁል ጊዜ የሚበዛላችሁ ሁኑ!! ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች - 1 ም 15 -58 ይህ የምታነበው ቃል ከፈጣሪ ጋር የቀረበ ግንኙነት ባላቸው በተልእኮው በታመኑ አገልጋዮቹና ባሮቹ የተጻፈ የሚወቅስህ፣ ባትሰማ ባትመለስ ዋጋህን የሚሰጥህ የፍርድ ቃል ነው፡፡ በስጋ ምኞት፣ በግል ስሜት የመጣ እንዳይመስልህ እዚህ ውስጥ የምትሰማውና
የምትረዳው መልዕክት አንዱም ነጥብ ሳይወድቅና ሳይለወጥ ይፈጸማል፡፡ ቆሞ ተርፎ ለማየት ያድልህ እንጂ፡፡ በእርግጥ መታወቅ የሚገባው እውነቱን አውቀህ ላልተመለስክ ልክ እንደ ኖህ ዘመን ሰዎች ጥፋቱ አንገተህ ደርሶ ተፀጽተህ ወደማትመለስበት ጫፍ ሲያደርስህ በዚያ ሰአት ብቻ ታውቀዋለህ፡፡ ይህ ቃል እውነት መሆኑን ወደ ሞት እየተላለፍክ ለነፍስህ፣ ለራስህ፣ ለውስጥህ ነግረህ ትከትማለህ ሰለዚህ ስማ !
ትንቢተ ኢሳኢያስ ምዕ ፡ 2፡ 6 – 22
ትንቢተ ኢሳኢያስ ምዕ ፡ 5፡ 7 – 30
የአዳም ዘር አድምጥ ፍርድህ ወጥቶአል፡፡ ማምለጫ የለም፡፡ በ1988 ዓ.ም. በህዳር 7 ቀን በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ 21 ገጽ የተከተተ የመጀመሪያው መልእክት የላክሁ ሲሆን ታላላቅ አገርና የዚያም መሪ ነን ለሚሉ የስጋው መሪዎች፣ መንፈሳዊ መሪ ነን ለሚሉ በአደራ ፖስታ እንዲደርሳቸው ልኬላቸዋለሁ፡፡ በአዲስ አበባ ለሚገኙ የ17 አገሮችና አለም አቀፍ ድርጅቶች እዚህ ባኖሩአቸው ኤምባሲዎቻቸው በኩል በአደራ ፖስታ በአድራሻቸው ልኬአለሁ፡፡ በአገሬ ለብዙዎች በግል እንዲደርሳቸው አደርጌአለሁ፡፡ ለመላው ህዝብም በየቋንቋው ተርጉማችሁ እንድትገልጹ አሳስቤአለሁ፡፡ ሃላፊነትም እንደምትወስዱ ገልጫለሁ፡፡ ይህንን ንቃችሁ ይህንን ሳታደርጉ ቀርታችኋል፡፡ የሚገርመው አንድም የመንግስት ድርጅት፣ መንፈሳዊ ተቋም፣ ተብዩ ለወገኖቹና ለሚመረው ህዝብ የገለጸው የለም፡፡
ይሁንና ዛሬ በአለማችን ከ2 አመት ወዲህ እየተከሰተ ያለውን የምጥ ጅማሮ ሰትመለከቱ ቆይታችኋል፡፡ ይህም
አይቆጠቆጣችሁም፡፡ ስለዚህ የዛሬው የሞት መርዶ መጥቶልሃል !!
የአባታችሁ የዲያብሎስ ሰራ፣ የዘፈን፣የዳንስ፣ የፊልም፣ የስፖርት፣ የፍጅት፣ የአደጋ ዜና፣ ብታገኙ በሰከንድ በረጫችሁት ነበር፡፡ ይሁንና ለኔ አይገደኝም፤ ሊያውቅ የሚገባው በተለያየ መንገድ ደርሶት አውቆታል፡፡ ያላወቀውም አሁን እያወቀው ነው፡፡ በዚህ የመጀመሪያ መልእክት የሚገጥማችሁ በግልጽ ተነግሯል፡፡ ስራችሁም ተገልጧል የእሳት ባህር ይጠርጋችኋል፡፡ ይህም የአለምን የሙቀት መጨመር እየተመለከትከው ነው፡፡ በሳይንስ ትመልሰዋለህ ጠብቀው፡፡ ለሚያስተውል ራሱንና ወገኑን የት እንዳሉ የሚያይበት መነጽር ነው፡፡ አሁን ያ ወቅት ሳትጠቀምበት አልፏል፡፡ 2ኛ አመቱን አጠናቋል፡፡ መጪው ምንድነው የሚለውን መመልከት
ተገቢም አስፈላጊም ነው፡፡ በመጀመሪያውም ሆነ በዚህ በ2ኛው መልእክት የተገለጸው ሁሉ ይፈጸማል፡፡ አንዳችም የሚቀር ነገር የለም፡፡ አለም የተለያየ መጠን ባላቸው ችግር ውስጥ ወድቃለች፤ ሙቀት ጨምሯል፣ረሃብ ነግሷል፣ ግጭት በዝቷል፣ የአየር ንብረት ተለውጧል፣ ምድር ባህሪዋን ለውጣለች፡፡ ይህ ሁሉ ልክ ነው፡፡ ይሄው ጥፋት በብዙ መቶ እጥፍ በከፍተኛ መጠን ይጨምራል፡፡ የዲያብሎስ ልጆች በእሳት ባህር ለመጠረጋችሁ መጠራጠር የለባችሁም፡፡ የቻይናን ምድር ያንቀጠቀጠና ያፈረሰ፣ በርማን የጠረገ፣ የቁጣ ምልክት ምን ይመስላችኋል? እናንተ ጋ አይመጣም? የሚያግደው አለ? በሺ እጥፍ ይመጣልሃል፡፡ እንናተ ሞት ሲውጣችሁ ብቻ ነው የሚገባችሁ፡፡ ስለዚህ ጠብቁት፡፡
አንዲት እርጉዝ ሴት ልትወልድ ወሯ ሲገባ ይጎረብጣታል፣ ይወጋጋታል፣ጭንቅ ጭንቅ ይላታል፡፡ ይህም የምጥ መምጫው ምልክት ነው፡፡ ዛሬም በአለማችን የሚታየው ይኄው የጥፋት መምጣት ምልክቶች ናቸው፡፡ ታላቁ ምጥ ገና ይጀምራል፡፡ የትስ ታመልጣላችሁ ! ከጌታ ወዴት ትሸሸጋላችሁ ! እውቀታችሁ፣ ሃብታችሁ፣ ግንባችሁ መኪናችሁ አውሮፕላናችሁ፣ የቆፈራችሁት መደበቂየችሁ፣ ወታደራችሁ፣ ጥበባችሁ ለመሆኑ የቱ ነው ከፈጣሪ የቁጣ በትር ሸሽጎ የሚያኖራችሁ ! ረሃብና የኢኮኖሚው ችግር ለደሃ ብቻ እንደመጣ ትናገራላችሁ፤ ባለጠጎች ናችሁና በወርቃችሁ በብራችሁ እንድናለን ባዮች ናችሁ፡፡ ጠብቁ ! ውጤቱን ታያላችሁ፡፡ ከተደበቅህበት ፈትሾ ገብቶ የሚበላ እሳት ይመጣልሃል፡፡ ኢሳኢያስ ም . 13 በእግዚአብሄር ቤት መሸሸግ የሚቻለው ለምኖ ከፈጣሪ ለማስታረቅም ለመታረቅም ለሁሉም የሚበቃ መንፈሳዊነትና መንፈሳዊ አባቶች ሲኖሩ ነው፡፡ ከአለማዊው አመጽ ይበልጥ አመጽ የሚፈጸመው በእምነት መሪዎች ነው፡፡ ሶዶሚያውያን ናቸው፣ አመጸኞችና በጥበባቸው የሚመኩ፣ ለጨለማ ስራ ድጋፍ የሚሰጡ የሚያበረታቱ ናቸው፡፡ በጥቅሉ ለዲያብሎስ ስራ የተጉ ናቸው፡፡
ከተጣመመና የእግዚአብሄር
መንፈስ ቅዱስን ትምህርትና ፈቃድ፣ ከናቀና ካደፈረሰ፣ ከደለዘና ከለወጠ የድፍረት
ትምህርታቸው በላይ አመጻቸው የበረታ ነው፡፡ ነፍሰ ገዳዮችን የሚባርኩ፣ በእምነት ሽፋን የፖለቲካን ስራ የሚሰሩ፣ ወደ ተለያየም ስፍራ ሲሄዱ በቀሚሳቸው የረቀቀ የዲያብሎስን ተልእኮ ለማስፈጸም የሚተጉ ናቸው፡፡ እናንተና የእግዚአብሄር ትእዛዝ ወዴት ስትተዋወቁ ! ህንጻ ቢያምር እውነትን አያሳይ በረቀቀ ጥበብ ቢሰብክ አያንጽ፡፡ ውስጣችሁ በአመጽ የተገነባና ለቢያብሎስ ፈቃድና ለጨለማ አሰራር የተገዛ በመሆኑ እንዴት መልካም ይወጣችኋል?
ትን ኢሳኢያስ 28 ፡ 3 – 29
የካቶሊኩ መሪና የእስልምና መሪዎች እርስ በእርስ በመጽሐፋቸው ሲመራረቁ የታየ ሲሆን የደም አፍሳሾችን መጽሐፍ እንደ መልካም ከቆጠረና ከዘከረ በምን መልኩ ነው መንፈሳዊ መሪ ሚሆነው? በሚመራቸው የእምነት ተቋሞች ሰዶማውያን ሞልተውበትና፤ የፖለቲካ ሰራተኛ በሆኑበት የእግዚአብሄር ፈቀድና ትእዛዝ በፈረሰበት እንዴት ነው ያላመነ የሚያምንበት? በምንስ መልኩ ነው የመንፈስ ስብራቱ የሚጠገንበት? በመጀመሪያው መልእክት እንደተገለጸው ብዙ የእምነት መጽሐፍትና የመስኩ ጠበብቶች አሏችሁ ብዙ ጽፋችኋል፡፡ እንደ ስጋው እውቀት እሰከ ዶክተር ማእረግ የሚያደርስ የቲዎሎጂ ትምህርት ማስረጃ ትሰጣላችሁ፡፡ ብጹእ፣ በጹእነታቸው
ትባላላችሁ፤ጳጳስ የተከበሩ ትባላላችሁ፡፡ የከበሬታ ወንበር በሄዳችሁበት ሁሉ ለናንተ ነው፡፡ ልብሳችሁ ያማረ ነው፡፡ ዝማሪአችሁ በብዙ መሳሪያና የሰው ጩኸት የተመላ ነው፡፡ ፕሮቴስታንቱ፣ አንጀሊካኑም፣ እስላሙም፣ ቡዲስቱም፣ ሌላውም ሁሉ እንደናንተው ነው፡፡
ኤሌክትሮኒክ ሚዲያው የናንተ ነው፡፡ መሰብሰቢያው ሁሉ የናንተ ነው፡፡ እጅግ የበዛ ሃብትም ባለቤት ናችሁ፡፡ የዘመኑ ሊቀውንት የፖለቲካ መሪዎች ለጥፋታቸው ሲሰማሩ መርቃችሁ አበረታታችሁ የምትልኩ እናንተ ናችሁ፡፡ የእውቀታቸውም የጥበባችውም አምላኪ ናችሁ፡፡ ልባችሁ ከነዚህ ከዲያብሎስ ልጆች ጋር ነው፡፡ ጀርባችሁን ለእግዚአብሄር ሰጥታችኋል፡፡ ለጸሎት በሚል ትሰባሰባላችሁ፡፡ ሰሚ የላችሁም፡፡ ፈጣሪ እናንተን ከሚያዳምጥ ጆሮውን ከደፈነ ቆየ፡፡ እንደ ፋንድያ ጭስ የሚሸተውን ጩኸታችሁን እንኩአን ሊየዳምጥ ሊታገሳችሁና ሊሸከማችሁ ታክቶታል፡፡
የዳዊት መዝሙር 35 ( 36 ) ፡ 1 – 4
በአለማችን ላይ መልከ ብዙ እምነቶች ምድርን ሸፍነዋል፡፡ የጥፋት መንገድ ሰፊ፤ የመዳን መንገድ ጠባብ፤ መሆኑን ሁሉም የሚያውቀው ነው፡፡ ሰፊው መንገድ የዲብሎስ መንገድ ነው፡፡ ስሙን ብቻ በለበሱ በውስጣቸው እውነት በሌለቸው የዲያብሎስ ልጆች የተሞላ ነው፡፡ ስማቸው ብዙ ነው፡፡ ካቶሊክ፣ ፕሮቴስታትን፣ እስላም፣ ቡዲዝም፣ ሺንቶኢዝም፣ ታኦኢዝም፣ ቁጥራቸው የበዛ ነው፡፡ አንዳንዶቹ
የክርስትና ካባ የለበሱ ውስጠ ባዶ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ ፍጹም ጣኦት የሚያመልኩ ናቸው፡፡ ሌሎቹም ፍልስፍና መሰል እምነቶች ናቸው፡፡ ከአለም 6 ቢሊዮን ህዝብ ቁጥር 90 በመቶ የሚሸፍኑ ናቸው፡፡ በድምጽ ብልጫ የፈጣሪን እጅ ሊጠመዝዙ እነደሚችሉ የሚያምኑና የሚገምቱ የሰይጣን ልጆች ናቸው፡፡
ይህ የሚያስታውሰው
ባንዱ የእግዚአብሄር
ሰው የሆነው ኤልያስና የእስራኤልን ህዝብ ይመሩ ከነበሩ ኤልዛቤልና አከአብ ከነ 400 የበአል ቀሳውስት ጋር የተደረገን ፍልሚያ ነው፡፡ በዚህ ፍልሚያ በብዙ ሺ የሚቆጠሩት የኤልዛቢል ልጆች የአከአብ ህዝቦች የቡኤል ዘቡኤል ካህናት በአንዱ ኤልያስ ላይ ዘምተው፤ በዚሁ በአንዱ የእግዚአብሄር የታመነ ባሪያ ተመትተዋል፡፡
በዘህ ንጽጽር ስናይ በአለም ሁሉ ፊት ከ5 ቢሊዮን በላይ የሚሆነው ህዝብ የተለያየ ስም አንጠልጥሎ ሁሉም በቀደመው ዲያብሎስ ( እባብ ) እየተመራ 99 በመቶ የአለም ህዝብ ከፈጣሪውእርቆ ከዚህ የዲያብሎስ አዝማቾች ጋር ቆሞአል፡፡ በተጻራሪው በቁጥርም በሃብትም በሁለመናዋ እጅግ ያነሰችው ሁሌም በነዚሁ የተቀጠቀጠችው የተዋህዶ ኦርቶዶክስ ቆማለች፡፡ ኤሊያስ ብቻውን ከፈጣሪው ጋር ቆመ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስን በአለም ካሉ ጥቂት ወንድሞችዋ ጋር ከፈጠሪዋ ጋር፣ ከፈቃዱና ከትእዛዙ ጋር ቆማለች፡፡
ማን ያሸንፋል ኋላ እናያዋለን፡፡ የተውህዶ ኦርቶዶክስን እምነት በአሁኑ ሰአት በታላቅ ፈተና የወደቀች ከውሰጥም ከውጭም በጠላት የተወረረች በታለቅ ፈተና ላይ ያለች ነገር ግን የማትጠፋ የገሃነም ልጆች ሁሉ የከበቡአት ሆናለች፡፡
የመላው አለም የዲያብሎስ ፊት አውራሪና ሰረዊቱ በዚች የተዋህዶ እምነት ላይና የጸና መሰረቷን ባጸናችባት በአገሬ በኢትዮጵያ ላይ ለዘመናት የቆየና የሸበተ ሁለ ገብ ጦርነት አካሂደውባታል፡፡ እያካሄዱም ይገኛሉ፡፡ ዛሬም በአመራርዋና በውስጥዋ የተቀመጡት ከጠላት የወገኑ የጠላትን ፈቃድ በማስፈጸም ላይ የሚገኙ ሲሆን ከማእከል እሰከ መንደር ድረስ በዘለቀ እጅና እግራቸው የቤተክርስቲያንዋን መሰረትና ጽናት ለመናድ እየተጉ ይገኛሉ፡፡ የፖለቲካው መሳሪያ በመሆናቸው ከመንግስት ኃይሎች ጋር በመተባበር እያፈረሱ ለመሆናቸው ሁሉ የሚያውቀው እውነት ነው፡፡ ህዝቡም ፍጹም ስቶ የዘመናችንን የጥፋት ሰዎች ባህልና እምነት ወርሶ
የዲየብሎስ ሰራተኛ ሆኖአል፡፡ አመንዛሪ ነው፣ ሌባ ቀጣፊ፣ ነፍሰ ገደይ፣ ሃሰት ተናጋሪና መስካሪ ነው፡፡
አምላካችሁ የሆነው የቀደመው እባብ ዲያብሎስ ለጥፋት አላማው ከአያት ቅድመ አያቶቻችሁ ጀምሮ እሰከ አሁን እየዘለቀ ባለው ጊዜ የተለያዩ የጥፋትና የጨለማ ህጎቹን አስጨብጦአቸዋል፡፡ ሰማይና ምድርን የፈጠረውን አምላክ ፈቃድና ህግ ንቃችሁ በዲያብሎስ ህግና ፈቃድ የምትመሩ ሆናችኋል፡፡
ማመንዘር መብት ነው፣ መዋሸት ጥበብ ነው፣ የደሃን ፍርድ ማጣመም ትክክል ነው፣ ለባለሃብቱና ለባለስልጣኖች ቆሞ ድሃን ማሳደድና መበደል ፤ አግባብ ነው ብላችኋል፡፡ ዘረኝነትን፣ ሰዎችን በዘራቸው የበለይና የበታች ማድረግ፣ ሰዶማዊነት፣ የወሲብ እንዱሰትሪ፣ የድሃን ጉልበትና ልፋቱን መንጠቅ የጥፋት መሳሪያ አዘጋጅቶ ህዝብን ማፋጀት፤ እኒህ በሙሉ ትክክለኛ ስራ ናቸው ብላችኋል !!
ባቢሎን (አሜሪካ)፣ ግልገል ባቢሎናውያን (አውሮፓ )የሚያወጡት ህግ የአባታቸው የዲያብሎስን በመሆኑ በዚህ በመመራት በጅምላም ሆነ በነጠላ የማይፈጽሙት ፍጅት የለም፡፡
ትንቢተ ኤርሚያስ ም 23 ፡ 9 – 40
ዛሬ ገንዘብ አምላክ ነው፡፡ በገንዘብ የማይገዛ ነገር የለም፡፡ የሁሉም ሰው ጣኦት ገንዘብ ነው፡፡ ዓለም በሙሉ ህልውናውን ለገንዘብ ሽጧል፡፡ ገንዘብ ደግሞ ዋነኛው የዲያብሎስ መሳሪያ ነው፡፡ ለዲየብሎስና ለናንተ ለጭፍሮቹ ብቻ የሚጠቅም የዲሞክራሲ መብት ትላላችሁ፡፡ አዘጋጅታችሁ ሁሉንም ህዝብ በዚህ ትነዳላችሁ፤ ለዚህ ዲሞክራሲ ለሚባለው ብሂልና ህጋችሁ አልገዛም ፤ በፈጠረኝ አምላክ ህግ ነው የምገዛው ያለውን ሰውም ሆነ ተቁአም ታሳድዳላችሁ፤ ትገላላችሁ፣ ታስራለችሁ ይህም ዘወትር የምትፈጽሙት ተግባራችሁ ነው፡፡
በአለም ላይ እንድንኖር የፈጠረን አምላክ የሰጠንን የፈቃዱን ህግና ስርአት በተዋህዶ ኦርቶዶክስ እምነት ጸንተው አባቶቻችን አልፈውበታል፡፡ ለእግዚአብሄር እውነት ተሰውተውበታል፡፡ የሚፈለገውንም ዋጋ ከፍለው አልፈዋል፡፡
ይኸው ተዋህዶ ኦርቶዶክስ እምነት በአገሬ ቆማ አልጠፋ ብላችሁ ፤ እነሆ እሷንም እንደ ድርጅት ለማጥፋት የተሳካላችሁ ሆኗል፡፡ እንደግል እምነት ግን በየሰው ልብ ውስጥ እግዚአብሄር ስለተከላት አልጠፋ ብላለች፡፡ ቫቲካን፣ ፕሮቴስታንት፣ ሙስሊም፣ ቡዲዝም፣ ሂንዱዚም፣ ኮንፊሽየስ ፣ ማናቸውም የእምነት ድርጅቶች ቅርጽ የያዘ በሙሉ ህልሙም፣ ጥረቱም፣ ዘመቻውም ይህቺን የእግዚአብሄር ቤት የእውነት ደጅ ፈጽሞ ማጥፋት ነው፡፡ ሁሉም የአለም ገዥዎች ፤ የእምነት መሪዎች በመሪያቸው በጨለማው ገዢ እየተመሩ ተዋህዶን ለማጥፋት ይደክማሉ፡፡ የሾሙአቸው፣ ያሳደጉአቸው፣ የኮተኮቱአቸው ጳጳሳት ስራቸው ይኸው ነው፡፡ ለዚህም ዛሬ በኢትዮጵያ ምድር ቁጥር የበዛ እስላም፣ ፕሮቴስታንት፣ ካቶሊክ ሌላም ሌላም የሞላው፡፡ ይህ ሁሉ የእምነት
ተቁአምና ድርጅት ከጠዋት እስከ ማታ ዘምቶና አጥፍቶ የሚገባው የተዋህዶ ኦርቶዶክስ እምነትን ነው፡፡
ዘመቻቸው እመጨረሻው ጣሪያ ላይ በመድረሱ በውጭዎች የተተከሉት ጳጳሳት፣ ዲያቆናት፣ አገልጋይ ተብየዎች በተለያየ የዲያብሎስ የዘመቻ ስልት ተመርቀውና ተክነው ለሆዳቸው ያደሩ ሆነው የተለያየ የጠላት ዶክትሪን አንጠልጥለው እንደ ቅባት፣ ጸጋ፣ ተሀድሶ፤ የሚል የዲያብሎስ የረቀቀ ማጥፊያ አዝለው የማፍረስ ስራ መስራት ከጀመሩ ረጅም ዘመን ተቆጠረ፡፡ ከዚህ የዘለሉትን በሆዳቸው እንዲያስቡ ተደረገ፡፡ ለፖለቲካው መሳሪያ ሆኑ፣ ለፈጣሪ መገዛት ተዉ፡፡ ምዕመኑን ለአውሬ በተኑ፡፡ ሆዳቸውን ለመሙላት ከቅርስ ጀምሮ ማናቸውም ነገር ገንዘብ ያወጣል ብለው ያመኑበትን ሁሉ ሸጡ ለወጡ፡፡ አልጠፋም ያላቸው ከሰው ልብ ብቻ ነው፡፡
ይህ ሁሉ የሚቀናበረው ታዲያ ዓለምን እየነዳ ባለው የቀደመው እባብ ነው፡፡ ዙፋኑን በአሜሪካ፣በአውሮፓ፣ በኤሽያ፣ በመካከለኛው ምስራቅ ተክሎ ለተቀረው የአለም ክፍል እንደየአቅማቸው የሚመጥን ማዘዣ ጣቢየ አደራጅቶ ዓለምን ወደ ጥፋት እየነዳ ይገኛል፡፡ መቀመጫውና ማዘዣው በአለም የታወቁ ከተሞች ናቸው፡፡ ሁሉም ሰው እንደገነት የሚያያቸው ናቸው፡፡ እነኒዎርክ እነዋሽንግተን፣ እነለንደን፣ እነፓሪስ፣ እነብራስልስ፣ እነማድሪድ እነሊዝበን፣እነፔኪንግ፣ እነሞስኮ፣ እነቶኪዮ ወዘተ አይደሉም እንዴ ! በነዚህስ ከተሞች አይደለም እንዴ እንደሰናኦር ግንብ የረዘሙትን ህንጻዎችስ የምናየው ! በነዚህ ከተሞች ገዝፈው ከሚታዩት የአማሩ ህንጻዎች ፤ የነቫቲካን፣ የነፕሮቴስታነት የነአንጀሊካን፣ የነሙስሊም፣ የነቡድሃ አይደሉም እንዴ? የእምነት ዩኒቨርሲቲዎች ከሚሊዮን መጽሐፍቶቻቸው ጋር ያሉት የት ነው? ከነዚህ ከተሞች ውስጥ አይደለም እንዴ? መቼ ራሳቸውን ደበቁ በግልጽ የዲየብሎስን ስራ የሚሰሩ አኮ ናቸው፡፡ አለምንስ እንመራለን፣ እንዳኛለን ፣ እንወቅሳለን፣ እንቀጠቅጣለን፣ እናፈርሳለን እንገነባለን የሚሉትስ መሪዎች፣ጦረኞች ከነኑይክለራቸው፣ ከነጀታቸው፣ ከነሚሳኢላቸው እዚሁ አይደሉም እንዴ? በነዚህስ ከተሞች አይደለም እንዴ የምንዝርናው፣ የፊልሙ፣ የዘፈኑ፣ አስረህ ምቺው ኢንዱስትሪ የሞላው? አባታቸው ዲየብሎስ ቢሳካለት ገና ሰማይ ላይ ዙፋኑን ሊዘረጋ አይደለም የሚለፋው? ቋሚው ሳተላይት እስቴሽን ተብየው ለዚሁ ህልም አየደለም እንዴ የሚደክሙበት፡፡
ዓለምን የምታምሱበት
የጥፋት መሳሪያዎቻችሁ
ዓለም ከተፈጠረች ጀምሮ የሰው ልጅ ያስገነባው አይደለም እንዴ? ንዩክለር፣ ኒዩተሮን፣ ኬሚካል፣ ባዮሎጂካል፣ ሚሳኤሎች እጅግ የረቀቁ ጀቶች፣ ፈንጂዎች፣ ታንኮች ፣ መድፎች፣ በህዋ ላይ ደግሞ ኒዩክለር የታጠቁ ሳተለይቶች፣ በጨረር የሚጠቀሙ ማጥቂያ ሳተላይቶች ዓለምን ደጋግሞ ሊያጠፉ የሚችል መሳሪያ አከማችታችኋል፡፡ እየተጠቀማችሁበትም ነው፡፡
እናንተ የአመጽ ልጆች የፈጣሪን ትእግስት ንቃችሁ እንደሌለ እንድትቆጥሩት ሆናችሁ፡፡ ፈጣሪ የለምም ብላችሁ እንድታምኑና እንድታሳምኑ አድርጎአችኋል፡፡ ፈጣሪን እስከነመኖሩ ረስታችኋል፡፡ በአለም ሁሉ ምንዝርናን ስራ ያልሆነበትና እንደኢንዱሰትሪ ያልተደራጀበት አገር አለወይ? እንኳን ምድር ባህሩም ነጻ ሊሆን አልቻለም፡፡ የምትመሩት በምድርና በባህር ውስጥ ባለው አጋንንት ብቻ አይደለም፤ በአየርም ከሚከንፈው የጨለማው ገዢ ጋር ጭምር ነው፡፡
ስለሆነም ይህ ሁሉ ተግባራችሁ ተመዘነ ቀለላችሁ፡፡ ዛሬም ትላንትም ከአያት ቅድመ አያቶቻችሁ ጀምሮ ለ 7000 ( ሰባት ሺ ) አመታት ስትመዘኑ ሰትለኩ አለፈ፡፡ በየመዝገባችሁ የሞላው የአመጽ ስራችሁ በሁሉም መስፈርት የሞት ፍርድን ወለደላችሁ፡፡ ለምህረትም የሚያበቃ ነገር ከውስጣችሁ ተፈልጎ ጠፋ ! እነሆም ፍርዱ ወጣ ተወሰነም፡፡ ዓለም አድምጥ !! ከእንግዲህ የናቅሃት ከነጭርሱም የማታውቃት ኢትዮጵያ በሰራዊት ጌታ ፊት የ 7000 ( ሰባት ሺ ) ዘመን ልፋቷ ታሰበ፡፡ ተወደደች ፡፡ እግዚአብሄር ወደዳት ባለድል ሆነች፡፡ ስማ የሰው ዘር !! ኢትዮጵያ በመንፈሱም በስጋውም ዓለምን የምትመራ፣ የምትገዛ ሆና በልዑል እግዚአብሄር ተሾመች !!
እንደ ፀሀይ የሚያበሩ የእምነት አርበኞቿ ተቀቡ ! ተሾሙ ! በአምላካቸው ተወደዱ !!
ደምህን አዝርተህ፣ እምባህን እረጭተህ ፣ በጉልበትህ ተንበርክከህ፣ ቅጣትህንና ፍርድህን ተቀብለህ ለምህረት የተረፍከው ትውልድ ብቻ እጅህን ለኢትዮጵያ ትሰጣለህ፡፡ የኢትዮጵያን ትንሳኤ ታያለህ ! ለዚችው ለተባረከች ምድር ትገብራለህ ! የሰረዊት ጌታ እግዚአብሄር ይህን ያደርጋል ! እወቅ የሰው ዘር ! ጌታ በከበረው ስሙ ምሏል፡፡ እኛም የታመንን ባሮቹ የውሳኔውን ማህተም ጨብጠናል፡፡ አስፈጻሚውም ከደጅህ ቆሟል፡፡ እንደ ንስር ዙሪያህን ይዞራል፤ አታመልጥም መሸሸጊያም የለም፡፡
በሰራዊት ጌታ እግዚአብሄር ስም ፤ በእመቤቴ ድንግል ማሪያም ስም አረጋግጥላችኋለሁ፡፡ ተፈጸመ ! ተከደነ !
ትንቢተ ኢሳኢያስ ም ፡ 62
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን
የሰራዊት ጌታ ስሙ ይባረክ !!!
በኢትዮጵያ ምድር ላላችሁ ከኢትዮጵያም ውጭ ላላችሁ ዜግነታችሁን እምነታችሁን ያልጣላችሁ ወገኖቼ በሙሉ ! ይህ በህይወታችሁ በአገራችሁ በኑሮአችሁ በዘራችሁ በሃብታችሁ ሁሉ ወሳኝ ሆነውን የአምላካችንን ፍርድና የመጨረሻው የቅጣት አመጣጥና የማዳኑን ውሳኔ ከዚህ በታች ባለው የመጨረሻው መልእክት እንድታነቡና ለሁሉም ወገናችሁም ሆነ ለሰው ዘር በሙሉ እንድታደርሱ በፈጠሪ ስም እጠይቃችኋለሁ፡፡
ትን ኢስአያስ መዕ - 18
ይህ መልእክት እንደጉዳያቸውና በህይወታቸው ወሳኝ ጊዜ ላይ መድረሳቸውን ለተገነዘቡ የፈጣሪም ተግሳጽ
ለሚያስደነግጣቸው ወደንስሃ ለሚመልሳቸው ( እንደ ነነዌ ህዝብ ፈጥነው ለሚመለሱ መዳኛቸው ሲሆን ) ለሚንቀው ለሚተቸው ለሚያንጓጥጠው ደርሶ አዋቂ ነኝ ብሎ ለሚመጻደቀው የትችትና የአሽሙር ምላሱን ለሚያስቀድመው ፤ ተውት ለሞት ልጅ አንዴ ለታወረ ምንም ቢሉት አይመለስም ፡፡ ፈጣሪያችን ከነ ክብሩ እንኳ ወርዶ ቢያናግረው አይሰማም፡፡ ለእሳት የተጻፈ ለእሳት ነው፡፡
የኢትዮጵያንና የአለምን መልካም አያይም ! ከመጪው የበረከት ዘመን አይደርስም ! ስለዚህ ለሰው በሙሉ በየትኛውም አለም በትኑ ! የፍርድ ቃል ነው ! አድርሱ ! አውቆ ይዳን ! አውቆ ይለቅ ማሳወቅ ብቻ ነው የኛ ግዴታ !!
አፌ ጽድቅህን ሁሉ ግዜ ማዳንህን ይናገራል በእግዚአብሄር ኃይል እገባለሁ አቤቱ ጽድቅህን ብቻ አስባለሁ አምላኬ ከታናሽነቴ ጀምሮ አስተማርከኝ እስከዛሬም ታምራትህን እናገራለሁ እስካረጅም እስክሸመግልም ድረስ ለሚመጣው ትውልድም ሁሉ ክንድህን ኃይልህንም ጽድቅህንም እስክነግር ድረስ አቤቱ አትተወኝ
መዝሙር ዳዊት 70 ( 71 ) 15 – 18
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፡፡ አገራችንን ኢትዮጵያን ፈጣሪያችንና አዳኛችን፤ ለእናቱ ለድንግል ማሪያም የበረከት ልጆች አድርጎ፣ ምድሪቱንም እኛንም የሰጠ ጌታ የተመሰገነ ይሁን፡፡ በአባታዊ ቅጣቱና ማስተማሩ በጸጋው እየሸፈነ ሰው እንድንሆን ለመከረን፣ ለመራን፣ ላኖረን፣ ለቸሩ ፈጣሪያችን ምስጋና ይድረስ፡፡ እግዚአብሄር አብ፣ እግዚአብሄር ወልድ፣ እግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስ፣ አሃዱ አምላክ የተመሰገነ ይሁን አሜን !!
የነበረ ያለ የሚኖር ከመኖር ወደ አለመኖር የሚለውጥ ካልነበረ ወደህያውነት የሚያመጣ ማንም በማይቀርበው ብርሃን ውስጥ ያለ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሄር የተመሰገነ ይሁን !! የኢትዮጵያ ህዝብ አድምጠኝ ! አስተውል ! ሁሉም ነገር አበቃ የፍርድም ሰአት ደረሰ፡፡ የቀረችውም ትንሽ ጊዜ አለቀች፤ የመጨረሻው የፈጣሪያችን የአምላካችን መገለጫ የፍርድ ሰአት ደረሰ !!
የወደደን በአለም ሁሉ ፊት ለክብሩ ሊያቆመን ከዘመናት ጀምሮ አያት ቅድመ አያቶቻቸው የከፈሉትን፣ የደከሙበትን፣ የታመኑለትን፣ ለኛ ለልጆቻቸው ሊከፍለን ለወደደው እግዚአብሄር አብ፣ እግዚአብሄር ወልድ፣ እግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ ከዘለአለም እስከ ዘለአለም ምስጋና ይግባው፡፡
በፈጣሪ ፊት ለተወደደው የኢትዮጵያ ህዝብ !
በተዋህዶ እምነትህ የጸናህ ውርደትን መከራን የጠጣህ !
በድንግል ማርያም እናትነት ያመንክና በአማላጅነቷ በኢትዮጵያ ባለ ርስትነቷ ታምነህ ለቆምክ !
ውርደቱ ንቀቱ ማጣቱ መገፋቱና መጠላቱ መገደሉ መገረፉ መታሰሩ ሁሉ ሳይበግርህ በፈጣሪህ ታምነህ ቆመህ እንባህን ላፈሰስክ ወገኔ ሰላም ይብዛልህ፤ ደምና አጥንትህን ለገበርከው የእግዚአብሔር ውድ የኔም ወንድም፤ ከዚች ቅድስት ምድር አብረን ለበቀልነው ወገኔ፤ በዱር በገደሉ ለምትንከራተተው የሰራዊት ጌታ የእምነት አርበኞች የተዋህዶ ኦርቶዶክስ ጀግኖች !!
ከቤተክርስቲያን ተባራችሁ በተኩላ ለተሰደዳችሁ ሁሉ፤ የበይ ተመልካች ሆናችሁ በዘረኞች፣ በአመንዛሪዎች፣ በነፍስ ገዳዮች፣ የእምነት ካባ በለበሱ ቀጣፊዎች ለተረገጣችሁ፣ ቤት ንብረታችሁ ተነጥቆ፣ ትዳራችሁ ፈርሶ፣ ለልመና የተዳረጋችሁ ወገኖቼ !
እንደ ክረምት ሙጃ ሁሉን ቦታ ፈሰውና በቅለው ወፍረው ባበጡ የሙስሊም፣ የፕሮቴስታነት፣ የካቶሊክ፣ የጥንቆላ ሰረዊቶች ለተመታችሁ ለተዋረዳችሁ ወንድሞቼ እህቶቼ !
መንግስት ተብየው በኮለኮላቸው የሆድ አምላኪዎች ዘወትር ለምትገፋና ለምትጨነቁ በሙሉ !
ሰአት ደረሰ ፍርዳችሁን እንደፀሀይ የሚወጣው የሰራዊት ጌታ እነሆ በደጅህ ለፍርድ ቆሟል፡፡ ልትደሰቱ ህሊናችሁን ልታዘጋጁ ይገባል፡፡ ብዙ ወገኖቻችን መልካሙን ቀን ለማየት አየተመኙ የጌታ ፈቃድ አልሆነምና አልፈዋል፡፡ ለአገራቸው ለእምነታቸው ለህዝባቸው ተጨንቀው ተጠበው በጨለማው ገዢ ተረግጠው ተከፍተው ወደ ጌታችን እቅፍ ሄደዋል፡፡ ዛሬ በህይወት ያለነውም በዲየብሎስ እስራት ተጠፍረናል፡፡ ለረሃብና ለችግር፣ ለሞት ለመንከራተት፣ ለእስራት ለስደት ተመድበን በዚሁ ሰንሰለት ኖረናል፡፡
ብዙዎቻችን አምላካችን ዘገየ ብለን ተስፋ ቆርጠን ለጠላት እስከመንበረከክ ደርሰናል፡፡ እረኛ የሌለው ተቅበዝባዥ በጎች ሆነናል፡፡ የተኩላ እራትም እስከምንሆን ዘልቀናል፡፡ ወገኔ ! በዘርህ ተለይተህ ተረግጠሃል፣ በእምነትህ ተጠልተሃል፣ በአገርህ በጠላትነት ተፈርጀሃል፣ ይህችን አገር የማያውቋት ለጥፋቷ ለሚደክሙና ከአያት ቅድመ አያቶቻቸው ጀምረው ሲያጠፏት የኖሩ የሁሉ ነገር ባለቤት ሆነዋል፡፡ ሁሉንም ወርሰዋል፤ ሃብት ንብረት ሰበስበዋል፤ ገንብተዋል፤ ወደ ነጩ ምድርም አፍልሰው አከማችተዋል፡፡ ማንም አይነካንም ብለው ራሳቸውን በግንብና በምሽግ ከልለው ተቀምጠዋል፡፡ በጦራቸው፣ በጀታቸው፣በታንካቸው በወታደሮቻቸው
ታምነዋል፤ አውሮፓ፣ አሜሪካ፣ ቻይና፣ ህንድ በወዳጆቻቸው ታምነዋል፡፡
ወገኖቼ ኢትዮጵያውያን
! አገራችን መጠለያችን እንድትጠፋ እሷንም የሚወዱ ልጆቿ ከእምነታቸው እንዲከስሙ ተወስኖ መስራት ከተጀመረ ብዙ ዘመናትና አመታት አልፈዋል፡፡
አንድ ህዝብ፣ አንድ የተዋህዶ ኦርቶዶክስ እምነት፣ አንዲት አገር፣ አንዲት አረንጉአዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ ብሎ ያመነና በዚህ የጸና ወገኔ ወንጀለኛ ነው፤ ስለሆነም ይሳደዳል ይገደላል ይታሰራል ቢዘረዝሩት ብዙ ነው፡፡ያለቀውና የደቀቀው ማንነትህ ይገልጸዋልና !!
ትግስቱ የማያልቅበት
አምላክ አሁን ግን ትእግስቱ አለቀና አበቃ ! በስጋችንም ያመንናቸው ያደራጀናቸው ተበተኑ፡፡ ተስፋችን ጨለመ፤ በመሆኑም መታመኛ ጥበብ ሁሉ አለቀ፤ በመሆኑም ይህን የተመለከተው አምላካችን ትግስቱ ተሟጧል ! የማዳን ክንዱን አነሳ፤ ፍርዱን እንደጸሀይ ሊያወጣ ከሰማይ ማንጎዳጎድ ጀመረ !!
ተስፋህን አለምልም ወገኔ አባትህ የታመነው ጌታ ደርሱአል !!!
አንተ ባህርን በክንድህ አጸናሃት፤ አንተ የእባቦችን ራስ በውሃ ውስጥ ቀጠቀጥህ ( ሰበርህ ) አንተ የዘንዶውን ራሶች ቀጠቀጥህ ለኢትዮጵያ ህዝቦችም ምግብን ሰጠሃቸው
መዝሙረ ደዊት 73 ( 74 ) 13 – 14
Blogger Comment
Facebook Comment