በመከራው ጊዜ የሚያስፈልጉ ከገዳም አባቶች

ለሚመለከታችሁ❗️እና ቀኑን ለምትጠባበቁ በሙሉ❗️ 

➪ ባቄላ ፤ ሽምብራ ፤አተር ፤ነቀዝ እናዳይበላው በምጣድ አመስ አመስ አድርጎ ማስቀመጥ ➪ ጥቁር ጤፍ ለአጥሚት የሚሆን በጥሬነቱ ሳይፈጭ ማስቀመጥ ረሃቡ ሲገባ እፍኝ ያህል እየዘገኑ በድንጋይ ወፍጮ ፈጭቶ በጨው አጥሚት ሠርቶ ብዙ ቤተሠብ ውሎ ያድርበታል፡፡

➪ ከማይነቅዙ እህሎች ዳጉሳም ያስፈልጋል፣ ቀዪ ውሀ የሚያነሳው ዳጉሳ ሌላው አይሆንም። 

➪ ከተገኘ ንፁህ ማር ችግሩ ሲገባ በውሃ በጥብጦ መጠጣት ነው፡፡ ብዙ በሽታ ይከላከላል፡፡ 

➪ ገብስ ቆሻሻውን ለቅሞ እንክርዳዱን ጭምር ፈትጎ አድርቆ ለበሶ ቆልቶ የኤሌትሪክ ወፍጮ ሳይጠፋ ጨው ጨምሮ አስፈጭቶ በደረቅ ቦታ ማስቀመጥ በገበያ የተቆላው በሶ ስልሚተላ እርሱ አይሆንም፡፡ ➪አብሽ ቆሻሻውን ለቅሞ ወደ ማታ በውሃ ዘፍዝፎ ጠዋት ሲነጋ ውሃውን አጥሎ በፀሃይ ለሶስት ቀን በተከታታይ በደንብ አድርቆ በአብሽ ወፍጮ አስፈጭቶ በደረቅ ቦታ ማስቀመጥ የርሃቡ ዘመን ሲመጣ በሶውንና አብሹን በጨው በጥብጦ መጠጣት አዋቂ ቢጠጣው ለሰባት ቀን አይርበውም፣ ህፃን ቢጠጣው 3ቀን አይርበውም፣ ለራበው ሠው በጥብጠው ቢያጠቱት( ቢያዘክሩት) ቸሩ መድሃኒያለም ለገነት መንግስት ሠማይ የሚያበቃ ዝክር ቸሩ መድሀኒዓለም ያደርግለታል፡፡

የእስራኤል ጅብና መተተኛው የሱዳን ጦርነት ኢትዮጲያ ውስጥ ሲገቡ መፆም የለም መፆም፣ መፀለይና መስገድ የለም ፡፡አሁንም ዘመኑ አልፎ ፃዲቁ ንጉስና ጳጳስ ሲወጡ ነው፡፡ማለትም የእስራኤል ጅብና መተተኛው ሱዳን በተቅማጥ በሽታ ካለቁ በኋላ ነው፡፡ የሚጠፉቸው ገናናው ፈጣሪ ነው፡፡

➪ ሌላው ነጭ ሽንኩርት ከነጅራቱ ከነ ጎንጎኖ እንዳበላሽ ማዕድ ቤት (በጭስ ቤት ) ሰቅሎ ዘመኑ እስኪደርስ ማስቀመጥ ዘመኑ ሲደርስ አንድ እራስ ነጭ ሽንኩርት ፈልፍሎ ማታ ቤተሰቡ አንድ አንድ ፍልቃቂ ቢበላ ለሃያ አራት ሠዓት ከመተት ይድናል ቀንም ከቤቱ ሲወጣ በቀኝ አፍንጫው የተላጠ ነጭ ሽንኩርት ወትፎ መውጣት አለበት፡፡

➪ በድልህነት ደረጃ የሚዘጋጅ፡- አንድ ኪሎ ሚጥሚጣ፤ ሃያ ኪሎ ነጭ ሽን ኩርት፤ አምስት ኪሎ ጨው፤ ሩብ ኪሎ ጤናዳም፤ አንድ ኪሎ ዝንጅብል፡፡ ከዚህ በታች ያሉት የተዘረዘሩት ሲዘጋጁ ሩብ ኪሎ ይበቃል እነርሱም፡- ኮሰረት ወይም ክሴ፤ጥምዝ ቅመም ፤ቀረፋ፤ ቅርንፉድ፤ ቁንዶ በርበሬ ፤ነጭ አዝሙድ፣ ጥቁር አዝሙድ ፤ከሙን፣ ኮረሪማ ፤ በሶ በላ ፤ አዝመሪን ወይም የስጋ መጥበሻ ሌሎችም የቅመም አይነቶች ተወቅጠው ተነፍተው ደርቀው ልመው በትልቅ ዕቃ አደባልቆ በቀዝቃዛ ውሃ በደንብ በሳሙና በታጠበ አፉ ሰፊ የማይዝግ ብረት ወይም ላስቲክ እቃ ወይም ትንፋሽ በማያስወጣ የሸክላ እቃ ማስቀመጥ ይገባል፡፡ ክፉ ዘመን እስኪደርስ እየተብላላ ይቀመጣል፣ ሰዓቱ ሲደርስ ትንፋሹ ሳይወጣ ቀንሶ በምግብ ላይ አድርጎ መብላት ወይም መላስ ነው።

➪ በዱቄትነት ደረጃ የሚዘጋጁ፤- ማንኛውም ማስቀመጫ እቃ በወይራ ይታጠናል ፤ አስር ኪሎ ነጭ ሽንኩርት ሁለት ኪሎ ተኩል ጨው፣ ግማሽ ኪሎ ዝንጂብል፣ የሩብ ሩብ ጤናዳም፣ እነዚህን ደቁሰው አድረቀው ዱቄት አድርገው ያስቀምጡ፡፡በክፉው ዘመን በምግብ ላይ እየነሰነሱ መብላት ነው፡፡ እነዚህን የቀመሰ ሰው የእስራኤል ጅቦች ሲመለከቱ እጃቸውን እያርገፈገፉ ይሸሻሉ፡፡ የሱዳንም መተት አያገኘውም፡፡
➪ለወረርሽኝ በሽታ መከላከያው:- #የክትክታ_እንጨት ፈልጦ ማስቀመጥ ነው፡፡ ዘመኑ ሲደርስ መታጠን ነው፡፡ ➪የክትክታውን እንጨት ብር አለኝ ብሎ በገንዘብ መግዛት የተከለከለ ነው፡፡ የሸጠም የገዛ ወዮለት ተብሏል ፡፡

❗️በዚያን ዘመን የማይበሉ ለሱዳኖች የመተታቸው ማደሻ ስለሆነ #ቀይ_ሽንኩርት እና #በርበሬ በፍፁም አይበላም፡፡ እነዚህ ቅመሞችም እነዚህ በተወቀጡበት ሙቀጫ አይወቀጡም ጥንቃቄ ያስፈልጋል፡፡ ➪ በዚያን ዘመን እንደአቅሙ አዘጋጅቶ የጠበቀውን ሰው ትንሹን ትልቅ ያደርግለታል፡፡ ረድኤተ እግዚአብሄር በተዘጋጀው ቁሳቁሶች ላይ ያድርበታል፡፡ ➪ ሌላው የውሃ ማጠራቀሚያ ላስቲክም ይሁን የማይዝግ በርሚል በወይራ አጥኖ ማስቀመጥ ይገባል፡፡በየአስራ አምስቱ ቀን እየተጠቀሙ መልሶ አጥቦ እቃውን በወይራ አጥኖ መጠበቅ ይገባል፡፡ ቀኑ መቸ ነው ከሰራዊት ጌታ እግዚአብሄር በስተቀር ሚያውቀው የለም፡፡

➪ ለቀኑ መዳረሻ የሚሆኑት አብዛኛው ተፈፅሟል፡፡ ➪ ስዕለ አድኖወች በየመንገዱ መናፍቆች ያስቀምጣሉ እንዳትረግጡ ሰብስባችሁ በመንገዱ ዳር ብትችሉ ለቅማችሁ ቅድስት ቤተክርስትያን ማስቀመጥ ነው፡፡

ሌላኛው:- 

➪ረጅም ትራንስፖርት ይሄ ማለትም የባቡር አገልግሎት መጀመር ቅድስት ቤተክርስትያን በሳምንት አንድ ቀን መቀደስ ቅዳሴውም እየተጣደፈ ነው የሚቀደስው፣ ከህናት የገቡበት ድርጅት ስዓቶችን እንዳያልፍ በማለት ያደርጉታል፣ ያስተውሉ በመጨረሻ ከክፍለ ሀገር ክፍለ ሀገር የሚጓዝ አውቶብስ የእቃ መጫኛው ላይ እንደ ሄሊኮፍተር የሚሽከረከር መኪና ይመጣል፤ ብዙ ቀንም ሳይቆይ የእስራኤል ጅብ ይገባል፣ በእነሱ እግር ተከትለው መተተኛው ሱዳን በመተማ በተቀደደለት መንገድ ይገባል፡፡ በዚያን ጊዜ የመንግስትም ሆነ የግል ሥራ የለም ሁሉም በየቤቱ መቀመጥ ይሆናል፡፡ ያዘጋጀ እየተጠቀመ ላዘጋጀ ቢሰማም እንኳን አልሰማሁም በማለት ይክዳል፡፡ በዚያን ጊዜ ወላዲተ አምላክንና የሰው ልጅ ፈጣሪውን ማማረር አይችልም አስቀድሞ መልዕክቱን በባሪያዎቹ ስላስተላለፈ ልብ ያድርጉ፤ አነሰ በዛ ሳይሉ ተዘጋጅተው ይጠብቁ፡፡ የድንጋይ ወፍጮ ከነመጁና መሠለቂያው ያስፈልጋል፡፡ በዚያን ዘመን በመከራው ጊዜ ፆም የሌለው ጠዋት የታመመው እስከማታ አይደርስም፣ ማታ የታመመው እስከ ጠዋት አይደርስም ይሞታል ወረርሽኝ በሽታውና ርሃቡ ፅሙ መተቱ ያጠፋዋል፡፡ በዚያን ዘመን ሰው የሚቀብረው ጠፍቶ በየፈፋው በየገደሉ ይጣላል፤ የሰው ልጅ ክቡር ስለሆነ ከእየሩሳሌም የመጡ አሞራዎች ስጋውን በልተው በሆዳቸው ይቀብራሉ፣ አጥንቱንም ከስላሴዎች የታዘዙ አንበሶች ቆረጣጥመው በሆዳቸው በፈጣሪ ትዕዛዝ ይቀብራሉ፡፡ ይህ መከራ ዓለም ከተፈጠረ ሆኖ የማያውቅ ነው፡፡ ከህንፃ በዓለም ካለው የፋሲል ግንብ ብቻ ለምልክት ይቀራል፣ ጣሊያን የሠራው የምፅዋ ወደብ ደግሞ እስከ ዳግም ምፅዓት ይቆያል፣ ይህ አይሆንም ማለት መሽቶ አይነጋም ማለት ነውና እንደ አብርሃና አጽብሃ ዘመን ሁለት ነገስታቶች ይነግሳሉ ቴዎድሮስና ስሙ ዛሬ የሚነግረው የጽድቅ ንጉስ አቡነ አረጋዊ፣ አቡነ ፀሐይ ተብለው ለሰባቱም ክፍለ ዓለም ክፍለ ዓለም ኢትዮጵያ ገዢ ሆኖ ከመቶ አስር ሰው ታስተዳድራለች፡፡ ከመናፍቆችም በዓለም ውስጥ ካሉት ለወሬ ነጋሪ የሚተርፍ የለም፡፡ ነገር ግን ከእስላሞች ከመቶ አንድ ተርፈው ለጥምቀተ ክርስትና በቅተው ፈጣሪያቸውን እንኳን ፈጠርከን ብለው የሚያመሰግኑበት ዘመን ከተዋህዶ ልጆች ጋር ከመቶ አስር ከተረፉት ጋር ይደርሳሉ፡፡ አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ አንዳንድ አውሮፓውያን ተርፈው ከመከራው በኋላ ቴዎድሮስ ሲነግስ ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ለቴዎድሮስ አንድ መርከብ ሙሉ ወርቅ ለዘር ኢትዮጵያ አተረፈችን ቅድስት ሀገር ብለው ፈጣሪያቸውን ያመሰግናሉ፡፡ 

 ስለዚህ እንደፀሐይ የምትሞቀው ዘመን ለመድረስ ቸሩ ፈጣሪያችን ያብቃን! አሜን!

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment