ታላቁ የኢትዮጵያ ትንሳኤ

✍ አየነው ገብረመስቀል

ባለ ተራዋ ኢትዮጵያ የአለም ቁንጮ ከመሆኗ በፊት በታሪክ ያለፉትን የአለም ሀያልን ሃገሮች ብናይ ምንም እንኳን ከእሱ በፊት ብዙ ታሪኮች ቢኖሩም ቀዳሚ ሆኖ የምናገኘው እስራኤላዊያን በባርነት የነበሩበትን ጊዜ ያውም የግብፅን ኃያልነት ነው፡፡”እስራኤልም በካም ምድር አደረ” ተብሎ እንደተነገረ የኃያላኖች ኃያል የተባሉ የእግዚያብሄር ህዝቦች እስራኤላውያን በጥበበ እግዚያብሄር በዮሴፍ ምክንያት ወደ ግብፅ መውረዳቸው ይታወሳል፡፡”እግዚያብሄርም ከዮሴፍ ጋር ተሸጠ” መፅሀፍ እኝህ የእግዚያብሄር ህዝቦች ኃያላን ሆነው ሳለ ለባርነት ቢዳረጉም ሊቀ ነቢያት ሙሴ በነበረበት በ1600 ዓ.ዓ የአለም ስልጣኔ በግብፃዉያን እጅ እንደወደቀና ከዚያም በእነ ክቡር ዳዊትና ልጁ ጠቢቡ ሶሎሞን ይኸውም በ1100 ዓ.ዓ አካባቢ ማለት ነው አለም ፊቱን ወደ እስራኤል አዞረ፡፡በመቀጠልም በ600ዓ.ዓ አካባቢ የአለም ስልጣኔና የሀይል ሚዛን ወደባቢሎን አመራ፡፡ከክርስቶስ ልደት ጀምሮ ደግሞ የሮማ ስልጣኔና ግዛት በአለም መድረክ ልዕለ ኃያል መሆነ ቻለች፡፡እንድህ እንድህ እያለ በአሁኑ ዘመን ደግሞ በዮሀንስ ራእይ ታላቋ ባቢሎን ተብሎ የተፃፈላት አሜሪካ (ፍፁም የምትጠፋ አሻራዋ እንኳን ለትውልድ የማይቀጥል) የአለም ፖሊስ ሆና በኢኮኖሚም አለምን አሸንፋ ገደልኳችሁ አጠፋኋችሁ እያለች እያስፈራራችን ትገኛለች፡፡     

በታአምረ ማሪያም ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅድስት እናቱ በመስታወት የተዘጋች አድርጎ አሜሪካን በስደቱ ዘመን እንዳሳያትን እሷም ልጇ ወዳጇን ይህች ሃገር ማን ነች ብላ በጠየቀችው ጊዜ “ይህች ሃገር ዛሬ የሰው ልጅ አይገባባትም ነገር ግን በ8ተኛው ሽህ ይህች ሃገር ትከፈታለች ፡፡ትልቅም ተሆናለች፡፡ሁሉም የአዳም ልጆች ወደዚች ሃገር ለመግባት የሚያደርጉት ጥረትና ትግል መንግስተ ሰማያት ለመግባት ከሚያደርጉት ትግል ይበልጣል፡፡በዚያን ዘመን ወደዚች ሃገር ለመግባት ሰው ሁሉ ከአራቱም የአለም ማእዘን ይረባረባል”ብሎ ነገራት፡፡ ከዚህ አምላካዊ ቃል የተነሳ ሁላችንም በተግባር እንኳን ባይሆንልን በመንፈስ ሸፍተን አሜሪካን ለመግባት ያላሰብንበት ጊዜ የለም፡፡እንደውም ድቪ ሎተሪ ያልሞል ሰው የለም ባልልም ሁላችንም የሜክሲኮን ድንበር ለማቋረጥ እንደሚታገሉት በሃሳብ ጥሰን ለመግባት ሞክረናል፡፡ሆኖም ግን የተሳካለት ተሳክቶለት ቀሪዎቻችን በጥበበ እግዚያብሄር እዚችው ቅድስት ሀገር ምህረቱንና ቸርነቱን፤ሰላሙንና ፍትሁን፤ፅድቁንና በረከቱን እየተጠባበቅን እንገኛለን፡፡      
ወጣቶች እህቶቼና ወንድሞቼ፤አረጋዊያን እናቶቼ እና አባቶቸ እኛ አላወቅናትም እንጅ እኛ አለወደድናትም እንጅ፤እኛ እንዳባቶቻችን አልሞትንላትም እንጅ ከአሜሪካ በእጅጉ የምትበልጥ ቅድስት ሃገር አለችን፡፡ይህች ሀገር የሰማይ መግቢያ ኤምባሲም ጭምር ነች፡፡በምድር ላይ ያለች ኤምባሲ የቅዱሳን ከተማ ነች፡፡እኛ በስራችን ሳይሆን በአባቶቻችን ስራና ባለሟልነት እዚህ ጊዜ ደረስን፡፡ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ይወርዳል ይወለዳል እያሉ ነቢያቶችና የነቢያቶች ቤተሰቦች ይጠባበቁ ነበር፡፡ነገር ግን እሱ ሳይወለድ የእነሱ ጊዜ ተፈፀመ፡፡ጌታችንም በወንጌል የእኔን መወለድ ብዙዎች ተጠባበቁ ግን አላዩም፤እናንተ ግን ተወልጀ አያችሁኝ እኔን ያዩ የእናንተ አይኖች ብፁዐን ናቸው ብሎ ለቅዱሳን ሀዋሪያቶቹ እንደነገራቸው፤እናንተ እና እኔም የሀዋሪያቶች ቢጤዎች ነን፡፡ደግሞም ይህ የሀገራችን ብሎም የአለም ትንሳኤ እንደ ጌታችን ልደት እኩል ባይሆንም እንኳን ብዙ አባቶቻችን ቅድሱ ቴዎድሮስን ዛሬ ይመጣል ነገ ይመጣል እያሉ ሲጠባበቁት ኖረዋል፡፡ሆኖም ግን እነሱ እንደ ነቢያት ሳያዩት እድሜያቸው ተገደበ፡፡    
 
እኛ ግን ሌሎች በደከሙበት ታሪክ በ11ኛ ሰዓት ላይ መጥተን ታሪካቸውን ታሪካችን ልናደርግ ጫፍ ላይ ደረስን፡፡ምክንያቱም እኔ ብሞትም ሌሎች ሰማንያ አመት የሆነው ሽማግሌ እንኳን ሳይቀር ለዚህ ታሪክ ተዘጋጅተዋልና፡፡በመሆኑም የሀገሬ ትንሳኤም ሆነ የአለም ትንሳኤ የሀገራችንም ሆነ የአለም ህዝብ በሶስት ዋና ዋና (ጥሎ ማለፍ) ክስተቶችን የሚመድብ  ሲሆን ይህም የሚሆነው ምድር ሳትቀር ለአውሬው በመገበፘ መፅዳት ስላለባት ከፀዳችም በኋላ የተቀደሱ ሰዎች ሊኖሩባት ስለሚገባ አምላካችን እግዚያብሄር የትውልድ ለውጥ ያደርጋል፡፡ይህ የትውልድ ለውጥ ጠላ ሲጠጡ ቆይቶ ወይን እንደመቀየር ነው፡፡ሁለቱንም የሚያመሳስላቸው የመጠጥ ዘር መሆናቸው ነው፡፡የሚለያቸው ደግሞ ከጠላ ይልቅ ወይን ደረጃው ከፍ ስለሚልና ያስደስታል ተብሎ ስለሚታመን ነው፡፡ዳዊትም እንዳለ “ወይን ልብን ደስ ያሰኛል” አለ፡፡እናም ይህ ትውልድ እንደ ሎጥ ፃድቅ ነፈሱን ሲያስጨንቅ የሚውል አለ፤ሌላም በግብረሰዶማዊነት የሰከረ ከመላእክቶች ጋር ካልተኛሁ የሚል የዝሙት አባዜ ያለባቸው ትውልዶች ነበሩ፡፡ስለዚህ እግዚያብሄር ሎጥን ሰወረው ሰዶማዊያንን ግን ሙት ባህር ከተታቸው፡፡የአሁኑም ትውልድ ከዚህ የተለየ ባይሆንም መለኪያ ግን አልተገኘለትም፡፡እስኪ 3ቱን ገፅታወች ያልኳችሁን እንይ      
1ኛው ክስተት-ለሰማእትነት የታጩ ድል ነሽዎችን በውስጡ የያዘውን ነው፣እነዚህ በኢትዮጵያ ትንሳኤ የመኖር እድል የሌላቸው ሰማእታት፤በቅድስት ስላሴ የምርጫ ቀለበት የገቡና ከትንሳኤው ዋዜማ ለሰማእትነት የታጩ፤ የተዘጋጁ የልዑል ከዋከብቶች ናቸው፡፡እነሱም የአውሬውን መንፈስ(666)በፅኑ በመቃወም የአለም ፈጣሪ፤የአለም ባለቤት፤አለምን የሚመግብ፤አለምን የሚያሰተዳድርና የሚያሳልፍ ቅድስት ስላሴ መሆኑን የሚመሰክሩ ናቸው፡፡ድያበሎስንም በማንኪያ ሰጥቶ በጭልፋ የሚቀበል ውዳቂ ዉድቅ መሆኑን በግልፅ ባደባባይ የሚዘልፉት ናቸው፡፡እሱ እንኳን በማንኪያ ሊሰጥ የጤፍ ፍንጣሪ እንኳን የሌለው ትሉኝ እንደሆነ የአንዱን ለአንዱ ከመስረቅ ዉጭ ሌላ ምን ጥበብ አለው፡፡እነኝህ ሰማእታቶች አሁን እኛ እንደምንፈራው የሚፈሩ ሳይሆኑ ለዚህ ሰነፍ ትውልድ የሚመረውን ሃቅ የሚግቱ፤ሰባኪያን የስም እነ ሊቀ ጠበብት የፈሩትን ከኦርቶዶክስ ሃይማኖት ዉጭ ሌሎች ሃይማኖቶች ጣዖት እንደሆኑና በውስጣቸውም ያለው አጋንንት መሆኑን በግልፅ የሚመሰክሩ ናቸው፡፡ስለ ቀናች ሃይማኖታቸው ላደረጉት ተጋድሎ ፅኑዓን ተጋዳሊያን ይባላሉ፡፡በእነሱ የክብር መዝገብ ስር እንደነሱ ፅኑዓን ባይሆኑም ሃይማኖታቸውን ከምግባር አስተባብረው፤ ሀይማኖቴን አልክድም፤የሰው ገንዘብ አልቀጥፍም፤አላመነዝርም፤ህገ አምላክን አልጥስም ብለው በማመናቸውና በመኖራቸው ምክንያት በአማፅያንም ሆነ በሌላ የተፈጥሮ አደጋ በሀይወት የሚያልፉና የኢትዮጵያን ትንሳኤ ያልተቀላቀሉ ሁሉ ከሰማእታት ወገን የሚጨመሩ ይሆናሉ፡፡   

2ተኛው ክስተት ለኢትዮጵያ ትንሳኤ የሚደርሱና የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክን ፈቃድ በአለም ላይ የሚፈፅሙና የሚያስፈፅሙ ለአምላክ እናት ለቅድስት ድንግል ማሪያምና ለቅዱሳን ሁሉ ፍቅር፤ክብርና ምስጋን የሚያቀርቡ በበጉ በኢየሱስ ክርስቶስ የደሙ ማህተብ በስላሴ ስም አንፃር በግንባራቸው ማህተብ የተደረገላቸው ፤በፅድቃቸው ሳይሆን በቅድስት ስላሴ የምርጫ ቀለበት ውስጥ የገቡ ናቸው፡፡እነኝህ በቅርቡ በሚመጣው ትንሳኤ የቤተ መንግስቱንም ሆነ የቤተ ክህነቱን ከፍተኛ የስልጣን እርከን የሚቆጣጠሩ ናቸው፡፡ከንጉሳቸው ከሳልሳዊ ቴዎድሮስና ከጳጳሳቸው የሚሰጣቸውን ትእዛዝ ሁሉ የሚፈፅሙ፤ ምእመናንን የሚያገለግሉ ናቸው፡፡እጅግ ጥቂት ምዕመናንም እንደነሱ ዉድ ዋጋ ከፍለው ትንሳኤውን የሚቀላቀሉ ይሆናል፡፡    
   
3ተኛው ክስተት ደግሞ እጅግ በጣም አሳዛኝ ገፅታ ነው፡፡ይህን ስናገር እየሰቀጠጠኝም ቢሆን ግን የማይካድ ሀቅ አይቀሬ ጉዳይ ነወና መርዷችሁን ላረዳችሁ ግድ ነው፡፡በዚህ ምዕራፍ ስር የተካተቱ የአዳም ዘር በሙሉ በአለም ተበትነው አጋንንት ጋር ተፈራርመው፤ ተጋብተው በምድር ገነትን የመሰረቱና የኖሩበትም ናቸው፡፡ለእነዚህ ሰዎች ፀሀይ አትጠልቅም፤ጨረቃም ከቀበጠች ከእሷ የሚበልጥ ጨረቃ ይተካባታል፡፡እነኝህ ሰዎች ቀን እንደመላእክት ሌሊት ደግሞ እንደ ሰይጣን መሆን ይችሉበታል፡፡እግዚያብሄር ስለመኖሩ እርግጠኛ አይደሉም፤እንደው ስሙ ራሱ ሲጠራ ሰምተው የሚያውቁ አይመስልም፤ቅዱሳንንማ በፍፁም አያቋቸውም፤ዉስኖቹ ስለቅዱሳን ሰምተው እንኳን ቢሆን ድጋሚ ስማቸው እንድጠራባቸው አይፈልጉም፡፡በተለይ ይህች ማርያም የምትባል፤ገብርኤል፤ሚካኤል፤ጊዮርጊስ፤ተክለ ሃይማኖት….ወዘተ(ወዳጀ አንተ አታቅም እንጅ እነሱስ የፀጋ አምላክ ናቸው፡፡ባንተ ህይወት ላይ የተሾሙ ባለሟሎች ናቸውና ስለማታውቀው ነገረ በቅዱሳን ላይ አፍህን አትክፈት)ተብሎ ቢጠራባቸው ያንባርቃሉ፡፡በዚህ ክፍል ዉስጥ ያሉ ሰዎች በደፈናው የሚታለፉ አይደለም መዓቱም የመጣው ለእነሱ እንጅ ለማንም አይደለም፡፡አምላካችን ለአህዛብስ እንኳን እንደሚፈርድላቸው ተፅፚል፡፡ሆኖም ግን ጥብቅ ግን ፍትሃዊ ፍርድ ይፈርዳል፡፡ማፍያወች አሉ፤ቀን መላእክት ሌሊት ደግሞ ሰይጣን የሚሆኑ አሉ፤እንደ አጋንንት ቀንድ የሚያወጡ አሉ፤ሰው ለመብላት የተፈጠሩ ይመስል ሰው በላ ህዝብ፤አጋንንትን የሚጠሩ፤የሚያዙ፤የሚያሰሩ፤የሚፈቱ አሉ፡፡የሰውን ነፍስ ከነህይወቱ የሚቀብሩ አሉ፤24፡00 በመብላትና በመጠጣት የሚያሳልፉ አሉ፡፡የሰው እድል በመስለብ አሊያም እንድሞት ሽባ እንድሆን፤ እነዳያልፍለት፤ ቤቱ ሰላም እንዳይሆን፤ የማንም አገልጋይ እንድሆን የሚሰሩ አሉ፡፡”ሆዳቸው አምላካቸው፤ ክብራቸው በነውራቸው ነውና እግዚያብሄር ይደመስሳቸዋል፡፡ እንደ አህያ እሬሳም ያደርጋቸዋል፡፡እነኝህ ባልተፈጠሩ በተሻላቸው ነበር፡፡ቁጥራቸውም ቀላል እንዳይመስላችሁ በሚሊየንም አይደለ በቢሊየን የሚቆጠር ነው እንጅ፡፡በምድርም እነሱን የሚያጠፉ ቅዱሳን መላእክቶች ሰይፍ ሰይፋቸውን ይዘው እየተጠባበቁ ነው፡፡የተፈጥሮ ሃይላትም ይገለባበጡባቸዋል፡፡ምድርንም ሰማይንም ሰዉሩን ይሏቸዋል እነሱ ግን አይሰሟቸውም፡፡ሞተው በሰማይም መግቢያ በራቸው የተዘጋ ነው፡፡አሁን የሚጣሉበት ቤትና ህንፃ፤ የሚገዳደሉበት ብሄርና ክልል፤የጦር መሳሪያና ሃብት፤ቡድንና ሃገር ያድናቸው ይሆን?አይደለም የተመኩበት ሁሉ ቤትና ህንፃ፤ የሚገዳደሉለት ብሄርና ክልል፤ሃብት፤ንብረት ሃገርም ሁሉ ለተናቁት ተላልፎ ይሰጣል፡፡ሀሀሀሀሀሀሀ እነሱ ሲሄዱም ምንም ይዘው እንዳይሄዱም ይፈተሻሉ ድንገት እንደለመዱት ስላሴን እንዳይሸውዱም ጥብቅ ፈተሻ ይደረጋል ልበላችሁ?የተናቁት፤ጎዳና ላይ የወደቁት፤የአውሬው ስርዓት የተፋቸውና አበቃላቸው የተባሉት ግን ክብርና ምስጋና ይገባቸዋል፤በበጉ ደም ፀንተው የክርስቶስ ወታደር ሆነዋለና፡፡እነሱም በተራቸው ባለ ፀጋ፤ባለ ቤት፤ባለ ሃገርና ባለስልጣን ይሆናሉ፡፡ክብርና ምስጋና ለቅዱሳንና ለማሪያም፤ለአምላካቸውና ለአባታቸው ለእግዚያብሄርም እንደጎርፍ ዉሃ ምስጋናን ያፈሳሉ፡፡አለም ለእነሱ ተገብታቸዋለችና፡፡አሁን አለም ይህን ሃቅ መስማት አትፈልግም ዳንኪራ ላይ ነች ግን የማየት እድሉ የላቸውም እንጅ መጨረሻውን ቢያዩት መልካም ነበር፡፡”የሰው ልጅ ክቡር ሆኖ ሳለ ሳር እንደሚበላ እንሰሳ መሰለ” አለ ክቡር ዳዊት፡፡ 

አይ የሰው ልጅ………  
ሰው ማለት በምድር ላይ ወድቆ የሚቀር ሳይሆን የመላእክትን ባህሪይ የተላበሰ ሰማያዊ፤በአንፃሩ ደግሞ እንሰሳዊ ባህሪንም የተላበሰ ምድራዊ ፍጥረት ነው፡፡ሰው ማለት የነፍስና ስጋ ውህደት ነው፡፡የእግዚያብሄር መንፈስ ማደሪያ የሆነ በፀጋ እግዚያብሄር የከበረ ፍጥረት ሁሉ ለእሱ የተፈጠሩለት ነው፡፡የእግዚያብሄር መንፈስ በእኛ ላይ ስለሚያድር እኛ ልዩ ፍጥረቶች ነን፡፡ነገር ግን ዳዊት “አቤቱ በዚያን ዘመን ሰው የሆነ ሰው አጣሁ” አለ፡፡በመንፈስ ቅዱስ ተመጥቆ የዚህን የ8ተኛውን ሽህ ትውልድ ስላየው ከሰውነት ተራ ወጥቶ አጋንንት ጋ ተዋህዶ ምትሃተኛ ትውልድ ሆኖ ስላየው ነው፡፡ጌታችንም ክብር ምስጋን ይግባውና ለቅዱሳን ሃዋሪያቶቹ ”በዉኑ የሰው ልጅ ሲመጣ ሰው የሆነ ሰው ያገኝ ይሆን” አለ፡፡ነፍሳችን ከአጋንንት ጋር ስትዋሀድ አመፅን፤ግድያን፤ክፋትን ትሰራለች፡፡በአንፃሩ ከእግዚያብሄር ጋር ስትዋሀድ ደግሞ ፅድቅን፤የዋሀትን፤ገርነትን፤በጎነትን፤ቸርነትን….ወዘተ ታደርጋለች፡፡ከስላሴም ዘንድ በምድር ላይ ተገልፃ የምናየውን የሃብትም ሆነ የልጆች ስጦታን የምናገኘው ነፍሳችን ከተሰጠችው በረከት የተነሳ ነው፡፡ስለዚህ በረከትን የምትቀበል፤የምትመሰገንም ሆነ የምትዘለፍ ነፍሴ እንጅ ይህ ግዑዝ የሆነ ስጋችን አይደለም፡፡ይህማ በቀላል አማርኛ ጃኬታችን ነው፡፡እኔን ይህ ስጋየ አይወክለኝም፡፡ግን ደግሞም ያለ እሱ ነፍሴ በምድር ላይ ተገልፃ መኖር አትችልም፡፡ወንድሞች ሆይ እስኪ አስተዉሉት አንድ በጣም ቆንጆ የሆነ ወጣትና አንድ በለምፅ የተመታ የኔ ቢጼ ወጣት በስላሴ ፊት የሚታዩት አፈር የሆነ ስጋቸው አይደለም የነፍሳቸው ንፅህና እንጅ፡፡መማራቸው፤ሊቅነታቸው የሚለካው በንፅህናቸው እንጅ በወረሱት ምድራዊ እውቀት፤ሃብትና ጥበብ አይደለም፡፡በዚህ ዘመን የሰው ልጅ ከፍተኛ የሆነ የቴክኖሎጅ ፤የስልጣኔና የሀብት ደረጃ ላይ መድረሱ ይታወቃል፡፡በአለም ላይ ቀርቶ በሀገራችን የሚለበሰውን የልብስ አይነት፤ደረጃና ጌጥ እናንተ ታውቃላችሁ፡፡ነገር ግን ትውልዱ ሁሉ ልብስ የተባለ ፀጋ እግዚያብሄር ስለሌለው ሁሉም ራቁቱን ይሄዳለ፤ይኖራል፤….እስኪ አስቡት ስንት ሰዎች በአለም ላይ  ልብስ ለብሰው ይሆን? እሱም ልብስ የተባለ ፀጋ እግዚያብሄርን ለብሰው ይሆን?ለዚች ለኮንትራትና ጊዜያዊ ኑሮ ብለን ስንቶቻችን ራቁታችን ሄደን ይሆን፡፡አብርሃም አባታችን ለዚያ ሁሉ እድሜው ድንኳን ከሰራ እኛ ለሰባ እና ሰማኒያ ለማይሞላ እድሜያችን ጅ- ፕለስ ሰማኒያ እና ከዚያ በላይ መስራታችን ለምን ይሆን?ቢሆንስ በወንድሞቻችን የደም መሰረት ማነፁ ፍትሃዊነት ይኖረዋልን?የሚገርመው ደግሞ ለሌሎች ቀርቶ ለራሳችን እንኳን አለማወቃችን ነው፡፡

ሳይንስ፤ግለሰብ ፤ቴክኖሎጅ፤ቡድንም ሆነ መንግስት ስለኛ ስጋ(ልብስ) እንጅ እስካሁን እኛን ስለምትወክለን ስለ ነፍሳችን አላወሩም አልሰሩምም፡፡ይህ የሚያሳየው ሰው ራስ ወዳድ ሳይሆን ራሱን መጣሉን ነው፡፡ስለራሱ እንኳን የማያውቅ ምሁር፤ስለ ራሱ እንኳን የማያውቅ መሪ፤ስለራሱ እንኳን የማያውቀ ሳይንቲስት በቁሙ የሞተ ተንቀሳቃሽ አስከሬን እንጅ ሰው አይባልም፡፡እውነት ነው ለራሳችን የሆነ ቪላ ቤት፤መኪና፤የቅንጦት ምግብና ልብስ ሊኖረን ይችላል፡፡ታዲያ ምን ያደርጋል ደስታ የለ፤ሰላም የለ፤እርካታ የለ፡፡ለምን ቢባል የነፍሳችሁ ውህደቷ ከአጋንንት ጋር ከጨለማው ገዥ ጋር ነዋ! እውነተኛ ሰላምና ደስታ ግን የሚገኘው ለስላሴ በመስገድና ቅዱሳንን በመዘከር ነበር፡፡መፅሀፍ ካለማወቅ የተነሳ ትስታላችሁ እንዳለ በመንፈሳዊያንና ቀለማውያን (በአለማውያን)  መካከል ብዙ ልዩነት አለ፡፡ ለምሳሌ ላንሳላችሁ እና ወንድሜ ዳንኤል ክብረት ከዶ/ር አብይ ጎን ሁኑ አለ፡፡ከጎኑ መሆን ካልቻላችሁ ደግሞ ተከተሉት አለ፡፡መከተል ካልቻላችሁ ግን እንቅፋት መሆን አትችሉም አለ፡፡እሱ የሚያስተምርለት ስላሴ ግን ይህን አይደለም ሊሰራ ያሰበው፤ድሮ ስለ አብይና ሌሎች አህዛብ ህውሃትን ጨምሮ የተነገረላቸውን አሳይመንት ጨርሰው ቅዱሱን ማንገስ ነው፡፡እነሱ ሳይመጡ ቅዱሱ አይወጣም፡፡የነሱ ዘመን ደግሞ ድያ፤ዘረፋ፤ክህደት፤ገንጣይነት፤ፓጋንነት…..ነው፡፡ግዛቱ የጨለማ(የአውሬው አሰተዳደር በመሆኑ፡፡)በዋናነት ትንሳኤው የሚመጣው በመንፈሳዊያንና በአጋንንትን እንድሁም በአጋንንት አሽከሮች በተደረገ መንፈሳዊ ዉጊያ ነው፡፡እናም ዳንኤል አሰላለፉ መስተካከል ነበረበት፤ ግን ስጋዊ ነውና የጨለማው ዘመን እንድቀጥል ፈለገ፡፡ የሰው ልጅ ፅድቅም ሃጢያትም ይስማማዋል፡፡ሃጢያተኛ ከሆነ ግን በምድር ላይ ደካማ ይሆናል ድያብሎስ እንደፈለገ ይዋሀደዋል፤ይገባበታል ይወጣበታልና፡፡ 

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment