ኢትዮጵያን እና ተዋህዶን ለማጥፋት ብሔርተኛ ትውልድ መፍጠር!!!


ከታሪክ መማር ካልቻልክ ስህተቶችን ከመደጋገም አትቆጠብምና ሞኞቹ ኢትዮጵያውያን በውጭ ጠላቶቻቸው በመታለል የራሳቸው ጠላቶች በመሆን ላይ ናቸው።
ቀደም ሲል፡ ሱዳኖች የተባሉት ኢትዮጵያውያን “የሱዳን አረቦች ነን ኢትዮጵያውያን አይደለንም” አሉ፤ ከዚያ የጂቡቲ ኢትዮጵያውያን “ጂቡቲያውያን ነን ኢትዮጵያውያን አይደለንም” አሉ፣ ቀጥለውም ሰሜን ኢትዮጵያውያን “እኛ ኤርትራውያን ነን ኢትዮጵያውያን አይደለንም” አሉ፣ ብዙም አልቆየም ደቡብ ኢትዮጵያውያን፤ “የለም እኛ ኢትዮጵያውያን አይደለንም ኦሮሞዎች ነን” አሉ፣ ዛሬ ደግሞ “ትግሬ እና ዐምሓራ” የተባሉት “አይ እኛ በቅድሚያ ትግሬዎች እና ዐምሓራዎች ነን” በማለት ላይ ናቸው።

እንግዲህ እነዚህ ኢትዮጵያውያን የጠላትን ተንኮል ባለመረዳትና ከጠላት ጋር፡ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መልክ በማበር “ኢትዮጵያን” ከማንነታቸው ላይ ለመፋቅ በፈቃዳቸው ተግተው በመሥራት ላይ ናቸው። እራስን ለማጥፋት!

ሰሞኑን “ዐምሓራ” በተባሉት ኢትዮጵያውያን ላይ እየተካሄደ ያለው ጥቃት ሆን ተብሎ፣ ሰው ሠራሽ በሆነ መንገድ በመንደርተኛ ብሔር ግንባታ ላይ በተናጠል ትኩረት እንዲያደርጉ ለመገፋፋት ነው፤ ልክ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ ሲዳማ ወዘተ እንደተባሉት፡ ከኢትዮጵያዊነታቸው በፊት መንደርተኛነታቸውን ያስቀድማሉ ማለት ነው። “ዕንቁላል ወይስ ዶሮ?” የሚለውን የተለመደ ዕንቆቅልህ ምን አውቅልህ ጨዋታ ይመስል”።
የዚህ ሁሉ ዲያብሎሳዊ አጀንዳ ዓላማም የእኔ የሚሉትን አዲስ ማንነትን እንዲይዙ እና “ኢትዮጵያን” እንዲረሱ፣ አማርኛ ቋንቋን ከብሔራዊ ቋንቋነት ለማስወገድ፣ የኢትዮጵያን አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ሰንደቅ ዓላማ ለማስተው፤ በመጨረሻም፡ ዋናው ግባቸው ነው፤ የተዋሕዶ ክርስትናን ለማጥፋት ነው።
በቀጥተኛነታቸውና በግልጽነታቸው የማደንቃቸው ኢንጂነር ይልቃል እንኳን ባንድ ወቅት “አማራ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ማለቱ አስጠቅቶታል ” ብለው ነበር።
አይ! ይህማ አይሆንም፤ “ኢትዮጵያዊነታችንንማ በፍጹም አንተውም” ልትሉ ትችላላችሁ፤ ነገር ግን አይምሰላችሁ፤ በዚህ ከቀጠለ፤ በዛሬው ውጥቅንቅጥ ሥርዓት እያደጉ ያሉት ሕፃናት በሚቀጥሉት ሃያ አመታት ውስጥ ሁሉንም ነገር እርግፍ አድርገው በመተው ዲያብሎስ የፈጠረላቸውን አዲስ ማንነት ይቀበላሉ። ለዚህም የእነ ዶ/ር አብዮት አሕመድን ፀረ–ኢትዮጵያ አጀንዳ አራማጆች እና እየተሠራ ያለውን ፀረ–ኢትዮጵያ ሤራ ማየት የተሳናቸው እውሮች ከተጠያቂነት አያመልጡም። ኢትዮጵያን በመተው ባንዲራዋን እና መስቀሏን ያልተሸከም ሁሉ ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ እንደሚወድቅ፡ ሱዳን፣ ጂቡቲ እና ኤርትራ ምስክሮች ናቸው።
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment