ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን - መልዕክት አንድ




በምድሪቱ ሁሉ ላለህ የሰው ዘር በሙሉ

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን!!

የፍጥረት ሁሉ ጌታ ስሙ የተመሰገነ ይሁን አሜን!!

በምድሪቱ ፊት ሁሉ ተበትናችሁ ለምትኖሩ ህዝቦች፣ በተለያየ ቋንቋና ዘር ነገድ ተከፋፍላችሁ፣ በአህጉር በአገር፣ በቀበሌ፣ በመንደር ለተበተናችሁ የሰው ዘር በሙሉ!!

በዚህ ዘመን አለምን ለምትመሩ መሪዎችና ገዢዎች፣ በምድሪቱ ሁሉ ባሉ የእምነት ተቋማት በመሪነት በአስተዳዳሪነት፣በሰባኪነት እናም በአደራጅነት፣ ለምትመሩ እንዲሁም እምነታችሁን በማስተማር ለተማስራችሁ የእምነት አባቶች ሁሉ!!

ለጥበበኞች፣ ለፈላስፎች፣ ለጦር አለቆች፣ ለነገስታቶች፣ ለአለም አቀፍ ድርጅቶች፣ መሪዎች፡፡ ዓለምን በጥበባችን፣ በሃብታችን በጉልበታችን እየገዛነው ነው ለምትሉ፤ በተለይ ለታላቋ አሜሪካ (ባቢሎን) ከሷም ጋር ዘወትር ለሚያመነዝሩ ጋለሞታ ወዳጆቿ፣ አውሮፖውያን፣ ኤሻውያን፣ አረባውያን፣ ላቲን አሜሪካውያን፣ አፍሪቃውያን፣ እንዲሁም በታላቋ ባቢሎን (አሜሪካና) አውሮፖውያን ተጠፍጥፈው ለተሰሩ ህዳጣን ጋለሞታ መንግስታት በሙሉ!!

በዚህ ክፉ ዘመን እራሳችሁን በታላቅ ፈተናና መከራ ውስጥ ለጣላችሁ፣ ስለእምነታችሁ፣ ስለፈጣሪያችሁ መውደድና መታመን በታላቅ ጉዳት ላላችሁ የእግዚአብሄር ልጆች በሙሉ!!

እኔ ቃል ተመልቻለሁና በውስጤም ያለ መንፈስ አስገድዶኛልና በተሃ ጠጅ እንደተሞላና ሊቀደድ እንደቀረበ አቁማዳ ሊፈነዳ እንደማይችል እንደ ወይን ጠጅ አቁማዳ እነሆ አንጀቴ ሆነ ጥቂት እንድተነፍሰ እናገራለሁ ከንፈሬን ገልጨ እመልሳለሁ መጸሐፈ ኢዮብ 32 18 – 20 ከላይ በእግዚአብሄር ቃል እንደተመለከተው ይህንን መልእክት እናገር ዘንድ ግድ ስለሆነብኝ እናገራለሁ፡ ላለመናገር ላለመተንፈስ ከራሴም ከፈጣሪየም ጋር ተሟግቻለሁ፡፡ እንደ ዮናስም እምቢ ብያለሁ፡፡ ይሁንና ከእግዚአብሄር ሃይል ጋር ተሟግቼ ስላልቻልኩ፣ እየከፋኝ ይህንን ትእዛዝ እፈጽም ዘንድ ግድ ሆነብኝ፤ ስለዚህም እንሆ እናገረው ዘንድ የሚገባኝን የዓላማችንን መጻኢ ሁኔታ እናገራለሁ፡፡ ይህ ማስጠንነቀቂያና መፃኢ ፍርድ ይድረሳችሁ !!

እኔ እጅግ ታናሽ ሃጢያተኛ በእውቀትም ያነስኩ በኑሮዬም ምናምቴ ወዳቂ ኑሮ የምገፋ ነኝ፡፡ እናንተ በድህነቷ የምታውቋት ኢትዬጵያ ዜጋና ድሃ ልጇም ነኝ፡፡
መልእክቱ አራት ክፍሎች አሉት
1
/ ለዘመናችን ጥበበኞች፣ ገዢዎች፣ ባለጠጎች ፣የሃጢያት ባለሃብቶች፣ አመንዛሪዎች፣ ግብረ ሶዶመች፣ነፍሰ ገዳዮች፣ ዘራፊዎች ነጣቂዎች፣ ድሃ አጥፊዎች በጥቅሉ የቀደመው እባብ (ዲያብሎስ) ልጆችና አገልጋዮች በግልጽ በእግዚአብሄር ህግና ስርአት ላይ የማፍረስ ስራ በመስራት ፍጹም የጨለማን ስራ ላነገሱ የዘመኑ እባቦች ዘንዶዎችና ጊንጦችን ይመለከታል፡፡
2
/ በእምነት ካባ ተጠልለው በተለያየ የእምነት ተቋም ራሳቸውን ያደራጁትን ማለትም እንደ ካቶሊክ ቤተ-ክርስቲያን፣ኘሮቴስታንት፣ አርቶዶክስ፣ አንግሊክና እናም ሌሎች በክርስትና ስም ራሳቸውን ያደራጁ ተቋማትን ይመለከታል፡፡ ሙስሊም፣ ቡዲሂዝም፣ ኮንፊሺያን፣ ሂንዱይዝም እናም ቁጥራቸው የበዛ የእምነት ተቋማትን ይመለከታል፡፡
3
/ በምድሪቱ ላይ በሰፈነው ብርቱ ሃጢያትና ማእበሉ ዘወትር እየተሰቃዩ ላሉ የእግዚአብሄር ህዝቦች ይመለከታል፡፡
4
/ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ገዢዎቿን መጪውን እድሏን ይመለከታል፡፡
ባጠቃላይ አለምን በስራና ተግባሯ ተመስርቶ የሚጠብቃትን ቅጣትና ፍርድ ከዚያም ያለውን መፃኢ ሁኔታ የያዘ መልእክት የምታገኙ ሲሆን ይህንን መልእክት ለመስማት ባትወዱትም ወይም ባትፈቅዱትም የማይቀር ስለሆነ ፍርዱ በራሳቸው ላይ የሚያርፍ ይሆናል፡፡ የምትታመኑበት እውቀት፣ ጥበብ ብልጽግና ወይም የሃሰት አባታችሁ በፍጹም አያድናችሁምና
-
ለበደለኞች የመት ፍርድ መርዶአቸውን የሚሰሙበት
-
ለመልካሞች የእግዚአብሄርን ታዳጊነትና የታመነ አባትነቱን የሚያረጋግጡበት ነው፡፡

/ በአንደኛው መልእክት ለተጠቀሳችሁ ጆሮአችሁን ከፍታችሁ አድምጡ!
የዘመናችን ጉዶች ለመሆኑ እናንተ ማናችሁ! ይላል ጌታ እግዚአብሄር፡፡ ራሳችሁን ያሰማራችሁ በትእቢት የተሞላችሁ ፍጹም የታበያችሁ ምድርንና ሰማይን የዘረጋውንና የፈጠረውን አምላክ የናቃችሁ እኮ እነማናችሁ! የቀደመው እባብ ልጆች በፈጣሪ የተላገዳችሁ፣ እኮ እነማናችሁ! እስትንፋሳችሁ ባፍንጫችሁ ስር የሆነች ብትያዙ የምትጠፉ ለመሆኑ ምንድናችሁ!

አዎ ትቢያና ከንቱዎች የከንቱም ከንቱ ናችሁ፡፡ እስኪ ጌታ የሚያጠይቃችሁን ስሙ!!
ውሆችን በእፍኙ የሰፈረ፣ ማይንም በስንዝር የለካ፣ የምድርንም አፈር በመስፈሪያ ሰብስቦ የያዘ፣ ተራሮችን
በሚዛን ኮረብቶችንም በሚዛኖች የመዘነ ማነው! የእግዚአብሄርን መንፈስ ያዘዘ ወይስ አማካሪ ሆኖ ያስተማረው
ማነው! ወይስ ከማን ጋር ተመካከረ! ወይስ ማን መከረው! የፍርድንም መንገድ ማን አስተማረው! እውቀትንስ ማን አስተማረው! የማስተዋልንስ መንገድ ማን አሳየው! እነሆ አሕዛብ በገንቦ እንዳለች ጠብታ ናቸው፡፡ በሚዛንም እንዳለ ትንሽ ትቢያ ተቆጥረዋል፡፡ እነሆ ደሴቶችን እንደ ቀላል ነገር ያነሳል፡፡ ሊባኖስ ለመንደጃ እንሰሶችም ለሚቃጠል መስዋእት አይበቁም፡፡ አህዛብ ሁሉ በፊቱ እንዳልነበሩ ናቸው፡፡ ከምናምን እንደሚያንሱ እንደከንቱ ነገርም ይቆጥራቸዋል፡፡

እንግዲህ እግዚአብሄርን በማን ትመስሉታላችሁ! ወይስ በምን ምሳሌ ታስተያዩታላችሁ!
ትንቢተ ኢሳኢያስ ምዕራፍ 4012-19 ከላይ ለተጠቀሰው የእግዚአብሄር ቃል ምን መልስ አላችሁ! ምንም የምትመልሱት የለም ነገር ግን ከፈጣሪ በላይ አዋቂዎች ሁሉን ሻሪ ሁሉን አጽኚ ሆናችኋል፡፡ የፈጣሪን ትዕዛዝ የናቃችሁ ስለሆናችሁ በራሳችሁ ህግ የምትመሩ ናችሁ፡፡

የፈጣሪን ህግ ሽራችሁ የራሳችሁን ህግ ያጸናችሁ ናችሁ፡፡ በትእቢታችሁ በንግዳችሁ በክህደታችሁ በመታበያችሁ ብዛት የሰው ዘር ከተፈጠረ ጀምሮ ያልታዩ አይነት ናችሁ፡፡

ጌታ እንዲህ ብሎ አላዘዘምን! የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ የአብርሃም አምላክ፣ የሙሴ አምላክ፣ የነኤሊያስ አምላክ፣ የነጰውሎስ አምላክ የነዮሃንስ አምላክ ይህንን ታላቅ ትእዛዝ አላዘዘምን!

የሰራዊት ጌታ እግዚአብሄር እንዲህ አላለምን! - ከኔ በቀር ሌሎች አማልእክት አይሁኑልህ
-
የጌታ የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ
-
በላይ ከሰማይ ካለው በታችም በምድር ካለው ከምድርም በታች ከውሃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ
የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ አትስገድላቸው አታምልካቸውም በሚጠሉኝ እስከ ሶስተኛና አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶቻችን ሃጢያት በልጆች ላይ የማመጣ ለሚወድዱኝ ትዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ትውልድ ድረስ ምህረትን የማድረግ፣ እኔ እግዚአብሄር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና፡ የምበላ እሳትም ነኝና
-
በከንቱ ስሜን የሚጠራውን ከበደል አላነጻውም
-
የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ፡፡ እግዚአብሄር የሰንበትን ቀን ባርኮታል ቀድሶታል አርፎበታልና!! - አባትና እናትህን አክብር፣ አትግደል፣ አታመንዘር፣ አትስረቅ፣ በባልንጀራህ ላይ በሃሰት አትመስክር፣ የባልንጀራህን ቤት አትመኝ፣ ባልንጀራህን እንደ እራስህ ውደድ!!
ኦሪት ዘዳግም ምእራፍ 20 1 – 17
ከላይ የተጠቀሱትን የፈጣሪ አምላካችንን ትእዛዝ፣ ናቃችሁ፣ ምንዝርናን እንደ ትክክል ስራ አጸናችሁ ፈቀዳችሁ፣ ተገበራችሁ፡ አልፋችሁ ተርፋችሁ ግብረ ሶዶምነትን አጸናችሁ፡፡ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አጋባችሁ፣ ተገበራችሁ ለእንስሳቶቹም እንዲሁ አደረጋችሁ ሴትን በቤተክርስቲያን ሰባኪ ጳጳስ አድርጋችሁ ሾማችሁ፡፡

አትግደል የሚለውን የፈጣሪ ትእዛዝ ጥሳችሁ ለስልጣናችሁ፣ ለሀብታችሁ፣ ለጥቅማችሁ፣ ለክብራችሁ፣ ለንግዳችሁ፣ ብትእቢት ተሞልቶ ከፍ ለማለት ላላችሁ ጥማት ስትሉ ገደላችሁ፡፡ እንዲያውም የመግደያ መሳሪያዎቻችሁ አንድና ሁለት ሰው ከመግድል አልፈው በሚሊዮን የሚቆጠርን ሰው የሚያጠፉ መሳሪያዎች ሰራችው፡፡ በዚህም ብዙዎችን በአንድ ጊዜ ገደላችሁ፤ ዛሬም እየገደላችሁ ነው፡፡ ዛሬ መገዳደልን እንደስልት በብዙ ትተገብራላቸሁ ፡፡ አያት ቅድመ አያቶቻችሁን ከቃየል ጊዜ ጀምሮ ያስተማረው የቀደመው እባብ ጋድርኤል፤ ዛሬም በአንድ አቤል መግደል የጀመረውን ማስተማር፣ በሚሊዮን እንድትገቡ አስተማራችሁ፡፡ ኒዩክለር፣ ኒዩትሮን፣ ባዮሎጂካል፣ ኬሚካል፣ ጄት፣ ቦምብ፣ ታንክ፣ ፈንጂ፣ መድፍ፣ ሚሳኤል፣ ምን ስፍር ቁጥር አለው? ይህን ሁሉ ለሰው መጥፊያ ሰራችሁ፡፡ ገደላችሁበት እየገደላችሁም ነው፡፡ ለምን? ለስልጣን፤ ለክብር፤ ለሀብት፤ ለዝና!!

አትስረቅ፤ ይህን የጌታ ቃል ሁሉም ሰው የሚጥሰው ነው፡፡ በልዩ ልዩ መልክ ሰው ይሰርቃል፡፡ ያታልላል፡፡
በሃሰት አትመስክር፤ ይህንንም የፈጣሪ ትእዛዝ እንዲሁ ሁሉም ሰው የሚጥሰው ነው፡፡ በየእለቱ ሰው አብዝቶ ሲዋሽ ይውላል፡፡ እንዲያውም መዋሸትን እንደ እውቀት፤ እንደችሎታ ያየዋል፡፡ መሪዎች ገዢዎች አስተዳዳሪዎች እንደዘዴ ዘወትር ይጠቀሙበታል፡፡ የፖለቲካ ጥበብ ብለው የውሸትን ስልት እንደእውቀት ያጠኑታል፡፡ ህዝቡንም ለመንዳት ለመግዛት ለማታለል ይጠቀሙበታል፡፡

ባልንጀራህን መውደድ፤ በፍፁም በፍፁም እንክዋን ሊተገበር ከመሰረቱ የጠፋ ሆኖአል፡፡ እንዲያውም ወንድሙን አጥፍቶ ንብረቱን ሚስቱን ይነጥቃል፣ ይዘርፋል፡፡ እናትና አባትህን አክብር፤ የሚለው ትእዛዝ እንዲሁ ከተሻረ ቆየ፡፡ አባትና እናትን እንኳን ሊያከብር፣ ሊሰማ በተገላቢጦሽ ፈራጅ ምክር ሰጪ አመራር ሰጪ ታናሽ እና ልጅ ሆኗል፡፡ ስንበትን አክብረው ቀድሰው የሚለውንም ትዕዛዝ እንዲሁ እንደጅልነት ስለተቆጠር ሰው ከሻረው ቆየ፡፡
የፈጣሪን ስም በከንቱ አትጥራ፤ የሚለው አምላካዊ ቃልና ትዕዛዝ ሽሮ በውሸት ይምላል፡፡ እንዲሁም እንደዘዴና ብልሀት ተቆጥሮ በመሀላ የፈጣሪን ስም በመጥራት ለመነገድ ለማታለል እንዲውል ተደርጓል፡፡ በመጨረሻም ከኔ በቀር ሌላ አምላክ አታምልክ፤ እኔ ቀናተኛ አምላክ ነኝና! የሚለውን አምላካዊ ትዕዛዝ በመናቅ የሰው ዘር በተለያየ አምልኮ ተጠምዶአል፡፡ ይኸውም ገንዘቡን፣ እውቀቱን፣ ክብሩንና ጣኦትን ያመልካል፡፡ ገንዘብ አምላኩ ነው፤ ስልጣን ምሽጉ ነው፣ እውቀት የኑሮ መመኪያው፣ የትዕቢት ምንጩ ነው፡፡ ፈጣሪን የሚጠራው ለአፉ እና ለይምሰል ብቻ ነው፡፡ ፈጣሪን የሚጠይቀው ያቀደውን ሊፈጽም የወደደውን እንዲያጸድቅለት እንጂ ፈጣሪ የፈቀደውን እንዲፈጽም አይደለም፡፡ ዛሬ የሚታየው እውነት ይኸው ነው፡፡

የጥበብ መጀመሪያ ፈጣሪን መፍራት ነው፡፡ ይህም የሚገለጸው ህጐችን በመጠበቅና በማክበር ወደተግባርም በመለወጥ ብቻ ነው፡፡ በፍጹም ልብ በፍጹም ሀሳብ፣ ለፈጣሪ በመታዘዝና በመገዛት፤ ብቻ ነው ፈጣሪን መፍራታችን የሚገለጸው፡፡ ይህንን ተግባራዊ የሚያደርግ አንድስ እንኳን የለም፡፡ ታዲያ እናንተ እባቦች አለምን በሀጢያት ባህር አሰጠማችኋት፤ አንድም ስፍራ ሳይቀር ፍጹም የሃጢያት ስራ ነገሰ፡፡

እንደክብርም ታየ፡፡ በጨርቃችሁ ተሸፋፍናችሁ ስትታዩ ትልቅ ትመስላላችሁ፣ በየስልጣን መንበራችሁ ስትታዩ ቅን ፈራጅ ትመስላላችሁ፤ ነገር ግን መቃብር ውጪው እንዲያምር ውስጡ ትል፣ ምስጥ እንደመላው እናንተም እንዲዚያ ናችሁ፡፡ ቤታችሁ ከተማችሁ ያምራል፡፡ ግን በውስጡ ያላችሁት እባቦች ጊንጦች፣ አውሬዎች ናችሁና ! ምድሪቷ ትሸከማችሁ ዘንድ አቃታት፡፡ በየብስ፣ በባህር፣ በአየሩ ሁሉ የእናንት ክፉ ስራ መላ፡፡ በየትኛውም የምድሪቱ ፊት የአባታችሁ የዲያቢሎስ እባቡ እጅና እግር ያልደረሰበት ያልከበበው የለም፡፡ እናንተ እንዴትስ ተሁኖ ከለመዳችሁት ከኖራችሁበት የሃጢያት ቤታችሁ ትወጣላችሁ? አትወጡም! ባህሪያችሁ ሆኗል፡፡ የእባብ፣ የዘንዶ፣ የጊንጥ ልጅ ያው እባብ ዘንዶና ጊንጥ ነው፡፡ ተፈጥሮአችሁ ሰው ይሁን እንጂ ተግባራችሁ ሁሉ የእባቡ ስራ ነው፡፡ የሰራዊት ጌታ እግዜአብሔር ስለናንት እንዲህ ይላል፡፡

ምንልባትም መጠቀምም ትችዬ ወይም ታስደነግጪ እንደሆነ ከአስማቶችሽና፣ ከህጻንነትሽ ጀምረሽ ከደከምሽበት ከመተቶችሽ ብዛት ጋር ቁሚ፡፡ በምክርሽ ብዛት ደክመሻል፣ አሁንም የሰማይን ከዋክብት የሚቆጥሩ፣ ከዋክብትንም የሚመለከቱ በየመባቻውም የሚመጣውን ነገር የሚናገሩ ተነስተው ከሚመጣብሽ ነገር ያድኑሽ፡፡ እነሆ እንደ እብቅ ይሆናሉ፡፡ እሳትም ይጥላቸዋል፤ ሰውነታቸውንም ከነበልባል ሀይል አያድኑም፣ እርሱም ሰው እንደሚሞቀው ፍም ወይም በፊቱ ሰው እንደሚቀመጥበት እሳት ያለ አይደለም፡፡ የደከምሽባቸው ነገሮች እንዲህ ይሆኑብሻል፡፡ ከህፃንነትሽ ጀምሮ ከአንቺ ጋር ይነግዱ የነበሩ እያንዳንዳቸው ወደ ስፍራቸው ይሄዳሉ፡፡ የሚያድንሽ የለም፡፡ ትንቢት ኢሳያስ 47 12 – 15 ከላይ በሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ቃል እንደተነገረው የሚያድን የለም፣ የገነባችሁት ሁሉ ይፈርሳል ትቢያም ትሆናላችሁ፡፡ ፋብሪካችሁ ከተማችሁ የስልጣኔ አውታራችሁ፣ ከትንሽ መንግስትነት እስከ ልቅ ኃያል መንግስትነት ለመድረስ የደከማችሁበት ሁሉ በምትታመኑበት እውቀት፣ ጥበብ፣ ስልጣኔ ደረጃ አይድንም፣ ትቢያ ይሆናልና፡፡ አንተ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ፤ አህዛብንም ያዋረድክ አንተ ሆይ እንዴት እስከ ምድር ድረስ
ተቆረጥክ፤ አንተም በልብህ ወደ ሰማይ አርጋለሁ፣ ዙፋኑንም ከእግዜአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፣ በመሰብሰቢያ ተራራ ላይ እቀመጣለሁ፣ ከደመና ከፍታዎች በላይ አርጋለሁ፣ በልዑልም እመሰላለሁ አልህ፡፡ ትንቢት ኢሳያስ 14 12 – 14 አባታችሁ የቀደመው እባብ ህልሙ ከላይ በጌታ እንደተገለጸው ነው፡፡ እሱ ያስተማራችሁ ስለሆነ ምድርን ለቃችሁ ጨረቃ ላይ ማርስ ላይ ከዚያም በላይ እንሂድ ብላችሁ፣ ቤታችሁንም እዚያ ልታደርጉ እየጣራችሁ ነው፡፡ መሰሎቻችሁ ለሽርሽር እየሄዱ እየመጡ ናቸው፡፡ ነገ ከዚያ ለመኖር የሰሩት መንኮራኩር በየጊዜው ይሄዳል ይመጣል፡፡ አባታችሁ ዲያብሎስ ከፈጣሪ በላይ ሊሆን አይደል እናንተስ የሱ ደቀ መዝሙሮች ከሱ ሃሳብ በምን ትለያላችሁ? ትጥራላችሁ ከንቱዎች ናችሁ፡፡ ከንቱ ትሆናላችሁ፡፡
ነገር ግን ወደ ሲኦል ወደ ጉድጓድም ጥልቅ ትወርዳለህ፣ የሚያዩህ ይመለከቱሃልና በእውኑ ያንቀጠቀጠ መንግስታትንም ያናወጠ አለሙን ባድማ ያደረገ ከተሞችንም ያፈረሰ ምርኮኞችንም ወደ ቤታቸው ያልሰደደ ሰው ይህ ነውን? ብለው ያስተውሉሃል፡፡ የአህዛብ ነገስታት ሁሉ በየቤታቸው በክብር አንቀላፍተዋል፡፡ አንተ ግን እንደተጠላ ቅርንጫፍ ከመቃብር ተጥልሀል፡፡ በሰይፍም የተወጉት ተገለውም ወደ ጉድጓድ ድንጋዬች የወረዱት ከድነውሃል፡፡ እንደተረገጠም ሬሳ ሆነሃል፡፡ ምድርህን አጥፍተሃልና ህዝብህንም ገድለሃል ከነርሱ ጋር ከመቃብር በአንድነት አትኖርም፡፡ /አትሆንም/ ፡፡ እንዳይነሱም ምድርን እንዳይወርሱ ስለአባቶቻቸው በደል ለልጆቹ ሞትን አዘጋጁላቸው፡፡ ትንቢት ኢሳያስ 14 15- 21 አባታችሁ ዲያቢሎስ የቀደመው እባብ መንግስታትን ሲያምስ ህዝብን ሲያስፈጅ በኒዩክለር ከተሞችን ያፈረሰ በጀት በመድፍ ሲቀጠቅጥ እናንተም ይህን ስታደርጉ ስታስፈጽሙ ኖራችሁ ነገር ግን ፍጸሜአችሁ መጠረግ ነው እንኳን እናንት ልጆቻችሁም አይኖሩም፡፡

የሰራዊት ጌታ እግዚአብሄር ይህን ይላል!!
የሰራዊት ጌታ በእነሱ ላይ እነሳለሁ ይላል፡፡ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሄር ከባቢሎን ስም ቅሬታን ዘርንና ትውልድንም እቆርጣለሁ ይላል እግዚአብሔር፡፡ የጃርት መኖሪያ የውሃ መቆሚያ አደርጋታለሁ በጥፋትም መጥረጊያ እጠርጋታለሁ ይላል፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፡፡ ትንቢት ኢሳያስ 14 22 – 23 እንግዲህ የናንተ ጥፋት ከላይ በተገለጸው መልኩ ነው፡፡ ትጠረጋላችሁ፣ ትወድማላችሁ፣ ትቢያ ትሆናላችሁ፡፡ ይህ ይፈጸማል፣ ይህም ይከናወናል፣ ጌታም የታመነ ነው ያደርገዋል፡፡ ስለዘመናችን ባቢሎን /አሜሪካ/ ከሷም ጋር ስለሚነግዱ አብረው ስለሚያመነዝሩ ሁሉ ከዚህ የሚከተለው የጌታ ፍርድ ይፈጸማል፡፡ የሰራዊት ጌታ ይህን ይላል!
በብርቱም ድምጽ ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች የርኩሳን መናፍስትም ሁሉ መጠጊያ የርኩሳንና የተጠሉም ወፎች ሁሉ መጠጊያ ሆነች፡፡ አህዛብ ሁሉ ከዝሙትዋ ቁጣ ወይን ጠጅ የተነሳ ወድቀዋልና! የምድርም ነገስታት ከእርሷ ጋር ሲሴስኑ የምድርም ነጋዴዎች ከቅምጥልነትዋ ሃይል የተነሳ ባለጠጋዎች ሆኑ ብሎ ጮኸ፡፡ የዮሃንስ ራእይ 18 2 – 4 ዛሬ ከአሜሪካ ጋር የማይነግድ የለም፡፡ ከእንግሊዝ የማይነግድ የለም፡፡ የአረብ ነገስታት፣ የአውሮፓ ነገስታት፣ የኤሺያ፣ የላቲን አሜሪካ እናም አፍሪካ ነገስታት ሁሉም ከታላቋ በባሎን /አሜሪካ/ የሚነግዱ ናቸው፡፡ ዛሬ ከሷ ነግደው የበለጸጉ ናቸው፡፡ እንኳንና ነገስታት ግለሰቦችም አሜሪካ አውሮፖ ሄደው መኖር፣ መነገድ እንደ ክብር፣ ገነት እንደመግባት ይቆጥሩታል፡፡
ምክንያቱም ገንዘቡም አለ፣ ልቅ የሆነው ምንዝርና አለ፡፡ የዲያቢሎስ ዘመን የእባቡ ጊዜ ስለሆነ ሁሉንም በእጅ በደጅ አድርጎላቸዋልና! ስለዚህ ዘወትር ሩጫው ወደእዚያ ነው ወዬላችሁ! ትጠረጋላችሁ! አታመልጡም፡፡

እነሆ ይህንን ይላል ጌታ እግዚአብሄር ስሙ ሁሉን ቻይ ኤልሻዳይ አምላክ !!
ከሰማይም ሌላ ድምጽ ሰማሁ፣ እንዲህ ሲል፡፡ ህዝቤ ሆይ በሃጢያትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርስዋ ዘንድ ውጡ ! ሃጢያትዋ እስከ ሰማይ ድረስ ደርሶአልና ! እግዚአብሄር አመጽዋን አሰበ፡፡ እስዋ እንደ ሰጠች መጠን ብድራት መልሱላት፣ እንደስራዋም ሁለት እጥፍ ደርቡላት፡፡ በቀላቀለችው ጽዋ ሁለት እጥፍ አድርጋችሁ ቀላቅሉባት፡፡ ራስዋን እንደአከበረችና እንደተቀማጠለች ልክ ስቃይና ሃዘን ስጥዋት፡፡ በልብዋ ንግስት ሆኘ እቀመጣለሁ ባልቴትም አልሆንም ሃዘንም ከቶ አላይም ስላለች፣ ስለዚህ በአንድ ቀን ሞትና ሃዘን ራብም የሆኑ መቅሰፍቶች ይመጣሉ፡፡ በእሳትም ትቃጠላለች የሚፈርድባት እግዚአብሄር ብርቱ ነውና!
ከእርሷ ጋር የሴስኑና የተቀማጠሉና የምድር ነገስታት፣ የመቃጠልዋን ጢስ ሲያዩ፣ ስለእርስዋ ዋይ ዋይ እያሉ ያለቅሳሉ፡፡ ስቃይዋን ከመፍራት የተነሳ በሩቅ ቆመው አንቺ ታላቂቷ ከተማ ብርቱይቱ ከተማ ባቢሎን ወዬልሽ በአንድ ሰአት ፍርድሽ ደርሶአልና እያሉ ይናገራሉ፡፡
የመርከባችን ጭነት ከእንግዲህ የሚገዛ የለምና የምድር ነጋዴዎች ያለቅሱላታል፡፡ ያዘኑላትማል፡፡ ጭነትም ወርቅና የከበረ ድንጋይ እንቁም ቀጭንም ተልባ እግር፣ ቀይም ሃርም፣ ሃምራዊ ልብስ የሚሸትም እንጨት ሁሉ፣ ከዝሆን ጥርስ የተሰራ እቃም ሁሉ እጅግም ከከበረ እንጨት ከናስም ከብረት ከእብነ በረድም የተሰራ እቃ ሁሉ ቀረፋም ቅመምም የሚቃጠልም ሽቱ ቅባትም እጣንም የወይን ጠጅም ዘይትም የተለሰቀ ዱቄትም ስንዴም ከብትም በግም ፈረስም ሰረገላም ባሪያዎችም የሰዎችም ነፍሳት ነፍስሽ የጎመጀችው ፍሬ ከአቺ ዘንድ አልፏል፡፡ የሚቃጠልና የሚያጌጥም ነገር ሁሉ ጠፍቶብሻል፡፡ ስዎችም ከእንግዲህ ወዲህ አያገኙአቸውም፡፡ እነዚህን የነገዱ በእርሷም ባለጠጋዎች የሆኑት እያለቀሱና እያዘኑ በቀጭን ተልባ እግርና በቀይ ሃምራዊም ልብስ ለተጎናጸፈች
በወርቅና በከበረ ድንጋይም በእንቁም ለተሸለመች ለታላቂቷ ከተማ ወዩላት፡፡ ይህን የሚያህል ታላቅ ባለጠግነት በአንድ ሰአት ጠፍቶአልና እያሉ ስቃይዋን ከመፍራት የተነሳ በሩቅ ይቆማሉ፡፡ የመርከቡም መሪ ሁሉ በመርከብም ወደማናቸውም ስፍራ የሚሄድ ሁሉ መርከበኞችም ከባህርም የሚጠቀሙ ሁሉ በሩቅ ቆሙ፡፡ የመቃጠልዋን ጢስ ባዩ ጊዜ ታላቂቱን ከተማ የምትመስላት ምን ከተማ ነበረች? እያሉ ጮሁ በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነስንሰው እያለቀሱና እያዘኑ በባህር መርከቦች ያሉአቸውን ሁሉ፣ ከባለጠግነትዋ የተነሳ ባለጠጋዎች ላደረገች ለታላቂቷ ከተማ ወዮላት ! ወዮላት ! አንድ ሰአት ጠፍታለችና እያሉ ጮሁ፡፡ ሰማይ ሆይ ! ቅዱሳን ነቢያት ሃወርያትም ሆይ ! በእርስዋ ላይ ደስ ይበላችሁ እግዚአብሄር ፈርዶላችኋልና !!

አንድም ብርቱ መልአክ ትልቁን ወፍጮ የሚመስልን ድንጋይ አንሰቶ ወደ ባህረ ወረወረው፡፡ እንዲህ ሲል ታላቂቱ ከተማ ባቢሎን አንዲህ ተገፍታ ትወድቃለች ከእንግዲህም ወዲህ ከቶ አትገኝም፡፡ በገና የሚመቱና የሚዘምሩም ድምጽ እምቢልታና መለከትንም የሚነፉ ድምጽ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይገኝም፡፡ የወፍጮ ድምጽም ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፡፡ የመብራትም ብርሃን ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይበራም፡፡ የሙሽራና የሙሽሪይቱም ድምጽ ከአንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፡፡ ነጋዴዎችሽ የምድር መኳንንት ነበሩና በአስማትሽም አህዛብ ሁሉ ስተዋልና፣ በእርሷም ውስጥ
የነቢያትና የቅዱሳን ደም በምድርም የታረዱ ሁሉ ደም ተገኘባት፡፡ የዮሐንስ ራእይ 18 4 – 24 እንግዲህ ስም አድምጡ ! ታላቂቱ ባቢሎን /አሜሪካ/ እንዲሁም ልጆችሽ እንግሊዝ፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ካናዳ፣ስፔን፣ደች፣
ፖርቹጋል፣ ጣሊያን፣ ዴንማርክ፣ አየርላንድ፣ ኦስትራያ፣ አውስትራሊያ፣ ሜክሲኮ፣ ራሺያ፣ ጃፖን፣ ቻይና፣ ቬትናም፣ ህንድ፣ ሲንጋፖር፣ እስራኤል፣ እንዶንዢያ፣ሊቢያ፣ ኮርያዎች፣ ኩባ፣ ኢራን፣ ሶሪያ፣ ሳውዲ አረቢያ፣ ቤልጂየም፣ ስዊድን፣ ኖርዌይ ፊንላንድ፣ ከታር ኤሜሬትስ፣ ኩዌት ግብጽ፣ አልጀሪያ ናይጀሪያ፣ ደቡብ አፈሪካ ብራዚል፣ ቺሊ አርጀንቲና፣ ሌሎችም አናሳ መንግስታት ሁሉ የተሰናዳላችሁን ጽዋ ትጠጣላችሁ፡፡
ስልጣኔአችሁ ክብራችሁ፣ ሃብታችሁ ሁሉ ይጠፋል፡፡ የናንተ ንግስት አሜሪካ ጥፋት የታላላቅ ወዳጆችዋ መንግስታት ጥፋት ጢሱ ሰማይ ይወጣል፡፡ ትቃጠላላችሁ ትቢያም ትሆናላችሁ፡፡ አሻራችሁ ይጠፋል፡፡ መብራታችሁ ፋብሪካችሁ፣ ውብ ከተማችሁ፣ ጌጣችሁ ሃብታችሁ፣ ብራችሁ ምንዝር መፈጸሚያችሁ፣ ዘራችሁ ሁሉ ይጠረጋል፡፡ ትቢያም ይሆናል፡፡ አውሬ ይዋለድበታል፡፡ እንደ ኤፍራጥስ እንደ ግብጽ ስለጣኔ ምልከት እንኳ አየቀርላችሁም፡፡ የቀደመው እባብ አባታችሁ አያድናችሁም ጠበቃ የላችሁም፣ የናቃችሁት በስሙ የተላገዳችሁበት ጌታ፣ የሰደባችሁት እግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስ በእሳት መጥረጊያ ይጠርጋችኋል፡፡ ወዴት
ትሸሸጋላችሁ? ወዴትስ ትሸሻላችሁ? በሁሉም ስፍራ ጥፋታችሁ ውድመታችሁ ይከተላችኋል፡፡ እናንተ ያፈረሳችኋቸው፣ እናንተ ያጠፋችኋቸው, ድሆች ጎስቋሎች ረሃብተኞች ይወርሷችኋል፡፡ የነሱ ከፍታ ይሆናል፡፡ የናንተ ውርደትም ይቀድማል፡፡ ከሃዲዎች የእባብ ልጆች፣ ጨካኞች፣ ትእቢተኞች፣ በጥበባችሁ የተመካችሁ፣ ይህ ሁሉ መታመኛችሁ ይጥፋል፡፡ እንደ ጢስ ይተናል፡፡ የዘር ቅሬታችሁ ይነቀላል፡፡ ማንም አያስጥላችሁም፡፡ በስራችሁ በሃጢያታችሁ ብዛት ሶዶምና ጎመራን ሰባት እጥፍ በልጣችኋል፡፡ ሶዶምን የበላው እሳት ሰባት እጥፍ ሆኖ ይበላችኋል፡፡ በሰራችሁት መሳሪያም ትተላለቃላችሁ፡፡

ጥፋታችሁን ውደመታችሁን፣ መጠረጋችሁን፣ ደካሞች፣ የዋሆች፣ ጻድቃን የእግዚአብሄር ህዝቦች በመልካም ጥበቃ በጥሩ ስፍራ ሆነው፤ የፈጣሪያችውን ፍርድ /ቅን ፍርድ/ አፈጻጸም ያያሉ ይደ.. ተዘልለውም ይኖራሉ፡፡ ማን ይነካቸዋል? ጠባቂያቸው የታመነው የማያንቀላፋው የሰራዊት ጌታ እግዚአብሄር ነውና ! በጥበባችሁ ትምክህት ስላደረባችሁ ፈጣሪ የለም ትላላችሁ እድሜን የሚለካው የሚወስነው ፈጣሪ መሆኑ ቀርቶ ስለመሬት
ስለሰው ስለልዩ ልዩ ፍጥረቶች ቅሬተ አጽም እየሰበሰባችሁ ሚሊዩን ሸተ.. እያላችሁ እድሜ ትተምናላችሁ፡፡ ጥበባችሁ አስከራችሁ፤ ፍፁምም አሳታችሁ ያልተገደበ ምገባራችሁ ናላችሁን አዞረዉ፡፡ ስለዚህም በትእቢት ሰከራችሁ ፡፡ ድሃ መንግስታትና ህዝባቸው ለናንተ አገልጋይ ሆኑ፡፡ ለናንተ የሚመቻችሁን ገዢ በህዘብ ላይ ጭናችሁ፤ በመከራና በረሃብ ሰንሰለት እንዲሰቃይ ታደርጋላችሁ ሃብታቸውንም ትዘርፋላችሁ ታዳጊ የላቸውም ትላላችሁ፡፡ ምድር በየእለቱ የምትፈጽሙትን ክፉ ስራ መሸከም አልቻለችም፡፡ ስለዚህ ፍርዳችሁ ፈጠነ፡፡ እነሆ በአጭር ጊዜ ይመጣል ያወድማል፡፡ የት ይመለጣል የፈጣሪያችን ፍርድ ይፈፀማል፡፡ ቅን ፍርዱ ይገለፃል ፡በቅርቡም ይታያል መጥፋታችሁና ፍርዳችሁም በየደጃችሁ ቆሞዋል ፡፡

አይ ባቢሎን ! (አሜሪካ) አይ አውሮፓ! አይ ኤሽያ ! አይ አፍሪካ ! ወየው ላቲን አሜሪካ ! አይ አውስትራሊያ ! አይ አለም ወዴት ነው መድብቂያው? ተመዝናችሁ ቀለላችሁ (ማኔ ተቄል ፋሪ) ስለዚህም በእሳት ወንፊት ትበጠራላችሁ፡፡ ከውስጣችሁ ንፁሃን ከክፉ ስራችሁ የራቁ ዘወትር በናንተ ሃጢያትና ክፋት ነፍሳቸውን ያስጨነቁ ይድናሉ፡፡ ያመልጣሉ፡፡ የሰራዊት ጌታ ይህንን ያደርጋል ይፈፅመዋል፡፡

/ በሁለተኛው መልእክት ለተጠቀሳችሁ ! ጆሮአችሁን ከፍታችሁ አድምጡ ! በዚህ መልእክት ውስጥ የተጠቀሳችሁ የተለያየ እምነትን ይዛችሁ ይህንንም እምነታችሁን ለምታርም ይመለከታል፡፡

1/
በክርስትና ስም ላላችሁ ካቶሊካውያንና መሪዎችዋ፤ ፕሮቴስታንታውያንና መሪዎችዋ፤ ኦርቶዶክሳውያንና መሪዎችዋ፡፡ እንዲሁም ሌሎች የተለያየ የክርስትና እምነት ለምትክተሉ አናሳ በየሀገሩ ተከልላችሁ ያላችሁ ክርስቲያኖችና መሪዎችዋ !!
2/
ምድሪቱን በስፋት ለሸፈናችሁ የእስልምና እምነት ተከታዮችና መሪዎችዋ በሙሉ!!
3/
ኮንፊሺያን፤ ቡዲሂዝም፤ ሂንዱይዝም እና ሌሎችም በምስራቅ ኤሽያ በስፋት የተንሰራፋችሁ እምነት ተቋማትና መሪዎችዋ!

የሰራዊት ጌታ ያለ የነበረ የሚኖር ሁሉን ቻይ ሁሉን የሚያሳልፍ ሁሉንም በእጁ የያዘ ጌታ ይህን ይላችኋል !!
እነሆ እግዚአብሄር መአቱን በቁጣ ዘለፋውንም በእሳት ነበልባል ይመልስ ዘንድ ከእሳት ጋር ይመጣል፡፡ ሰረገሎቹም እንደ አውሎንፋስ ይሆናሉ እግዚአብሄርም በስጋ ለባሽ ሁሉ ላይ በእሳትና በሰይፍ ይፈርዳል፡፡ በእግዚአብሄር ተወግተው የሞቱት ይበዛሉ፡፡ ትንቢተ ኢሳያስ 66 15 - 16
ጌታ እግዚአብሄር ስራችሁን መዘነ ክፋታችሁ ምድርን ሸፈነ የእምነት መሪ ነን ትላላችሁ ስራችሁ የአባታችሁ የዲያቢሎስ ሆነ፡፡ ፈጽማችሁም የመዳንን መንገድ አጠፋችሁ፡፡ ክፉዎችን አመንዝራዎችን ነፍሰ ገዳዮችን አፀናችሁ፡፡ ስለዚህ የሃጢያታችሁ ብዛት ለአለም ሁሉ ተረፈ፡፡ ጌታ በእሳት ሰይፍ ይጠርጋችኋል፡፡

ስለዚህ እረኞች ሆይ የእግዚአብሄርን ቃል ስሙ ! ጌታ እግዚአብሄር እንዲህ ይላል እኔ ህያው ነኝና እረኛ ስለሌለ እረኞቼም በጎቼን ስላልፈለጉ፤ እረኞችም እራሳቸውን እንጂ በጎቼን ስላላሰማሩ በጎቼ ንጥቂያ ሆነዋልና ! በጎቼም ለምድር አራዊት ሁሉ መብል ሆነዋልና !

ስለዚህ እረኞች ሆይ ! የእግዚአብሄርን ቃል ስሙ ጌታ እግዚአብሄር እንዲህ ይላል ! እነሆ በእረኞች ላይ፤ ነኝ በጎቼንም ከእጃቸው እፈልጋለሁ በጎቼንም ከማሰማራት አስተዋቸዋለው፡፡ ትንቢተ እስቅኤል 34 7 - 10
በክርስትና እምነት ስም ተሰማርታችሁ እረኛና መሪ ሆናችሁ ጌታን የምታገለግሉ መስላችሁ ፓትሪያርክ፣ ጳጳስ፣ ቄስ፣ ካህን፣ ዲያቆን፣ ዘማሪ የሚል ማእረግ ይዛችሁ ወደ እራሳችሁ ስምሪትና ንግድ የወረዳችሁ ወዮላችሁ ! ይህ ሁሉ ክብራችሁ ይጠፋል፡፡ እናንተም የሰበሰባችሁት የአመፃ ፍሬ ሁሉ ይጠፋል፡፡

እውነትን በአመፃ በሚከለክሉ ሰዎች በሃጢአተኝነታቸውና በአመፃቻው ሁሉ ላይ የእግዚአብሄር ቁጣ ከሰማይ ይገለፃልና፡፡ እግዚአብሄር ስለ ገለጠላቸው ስለ እግዚአብሄር ሊታወቅ የሚቻለው በእነርሱ ዘንድ ግልጥ ነውና የማይታየው ባህርይ እርሱም የዘላለም ሐይሉ ደግሞም አምላክነቱን፤ ከአለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሰሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና ስለዚህም እግዚአብሄርን እያወቁ እንደ እግዚአብሄር የክርስትና እምነት መሪዎች ሁሉን ታውቁ ዘንድ ጌታ ሁሉን አሳውቆአችኋል፡፡ ግን ጥበበኞች ነን ትላላችሁ ደንቆሮ መሆናችሁ ተግባራችሁ ይገልፃል፡፡

በአለም ላይ ብዙ የተዋቡ ጌጣቸው ስእላቸው የህንፃ ጥበባቸው ድንቅ የሆኑ ካቴድራሎች የእምነት ቤቶች ሃብት ክብር አላችሁ ትነግዱማላችሁ እጅግ ግዙፍ ኮሌጅ ዩንቨርስቲ አላችሁ በስነ መለኮት ትምህርት በዶክተር በዲግሪ በመሳሰለው ማእረግ መርቃችሁ ባለእውቀቶች ታወጣላችሁ እጅግ ትላልቅ የመፅኃፍት ቤት በተ መዘክር ቤተ ምርምር አሉዋችሁ ትመረምራላችሁ ግን ምን ዋጋ አለው ከንቱዎች ናችሁ፡፡

ዳንኤል ሆይ አንተ ግን እስከ ፍጻሜ ድረስ /ዘመን ድረስ/ ቃሉን ዝጋ መጽሃፉንም አትም ብዙ ሰዎች ይመረምራሉ እውቀትም ይበዛል፡፡ ትንቢተ ዳንኤል 12 4 ከላይ በጌታ ቃል እንደተገለጸው፣ ምርምር እውቀት በዝቶአል፤ የእግዚአብሄር ሚስጥር ግን በእውቀት ብዛትና በምርምር ስለማይገኝ ተዘግቶአል ታትሞአል፡፡ በየዋህነት፣ በቅንነት፣ በእውነትና በመንፈስ ለሚያመልኩ ብቻ ይገለጻል፡፡ የዘመናችን እባቦች ግን የእግዚአብሄርን እውነት በውሸት ትለውጣላችሁ በአሁኑ ወቅት አለም በሙሉ በቀደመው እባብ ተግባር ተሸፍናለች፡፡ በናንተ ውስጥ፣ በቤተ ክርስቲያንም ፍጹም የዲያቢሎስ ስራ ነገሶአል፡፡ ትነግዳላችሁ፣ ግድረ ሶዶምነትን ታስፋፋላችሁ፣ ታደርጋላችሁ፣ የከፉ መሪዎችን፣ ገዢዎችን መረዎችን ታገለግላላችሁ፣ ታበረታታላችሁ፡፡ ሰለሃብታችሁ
ሁሉንም ክፉ ስራ ትሰራላችሁ፡፡ ስለዚህም እግዚአብሄር በእሳት ሊጎበኛችሁ ወሰነ፡፡ ወዴትም አታመልጡም ሞት ተፈርዶባችኋልና፡፡

ሙስሊም፣ ቡዲዝም፣ ሂንዱይዝም፣ ኮንፊሺያን እንዲሁም ሌሎች መሰል ተቋሞች በተራ ቁጥር፡ 2 – 4 የተጠቀሳችሁ በሙሉ ተረታችሁ ይቀራል፣ ይሻራል፡፡ የቅዱሳንን የነቢያትን ደም በከንቱ ለውሸት ትምህርታችሁ ስትሉ ገድለዋችኋል፣ እየገደላችሁም ነው፡፡ ሁሉም ተምክህታችሁ የገነባችሁት ሁሉ ትቢያ ይሆናል፡፡ የመቆሚያ ስፍራ አታገኙም፡፡ ድንገት ወደ ሲኦል ትወርዳላችሁ፡፡ ከምድር ፊት ፍጹም አለቅሪት ትጠፋላችሁ፡፡
ይህ ሩቅ አይደለም ፍርዳችሁ ወጥቶአል፡፡ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሄር የጦር እቃውን ለብሶአል፡፡ ቁጣውም
እጅግ ጢሶአል፡፡ ምድር ወየው በይ ! የተበተበሽ እባብ፣ ጊንጥ፣ ዘንዶ ሁሉ በእሳት ባህር ይዋጣል፤ ይህ እጅግ በቅርብ ይሆናል፡፡ ይፈጸማል፡፡ የሰራዊት ጌታ በቃሉ የታመነ ነው፡፡ ቃሉ ከሚጠፋ ምድርና ሰማይ ቢያልፍ ይቀላልና፡፡

አሜን የጌታ ቅን ፍርድ ይገለጥ ስሙም የተመሰገነ ይሁን !
/ በሶስተኛው መልእክት ለተጠቀሳችሁ የእግዚአብሄር ሕዝቦች ይመለከታል፡፡
በሰራዊት ጌታ ታምናችሁ፤ በጌታ ጸጋና ማዳን ጸንታችሁ፤ በእግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስ አጽናኝነት የወረደባችሁንመከራና ጭንቅ፣ እስራት ውርደትን፣ መራብን ማጣትን፣ እንግልትን ሞትን ሁሉ ታግሳችሁ በጌታ ቅን ፍርድ መዘግየት ምክንያት ለደከማችሁ ተሰፋ ቆርጣችሁ፣ ፊታችሁን ላዞራችሁ፣ ሁሉ ልዑል እግዚአብሄር እንባችሁን ሊያብስ ጭንቀታችሁን ሊያጠፋ ተነሳ ! አይዞአችሁ ጽኑ !!
የሰላምን ቃል ኪዳን ከነእርሱ ጋር አደርጋለሁ፣ ክፉዎችንም አራዊት ከምድር አጠፋለሁ፡፡ ተዘልለውም በምድረ
በዳ ይኖራሉ፣ በዱርም ውስጥ ይተኛሉ፡፡ እነርሱንና በኮረብታዬ ዙሪያ ያሉትን ስፍራዎች ለበረከት አደርጋቸዋለሁ፡፡ ዝናቡንም በጊዜው አወርዳለሁ፡፡ የበረከት ዝናብ ይሆናል፡፡ የምድረ በዳም ዛፍ ፍሬውንም ይሰጣል፡፡ ምድርም ቡቃያዋን ትሰጣለች በምድራቸውም ተዘልለው ይኖራሉ፡፡ የቀንበራቸውንም ማነቆ በሰበሩ ጊዜ ከሚገዟቸውም እጅ ባዳንኳቸውም ጊዜ እኔ እግዚአብሄር እንደሁንሁ ያውቃሉ፡፡ እንግዲህም ለአሕዛብ ንጥቂያ አይሆኑም፣ የምድርም አራውት አይበሉአቸውም፡፡ ተዘልለውም ይቀመጣሉ፡፡ የሚያስፈራቸውም የለም፡፡ የዝናን ተክል አቆምላቸዋለሁ፡፡ እንግዲህም ከራብ የተነሳ በምድር አያልቁም፡፡ የአሕዛብንም ስድብ ከእንግዲህ ወዲህ አይሸከሙም፡፡ እኔ እግዚአብሄር አምላካቸው ከእነርሱም ጋር እንዳለሁ እነርሱም የእስራኤል ቤት
ሕዝቤ እንደሆኑ ያውቃሉ፣ ይላል ጌታ እግዚአብሄር፡፡ እናንተም በጎቼ የማሰማሪያም በጎች ሰዎች ናችሁ፡፡ እኔም አምላካችሁ ነኝ ይላል ጌታ እግዚአብሄር፡፡ ትንቢተ ሕዝቅኤል 34 25 – 31 ይህ ቃል በመላው ዓለም
ለእግዚአብሄር ላደራችሁ ሁሉ ይመለከታል፡፡ የቅዱሳን መላእክትን ተራዳኢነት፣ የእመቤታችንን እናትነትና ብጽእትነት፣ አማላጅነት አምናችሁ፣ አክብራችሁ ለያዛችሁ ይመለከታል፡፡ ጌታ በኮረብታው ዙሪያ፣ በኢትዮጵያና ዙሪያዋን ባሉ ተራሮች የሚተክለው ብርሃን የሁላችሁም ቅኖች መሰብሰቢያ ይሆናል፡፡ ልዑል እግዚአብሄር ሀዘናችሁን ወደ ደስታ ይለውጠዋል፡፡ የታመነው ጌታ ለልጆቹ የሚነፍገው የለም፡፡ ይህም ደርሷል፡፡ በቅርቡም ይሆናል፡፡ ራሳችሁን አጽዱ፣ ጽኑ፣ አይዟአችሁ አትፍሩ፣ አትጨነቁ፣ በቁጣው እሳት የምትጎበኘው ምድር ከናንተ አንዲቷን ጸጉራችሁን እንኳን አይነካም፡፡ ባባታችሁ፣ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅን ፍርድም ትደነቃላችሁ፡፡

እግዚእብሄር አብ፣ እግዚአብሄር ወልድ፣ እግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስ፣ አሃዱ አምላክ ስሙ ይባራክ አሜን !!

/ ሌላው መልእክቴ ኢትዮጵያንና የህዝቦቿን መጻኢ ሁኔታና እድል ይመለከታል፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ ከፈጣሪው በመሸሽ ትእዛዙንም በመናቅ፣ በእንግዳ ባህልና በእንግዳ ትምህርት በመወሰን በከፍተኛ ደረጃ ፈጣሪውን በመበደሉ እነሆ ላልተቋረጠ መከራ ተዳርጎ ይገኛል፡፡ ከፈጣሪው ማግኘት የሚገባውን ምህረትና እርዳታ፣ ከአሜሪካና አውሮፓ ( ባቢሎናውያን ) ይፈልጋል፡፡ ይለምናል፡፡ ነገር ግን የተገኘ አንዳችም የለም፡፡ ምክንያቱም እነሱ እባቦች፣ የዲያብሎስ ልጆች እንጂ የፈጣሪ ወዳጆች አይደሉም፡፡ የሚያስፈጽሙትም
የአባታቸውን የዲያብሎስን ፈቃድ ነው፡፡ ዛሬ በኢትዮጵያ የነገሰው ዲያብሎስ ነው፡፡ የሚሰራውም ለዚሁ ለቀደመው እባብ ነው፡፡ ይህ የሚወገደው በፈጣሪ ኃይል ነው፡፡ የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ
የምድያም አገር መጋረጃዎች ሲንቀጠቀጡ አየሁ፡፡ ትንቢተ ዕንባቆም 3 7 አዎ ለረጅም ጊዜ አገራችን እየተጨነቀች ነው፡፡ ይህም ለስራ ነው፣ እየሰራንም ላለነው ጥፋት የመጣ ቅጣት ነው፡፡ ሌብነት፣ ምንዝርና፣ሃሰት፣ ክፋት፣ በሃሰት መመስከር፣ግድያ፣ ዘረፋ፣ክህደት፣ ዘረኝነት፣ ጭካኔ ምን ስፍር ቁጥር አለው፡፡ይህ ደግሞ ህዝቦችም፣ ገዥዎችም የሚሰሩት የየእለቱ ተግባር ነው፡፡ በመሆኑም አሁን እየታየ ያለው መከራ እየወረደ ነው፡፡
ይሁንና ጌታ ይህን እንዲያደርግ ልታውቁ ይገባል፡፡

ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ የሚማልዱኝ የተበተኑት ሴቶች ልጆቼ ቁርባኔን ያመጡልኛል፡፡ በዚያን ጊዜ አትታበዩ
የሚፎክሩትን ከመካከልሽ አወጣለሁና፤ አንቺም በቅዱስ ተራራዬ ዳግመኛ አትኮሪምና በዚያ ቀን በኔ ተላልፈሽ በሰራሽው ስራ ሁሉ አታፍሪም፡፡ በመካከልሽም የዋህና ትሁት ሕዝብን አስቀራለሁ፡፡ በእግዚአብሄር ስም ይታመናሉ፡፡ የእግዚአብሄር ቅሬታ ሃጢአትን አይሰሩም፣ ሃሰትንም አይናገሩም፣ በአፋቸው ውስጥ ተንኮለኛ ምላስ አይገኝም፡፡ እነርሱም ይሰማራሉ፣ ይመሰገኑማል፣ የሚያስፈራቸው የለም፡፡ ትንቢተ ሶፎኒያስ 3 10 – 13 ጽዮን ሆይ አትፍሪ ! እጆችሽም አይዛሉ፤ አምለክሽ እግዚአብሄር በመካከልሽ ታዳጊ ኃይል ነው፡፡ በደስታ ባንቺም ደስ ይለወል፡፡ በፍቅሩም ያርፋል፡፡ በእልልታም ባንቺ ደስ ይለዋል፡፡ ይባላል፡፡ ከጉባኤው ርቀው የሚያዝኑትን ከአንቺም የሆኑትን እሰበስባለሁ፡፤ ስድብ እንደ ሸክም ከብዶአቸው ነበር፤ በዚያ ዘመን እነሆ ባስጨነቁሽ ሁሉ ላይ አደርግባቸዋለሁ፡፡ አንካሳይቱንም አድናለሁ፤ የተጣለችውንም እሰበስባታለሁ፡፡ ባፈሩበትም ምድር ሁሉ ላይ ለምስጋና ለከበረ ስም አደርጋቸዋለሁ፡፡ በዚያ ዘመን አስገባቸዋለሁ፡፡ በዚ ዘመን እሰበስባቸዋለሁ፤ ምርኮአችሁንም በዓይናችሁ ፊት በመለስሁ ጊዜ በምድር አህዛብ ሁሉ መካከል ለከበረ
ስምና ለምስጋና አደርጋቸዋለሁ ይላል እግዚአብሄር፡፡ ትንቢተ ሶፎኒያስ 3 16 – 20 ይህ ከላይ የሰፈረው የጌታ ቃል ለኢትዮጵያ ሕዝብ የተነገረ ተስፋ በመሆኑ እነሆ በቅርብ ጊዜ መፈጸም የሚጀምር ነው፡፡ ክፉዎች ሁሉ፣ ጠማሞች ሁሉ፣ ሲወገዱ ጨካኞች ሁሉ፣ ዘረኞች ሁሉ፣ አመንዝራዎች፣ ጨካኝ ገዥዎች፣ ሁሉ ይጠረጋሉ፡፡
ጌታም በምድሪቱ ( በኢትዮጵያ ) ይነግሳል፡፡ ስለዚህ የኢትዮጵያ ህዝብ በፈጣሪው ብቻ ሊታመን ይገባዋል፡፡ በነጭ ገዥዎችና በባህላቸው በሃብታቸው፣ በእውቀታቸው መታመንን ፍጹም ከልቡ አውጥቶ መጣል አለበት፡፡ እነሱ! ነጭ ገዥዎች ምን እንደተዘጋጀላቸው ቀደም ብዬ በገለጽኩት ሁለት መልእክቶች ውስጥ ተገልጦአል፡፡
በኢትዮጵያ ምድር ያሉ የሃይማኖት መሪዎች የሰሩት ክፉ ስራም ይጎበኛል፡፡ በእሳት ይፈተሻል፡፡ የስራቸውም ዋጋ ይሰጣቸዋል፡፡

የሃይማኖት አባቶች ሳይሆኑ የሃይማኖት አጥፊዎች ሆነዋል፡፡ ጳጳስ፣ ካህን፣ዲያቆን፣ ቄስ መነኩሴ እነዚህ ሁሉ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይነግዳሉ፣ ያመነዝራሉ፣ የመንግስትን የፖለቲካ ስራ ይሰራሉ፣ ያታልላሉ፣ ሰዎችን ወደ ጨለማ ይነዳሉ፡፡ ወንጌል ጨብጠው ለሰው ልጆች የመዳንን መንገድ ማሳየት ሲገባቸው ወደ ጥፋት ወደ ክህደት ወደ ጨለማ ስራ ይመራሉ፡፡ ከሁሉም በላይ በእግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስ ላይ ያላግጣሉ፡፡ ስለዚህም በእሳት ይጠረጋሉ፡፡ እውነት የሚናገሩ ባህታዊያንን ያሳድዳሉ፡፡ ይገድላሉ፡፡

ቀጣፊዎች ስፍራና ቦታ ገንዘብ ይሰጣቸዋል፡፡ የሃሰትን ምልክት ይናገራሉ፡፡ እነዚህም ደፋሮች ከውሸት አለቆቻቸው ጋር ይጠረጋሉ፡፡ በአለም ያሉ የክርስትና እምነትን መሪነት ካባ ያጠለቁ ሁሉ የእግዚአብሄርን ቃል ሲቀንሱ ሲያሻሽሉ፣ ሲጨምሩ እንደኖሩ ይታወቃል፡፡ ሁሉም ለድፍረታቸው ዋጋቸውን ይቀበላሉ፡፡ አባቶቻችን የእምነት አርበኞች አጽንተው ተሰውተው፣ ያቆዩን ሰማኒያ አሃዱ መጽሃፍ ቅዱስ አለን፡፡ ነገር ግን ነጮች
የተቀነሰ መጽሐፋቸውን እንደ ትክክል በመቁጠር፤ ያልተቀነሰ ያልተጨመረ ሰማኒያ አሃዱን መጽሀፍ ‹‹ የኃይለ ሥላሴ መጽሐፍ ቅዱስ›› ነው ብለው እንደ ግለሰብ ድርሰት በመቁጠር ይተቻሉ፡፡ ይሳደባሉ፡፡

የኃይለ ሥለሴ መጽሐፍ ቅዱስ ነው ላሉት የግለሰቡ የጃንሆይ ሳይሆን የስላሴዎች፣ የአብ፣ የወልድ፣ የመንፈስ ቅዱስ፣ አሃዱ አምላክ ኃያል የሆነው መጽሐፍ ነው፡፡ ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ መቀነስ ያካሄዳችሁ ነጮች ፍርዳችሁን ታገኛላችሁ፡፡ በኢትዮጵያ ምድር የተለያየ መመሪያ ያለው የክርስትና እምነት ለምታራምዱ ሁሉ እንደ ስራችሁ እንደ ዘራችሁትም መጠን ታጭዳላችሁ፡፡ ከላይ በመልእክት 1 – 2 ለተጠቀሱት ሁሉ እንደተጠቀሰው እነሱ በሚመዘኑበት አካሄድ ትመዘናላችሁ፡፡ ዋጋውንም ትከፍላላችሁ፡፡ ከክርስትና እምነት ውጪ የሆነ እምነት ለምትከተሉ፤ በአለም ሁሉ ላሉ ቢጤዎቻችሁ እንደሚፈረድ ሁሉ ለናንተም ይኸው ፍርድ ይከተላችኋል፡፡
በኢትዮጵያ ላሉ ገዥዎችና አስተዳዳሪዎች ሁሉ ማንም እንደሚያውቃችሁ ከሃዲዎች ናችሁ፡፡ አታውቁትም እንጂ እምነታችሁ የአባታችሁ የዲየብሎስ ነው፡፡ ስለዚህ ለሰራችሁት ስራ ሁሉ፣ ላፈሰሳችሁት ደም፣ በብርቱ ትጠየቃላችሁ፡፡ በትእቢታችሁ፣ በክፋታችሁ፣ በተንኮላችሁ ሁሉ ትያዛላችሁ፣ ትመዘናላችሁ፣ ትዋረዳላችሁ፣ ወደ ትቢያም ትወርዳላችሁ፡፡ ከመሰረታችሁ ከነስራችሁ ከነልጆቻችሁ ትጠረጋላችሁ፡፡ በመልካሟ ኢትዮጵያ እንኳን እናንተ ልጆቻችሁም ቢጤዎቻችሁም አያዩ፡፡ ረጅም ታስባላችሁ ብዙ ታቅዳላችሁ፣ ዘር ከዘር ታጋጫላችሁ፣ የጦርነት እሳት ትጭራላችሁ፤ ግን ይህ ሁሉ የምታደርጉት እንኖራለን ብላችሁ ነው፡፡ አትኖሩም ፡፡ እጅግ በጣም ትንሽ ጊዜ ናት ያለቻችሁ፤ ትጠፋላችሁ፡፡ ባህረ ነጋሽ ( ኤርትራ ) በተመለከተ ብርቱ ቅጣትን፣ ብርቱም ጥፋትን ተቀብላ ወደ ነበረችበት ትመለሳለች፡፡ ከጥፋቷ የሚያመልጡ እድለኞች ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ምድር ላለው ጥፋት እጃቸውን ላስገቡ አገሮች ተጨማሪ በትርን ይቀምሳሉ፡፡ የሰራዊት ጌታ ይህን ይላል፤
አንተ የእባቦችን ራስ በውሃ ውስጥ ሰበርህ፤ አንተ የዘንዶውን ራሶች ቀጠቀጥህ፤ ለኢተዮጵያ ህዝቦችም ምግባቸውን ሰጠሃቸው የዳዊት መዝሙር 73 ( 74 ) 13 -14 ገዥዎችና መሰሎቻችሁ እባብ ማን ይመስላችኋል? ዘንዶውስ? አዎ እናንተ ናችሁ፡፡ ትቀጠቀጣላችሁ፣ ትሰበራላችሁ፣ ትጠፋላችሁ፡፡
ኢትዮጵያም የዋህ፣ ቅን፣ ትሁት ፈጣሪውን የሚወድድ ነጻ ይወጣል፡፡ ምግቡንም ያገኛል፡፡ ይህ ደግሞ ሳይርቅ በቅርቡ ይፈጸማል፡፡ በኢትዮጵያ በአዲስ የነጭ ባህል የተወሰዱ፣ ፍጹም የተበላሹ ሴቶች የሚበዙ ናቸው፡፡ ሱሪ ለብሰው ይሄዳሉ፣ ሃፍረተ ስጋቸውን ያሳያሉ፣ ምንዝርናን እንደ ስራ ይዘውታል፡፡ ፍጹም የዲያብሎስ ሰራተኞች ሆነዋል፡፡

ሴት የወንድ ልብስ አትልበስ ወንድም የሴት ልብስ አይልበስ ይህን የሚያደርግ በአምላክህ በእግዚአብሄር ዘንድ የተጠላ ነውና ኦሪት ዘዳግም 22 – 5 ይላል የጌታ ቃል፡፡ ወንዱም ያው ነው፤ አመንዛሪ፣ አታላይ፣ነጣቂ፣ ትእቢተኛ፣ ውሸታም፣ ስስታም፣ ሰካራም ጨካኝ ነው፡፡ እናንተም ከመጠረግ አታመልጡም፡፡ ይኸው ከላይ እንደተጠቀሰው በኢትዮጵያችን ይፈጸማል፡፡ አንዳችም የሚቀር ነገር የለም፡፡ ጌታ ከረጅም ጊዜ ትእግስት በኋላ የወሰነው ውሳኔ ስለሆነ፤ ተፈጻሚ ከመሆን በፍጹም አይቀርም፡፡

ማጠቃለያ
-
በመላው ዓለም ላላችሁ ገዥዎች፣ ነገስታቶች፣ የጦር መሪዎች፣ ዓለም አቀፍ ድርጅት መሪዎች ባለሃብቶች
-
በመላው ዓለም ላላችሁ የእምነት መሪዎች፣ ሰባኪዎችና ተከታዮች፤
-
በመላው ዓለም ላላችሁ ከሃዲዎች፣ ጸረ-ክርስቶስ፣ የተረት እምነት ተከታዮች፣ ጸረ ማርያም
-
ጸረ መላእክት አቋምና እምነት ላላችሁ
-
እግዚአብሄርንና ትዕዛዙን ንቃችሁ በራሳችሁ ተረት ተረት ለምትጓዙ በሙሉ በጥንቆላ በጣኦት ሥራ ላላችሁ እናንተንም ለሚከተሉዋችሁ
-
በሁላችሁም ላይ እነሆ የኤሊያስ አምላክ በእሳት ይፈርዳል፡፡ ጌታ ከአንድ ታማኙ ጋር ቆመ እንጂ፤ ከነአከአብ፤ ከነኤልዛቤል፤ ከነቡኤል ዘቡኤል፤ ካህናትና ሕዝቦች ጋር አልቆመም፡፡ በተጻራሪው ከታመነው አገልጋዩ እውነትን ብቻ ከሚያጸናው ባሪያው ኤሊያስ ጋር ቆመ፡፡ መልሱን በእሳት መለሰ ቁጥራቸው ቢበዛም ከሃዲዎች የእሳት እራት ሆኑ እንጂ ከጌታ ፍርድ አላመለጡም፡፡ እናንተም ቁጥራችሁ በሚሊዮን ቢቆጠር ዋጋ ያለውም ጌታ ከአንድ እውነተኛ ጋር በመቆም በሚጠሩ በቢሊዮን በእሳት ይፈርድባችኋል፤፤ ቁጥራችሁ በዝቶ ሃጢያትን እንደትክክል አንግሳችሁ አለምን ብትሸፍኑ፤ ጌታ ከጥቂት ወዳጆቹ አርነትን ያነግሳል፡፡ እናንተና አባታችሁ ዲያቢሎስ ከነሃጢያትና ወንጀላችሁ እንደገለባ በእሳት ትቃጠላላችሁ፡፡
ይህም ይሆናል የጌታ እግዚአብሄር ትእግስት አልቆ ተፈጽሞኣልና፡፡ የናንተም ወንጀልና ሀጢያት ተርፎ ፈሷልና፡፡ የግድ የአመፃን ዋጋ በህይወታችሁ ትከፍሉታላችሁ፡፡ የጌታም ቅን ፍርዱ ይገለጣል፤ በቅርቡ ይሆናል፡፡በየትኛውም የአለም ገጽታ ላይ ኑሩ የሰራችሁት እየሰራችሁት ያላችሁት አመጽ፤ ምንዝርና፤ ነፍስ ዝርፊያ፤ ውሸት፤ ትእቢት፤ ዘር ከዘር ማፋጀት፤ ዘረኝነት፤ ንቀት እንዲሁም ሴቶች ፍጹም ልቅ ታይቶ የማይታወቅ ምንዝርና፤ ጽንስ ማጥፋት፤ ወንዱም ግብረ ሶዶምነት ይህ ሁሉ ወንጀላችሁ አለምን ፍጹም በሃጢአት እንድትሰጥም አድርጓታል፡፡ ስለሆነም ፍጹም ተጠርጋችሁ በእሳት መጥረጊያ ትበተናላችሁ፡፡ ከትቢያ ትቀላላችሁ፡፡ ጌታ ይፈጽመዋል ታዩትማላችሁ፡፡ የእግዚአብሄር ሕዝቦች የትም ሆኑ የት ጌታ ደርሶላችሁ
የሰራዊት ጌታ ምክር ይድረሳችሁ፡፡ በአመጽ ሰፈር አትገኙ፤ ከክፉዎች ራቁ፤ በስራቸውም በሃሳባቸውም አትግቡ፡፡ከደም አፍሳሾች ጨካኞች፤ ትእቢተኞች፤ ውሸታሞች፤ አመንዛሪዎች፤ ሰካራሞች ራቁ፡፡ ፍፁም ራቁ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ዘወትር እንጸልያለን በማለት ጌታን ሰቅለው ቁስሉን ከሚወጉ ጋር መስዋእታችሁን አትቀላቅሉ፡፡….. የግላችሁን ጸሎት ጸልዩ፡፡ ዛሬ ሁሉም የእምነት ተቋሞችና መሪዎች ሕይወት ባራኪ ሳይሆኑ ሕየወት አጥፊ ናቸውና፡፡ በቤታችሁ እልፍኛችሁን ዝጉ፣ በእንባ፣ በፍጹም ልባችሁ፣ በፍጹም ሃሳባችሁ፣ ጸልዩ ስለቋንቋችሁ ልባችሁን የሚመረምር የአብርሃም አምላክ በእውነትና በመንፈስ፣ በተሰበረ ልብ፣ በእንባ ስትነግሩት ይሰማል ትራሳችሁን በእንባ አርሱት እንባችሁን ያብሳል፡፡ የታመነውን የሰራዊት ጌታ፣ ይህን የማንም ፍጥረት ሊመረምረው ሊያውቀው ፈጽሞ የማይቻለውን አለም በቅጽበት ይሁን ሲል የጸና እንዲሆን ያደረገ ፍጹም ይወዳችኋል፡፡ ዋጋችሁንም ይከፍላል፡፡ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሄር አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ ይህን ይላል፡፡ እስራኤል ሆይ ስማ! አምላካችን እግዚአብሄር አንድ አምላክ ( አንድ እግዚአብሄር ) ነው፡፡ አንተም እግዚአብሄር አምላክህን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹምም ነፍስህ፣ በፍጹም ሃይልህ ውደድ፡፡ እኔም ዛሬ አንተን የማዝዘውን ይህን ቃል በልብህ ያዝ፤ ለልጆችህም አስተምረው፣ በቤትህም ስትቀመጥ በመንገድም ስትሄድ፣ ስትተኛም፣ ስትነሳም ተጫወተው፡፡ በእጅህም ምልክት አድርገህ እሰረው፣ በአይኖችህም መካከል እንደ ክታብ ይሁንልህ፣ በቤትህም መቃኖች በደጃፎችህም በሮች ላይ ጻፈው፡፡ ኦሪት ዘዳግም 6 4 – 9
ሁሉን ቻይ ፈጣሪ የታመነ ነው፡፡ በሺ የተቆጠረ ዘመንን ታገሳችሁ፡፡ ደም ሲፈስ ወንጀል ሲሰራ ምን ውሸት ክፋት ተንኮል ትዕቢትን ስታነግሱ በግሳጼና በመለስተኛ አባታዊ ቅጣት አለፋችሁ፤ ሁሉን የሚችል አምላክ የነበረ ያለ የሚኖር ሁሉን የሚያሳልፍ ጌታ ሽንገላችሁን አየ፣ አለምን የዋጠውን ሃጢያታችሁን ምድሪቱም ጮኸች ትሸከማችሁ ዘንድ አቃታት፡፡ ልዑል የጦር ልብሱን ለበሰ፡፡ ለሺዎች ዓመታት ከእምቅድም አያቶቻችሁ ጀምሮ የፈተናችሁት ትዕግስቱ አለቀ፡፡ እንግዲህ ወዴት ይሆን መድረሻው? ሰውንም ፈጣሪንም በድላችኋል፤ ወዴት ነው መሸሸጊያው? እጅግ አስፈሪ ነው፡፡ እኔም እጅግ እየከበደኝ ተገድጄአለሁ፡፡ ስለሚሆነው ሳስብ
ፍጹም መድረሻ ይጠፋኛል፡፡ ይህንንስ ቁጣ ማን ይመልሰው ይሆን? አዎ ከፈጣሪ ፊት ወዴት መሰወር ይቻላል?
እንግዲህ መልእክቴ ይኸው ነው፡፡ ትሰሙት ዘንድ ግድ ነው፡፡ እንዳይሰማ ማድረግ ደግሞ ባይሳካም በራስ ላይ ትልቅ ጉዳት መጥራት ነው፡፡ ጨረስኩ! ሃሳባችሁም ልባችሁም ከመልእክቱ ላይ እንዲሆን እያሳሰብኩ እኔን ለመፈለግ አትድከሙ አታገኙኝም ካላችሁ እንኳ የምረዳችሁ የለኝምና እኔ አንድ ውዳቂ ድሃ ነኝ፣ አንድ ምስኪን ተላላኪ መልእክት አድራሽ በቃ ስራው የኸው ነው፡፡ እዚሁ ላይ ያበቃልና!!

አስጀምሮ ላስጨረሰኝ የአብርሃም የይስሃቅ የያእቆብም አምላክ፣ የነኤልያስ አምላክ፣ የሐዋሪያቶች አምላክ፣ ልዑል እግዚአብሄር አብ፣ እግዚአብሄር ወልድ፣ እግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ ስሙ ይባረክ፡፡
ቅን ፈራጅ ጌታ ከፍ ከፍ ይበል፡፡
አሜን!!
ማስታወሻ፡- - ማንኛውም ይህ ፍርድ አዘል መልእክት የደረሰው ሰው፣ ድርጅት፣ ተቋም፣ ባለስልጣን
ለሌላው የማስተላለፍ ግዴታ አለበት ይጠቀምበታል፤ ያተርፍበታል፡፡
-
ማንኛውም ግለሰብ፣ ተቋም፣ ድርጅት ወደፈለገው ቋንቋ መተርጎም ይችላል፤ ግን መቀነስ መጨመር፣ መለወጥ ክልክል ነው፡፡
-
ማንኛውም ግለሰብ፣ ተቋም፣ ድርጅት፣ መንግስት፣ ባለሰልጣን ይህን ፍርድ አዘል መልእክት ካሰናከለ፣ ካገደ
የሚገጥመው ቅጣት ለመጸጸት እንኳ እድል የማይሰጠው ይሆናል፡፡

ተጻፈ ቀን ኀዳር 7 ቀን 1998 ዓመተ ምህረት
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment