ለኢትዮጵያ የታዘዙ መቅሰፍቶች

✍ አየነው ገብረመስቀል

አለም ተገልፆ የማያልቅ ብዙ መቅሰፍቶች የተደገሰላት ቢሆንም፡፡ሃገራችን ኢትዮጵያ ግን ሶስት ዋና ዋና መቅሰፍቶች ታዘውባታል፡፡     
  
1ኛው.ጦርነት ነው፡፡በዚህ ማጣሪያ ወንፊት ሁሉም ጦርንትን ስለሚመኝ ይመሰለኛል ለጦር የሄደ ሁሉ አይመለስም፡፡ወንድማማቾቹ የትግሬና የአምሃራ ወጣቶች እርስ በእርስ ይገዳደላሉ፡፡ከሁለቱ ይህ ተረፈ የሚባል አይኖርም፡፡ሁሉም በሜዳ እንደወጣ መቅረት፡፡እኔ በግሌ ሁለቱንም ወንድማማቾች እወዳቸዋለሁ በእዉነት እንደነሱ ለረጅም ዘመን በታሪክ፤በደም፤ይልቁንም በሃይማኖት እግዚያብሄርን በማገልገል የተሳሰረ ያለ አይመስለኝም፡፡አክሱም ፅዮንንና ግሸን ማሪያምን፤ጣና ቂርቆስንና ደብረ ሃሌ ሉያ አቡነ አረጋዊን እንደት አድርጌ አንዱን ከአንዱ ልለያቸው፡፡የትኛውን ጠልቸ የቱን ልውደድ??ይህ አይገባም መለየት መለኪያውም አይደለም፡፡ከቦታ ይልቅ የከበሩት እነኝህን ወንድማማቾችም መለየትም አይቻልምና፡፡ሆኖም ግን በአሁን ስዓት፤ ዮሴፍን የማያውቅ ንጉስ በግብፅ ተነሳ እንደተባለ የአጤ ካሌብና የአጤ ዘርዓያእቆብ ልጆች ግን ይጨካከናሉ፡፡ይቺ መሆኒ የምትባል ቦታ የሁለቱን ወጣቶች ደም ትጨርሳለች የትግራይ ወጣትም ክልላቸው በጠላት እንዳትያዝ ቀድመው እዚች ቦታ ላይ ይከማቻሉ፡፡ነገር ግን ወንድማቸውን ገፍተውታልና ግባተ መሬታቸው እዚች ቦታ ላይ ይፈፀማል፡፡እኔ ትግሬ አይደለሁም እስኪሉ ድረስ በየቦታው ታድነው ይገደላሉ፡፡ከዚህ በኃላ ምድር ተዘርግቶ እስኪታጠፍ ድረስ ለትግሬ ዳግም መሪ መሆን  ጭንቅ ነው፡፡ይህን ሃቅ የእኛ ብቻ ብለው የሚቆጥፘቸው አባት ግን የሁላችንም የሆኑት አባ ዘወንጌልንም ቢጠይቁ ይረዱታል፡፡የሆነ ሆኖ ግን እጅግ ጥቂት የሚሆኑና የተመረጡ ዘረኝነት የሌለባቸው፤ሰውን በመግደልና በሌላው ሞት የማይደሰቱ፤የትግራይን ልጅ ከሁሉም የሰው ልጅ ጋ በጥቅምም ሆነ በሌላ ነገር የማይለዩ፤ትግራይ ትቅደም ሳይሆን ወንድሜ የአዳም ልጅ ይቅደም ብለው የሚያስቡ፤ የትግራይ ከዋክብቶች ልዑል ባዘጋጀላቸው ቦታ ለትንሳኤው እንደተዘጋጁ ይታወቃል፡፡ አምሃራ ግን አንዴ ነፃ የወጣ ህዝብ ነውና ወደፊት የሚዘመርለት ይሆናል፡፡አምሃራ ጠላት የለውም ካለውም የአምሃራ ጠላት የስላሴ ጠላት ነው፡፡እሱም የስላሴን ሃይማኖት የሚቃወም፤የስላሴን ባንድራ የሚቃወምና የስላሴን ሃገር ቅድስት ሃገር ኢትዮጵያን የሚቃወም ነው፡፡የአምሃራና ታቦት ይዞ የመዞር አባዜ ሚስጥር፤አምሃራና ቅድስት ስላሴ፤አምሃራና እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም፤አምሃራና ቅዱሳን ሰማእታት፤አምሃራና ቅዱሳን ፃድቃን፤ አምሃራና ኢትዮጵያ፤ አምሃራና  የጠፋው አለም ምን አይነት ህብረት እንዳላቸው ይተነተናል፡፡አምሃራ የስው ልጅ መለኪያ ውሀ ልክ መሆኑ ይነገራል፡፡አሁን ግን ትግሬ ብቻ አይደለም አለምም በአንድ ተደምሮ አምሃራንና ኦርቶዶክስን ለማጥፋት ይዶልታል፤ይሞክራል፤ተሳክቶለታልም፡፡ግን እስራኤልን የሚጠብቅ አያንቀላፋም፡፡ወዳጄ የሁሉ ጌታ የሁሉ ፈጣሪ አምላክህ  እግዚያብሄር አንዴ ስምክን በፍቅር ይጥራው፡፡አንዴ በፍቅርና በስስት አይኑ ይይህ ከዚያ በኃላ ስላሴ እንደ ሰው አይደለም ፊቱን አያዞርም፡፡አምሃራ ይህን ክብር ቢያገኝም የክፋት መንፍስ አገልጋዮች እንዳሉበት  ቁጥሩን  ቤት ይቁጠረው ብየ ነው፡፡ክፋትና ሃጢያትን በአጥንታቸው እንደ ቂቤ ያስገቧት ወደ አውሬነት የሚቀየሩ ሁሉ እንዳሉ ልብ ይሏል፡፡ እንደ አጠቃላይ ግን በሁሉም አለም ”ወንድ ያልቃል ሴቶች ግን አስከሬንና መሳሪያ ሰብሳቢ ይሆናሉ፡፡በዚህን ዘመን “ከሄደ የቆመ፡ከቆመ የተቀመጠ፡ይሻላል”፤የፀለየ ንፁህ ዉሃና ቆሎ የቆረጠመ ይድናል፡፡መሳሪያም ከእንግድህ በኋላ በምድራችን እንዳይኖር ከምድረ ገፅ ይወገዳል፡፡እንኳን ሚሳኤል ጩቤ እንኳን አይኖርም፡፡ይህ መቅስፍት ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለታላላቆቹ ሃገሮች ዘግናኝ ገፅታ ይኖረዋል፡፡ምናልባት እነሱ 3ተኛው የአለም ጦርነት ሊሉት ይችላሉ፡፡በትንቢት በኋለኛው ዘመን በፉጭት ይጠራራሉ የተባለው ቃል አሁን በግልፅ ጥፋቱ ያስረዳቸዋል፡፡በስልክ ፤ፌስ ቡክ፤ኢሞ፤ቫይበር……ወዘተ ይጠራራሉ፡፡ግን ሁሉም አይድን፡፡ይህ ትንሳኤ የሞተ የሚነሳበት ነበር(በእርግጥ ንጉሱና የበቁ አባቶች የሞተ ያስነሳሉ ግን ለማለት የፈለኩት ሳይሞቱ ለሞቱት የአዳም ልጆች ሁሉ፤ ሃይማኖቴ፤ሃገሬ)፡፡ነገር ግን ለሃያላኖቹ አሸናፊም ተሸናፊም በወደቁበት ቦታ ሰጋቸው ምድር ላይ ነፍሳቸው ሲኦል ላይ ይከትማል፡፡

2ኛ. ረሃብ ነው፡፡የአለምም ሆነ የሃገራችን ኢኮኖሚ በከፍተኛ ደረጃ ስለሚወድቅ፤አምርቼ በሰላም ሰርች እበላለሁ ብሎ የሚያስብም ስለሌለ የሚበላ የለም፡፡ዝናብ የሚቀርበት ዘመን አለ፡፡እጅግ ብዙ ህዝብ በረሃብ ያልቃል፡፡ይህ ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካዊያኖችም የተመደበላቸው በጀታቸው ነው፡፡አሜሪካ፤አውሮፓ፤አረብና ኤሲያማ ጦረኞች ናቸው አሉ!!!!ከዚህ አስከፊ የጦር፤ድርቅና የረሃብ ዘመን በኃላ ቅዱስ ሳልሳቂ ቴዎድሮስ ለሰባት ቀን ደመና በሌለበት በጠራ ሰማይ ለሰባት ቀን ዝናብ ያዘንባል ወዲያውኑ እንደነ አቡነ ገሪማ ለሰርክ መስዕዋት ይደርሳል፡፡የምድር በረከትም ከዚህ ይጀምራል፤ከዚያ በፊት ግን ሁሉም ለጦር ግንባር ቅድሚያ ሰለሚሰጥና የምርም ለማረስ እድሉ ስለሌለው እህል አይኖርም፤ ቢኖርም መሰረተ ልማቶች (infrastructure) አገልግሎት ስለማይሰጡ ሰዉ በረሃብ ያልቃል፡፡ይህም የሆነው በጥፋታችን እንጅ አምላካችንስ ጨካኝ አልነበረም፡፡የሚወዳቸውን ግን በጥበቡ ይመግባቸዋል፡፡መመገብ ብቻ ሳይሆን ከእረሃብና ከወረርሽን(በሽታ) የሚከላከሉበትን የአመጋገብ ስርዓት በቅርቡ በልዑል ባለሟሎች በኩል ይፋ የሚደረግ ይመስለኛል፡፡እነሱን ግን እንዳትቃወሙ ተጠንቀቁ ሙሉ ሃይልና ስልጣን ተሰጥቷቸው ነው የሚመጡት፤ለሰነፎች ግን መብታችሁ ነው እሳት የሚተፉ ይወጡላችኋል ምድረ እርጉዝ ሁሉ!

3ተኛ.ገዳይ በሽታ ነው፡፡ከኢቦላ የሚበልጥ በፍጥነት የሚዛመት አደገኛ ወረርሽኝ የሚከሰት ሲሆን አስከሬኑን እንኳን ለመቅበር አያስደፍርም፡፡ጤነኛ ነኝ ብሎ አስከሬኑን ሲሸከም እሱም አብሮ እስከወዳኛው ያሸልባል የሚቀብረውም የለ፡፡እነኝህ 3ቱ ለሃገራችን ቢሆኑም ለአለም ግን እነኝህን ጨምሮ  አይነቱ ብዙ ነው ዘርዝረን አንጨርሰውም፡፡ቁጣውን፤መዓቱን የሚያሳያቸው ይሆናል፡፡አንድት መንግስት፤ አንድት አገዛዝ፤አንድት ቋንቋና  አንድት ሃይማኖት ይችውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት በአለም ላይ ትዝረጋለች፡፡ዛሬ አለም እንደ ኖህ ዘመን ዳንኪራውን ከበሮውን ከፍ አድርገህ ምታ የሚልበት ሰዓት ነው፡፡ያገባሉ፤ይጋባሉ፤ምንም እንኳን በንፍር ውሀ ድጋሚ ባይጠፉም ውሃዉ ከእግራቸው ሆኖ ሳለ ወደ ላይ ወደ ጉልበታቸውና አንገታቸው እስኪደርስ ድረስ ከፍ አድርገህ ምታ እያሉ ነው፡፡እግዚያብሄር ግን የድያብሎስን አሻራ ፤ጋጋታ፤ፈጠራና ፍልስፍና ሁሉ ይደመስሰዋል፡፡አዎ እግዚያብሄር ይነሳል፡፡እግዚያብሄር ከቴማን፤ቅዱሱም ከፋራን ተራራ ይመጣል፡፡ትንቢተ እንባቆም ዛሬ በእግር ኳስ የሚመለከው ማን ነው?ፖለቲከኞች ማንን ያመልካሉ?የእውቀት ምንጫቸው ማን ነው?የሃብት ምንጫቸው ማን ነው?ሃብታቸው ግርማ ሞገሳቸው ማን ነው?እሱ ብርያል የተባለው የጨለማው ገዠ አይደለምን???ለእኛስ ተስፋችን ማን ነው?ዉበታችን ማን ነው?ሰላማችን ማን ነው?ባለሚሳኤሎቹ በአንድ ቀን ጭጭ እንዳያደርጉን ያገደልን ማን ነው? ልጆቼ የሚለን ማን ነው?በስስት የሚያየን ማን ነው?አይኖቹ ለሰኮንድ ከእኛ የማይለየው አለምን በእጁ የጨበጠ፤ዉሃን በእፍኙ የሚለካ ከበርባኖስ እስከ አርያም ከዚም በላይ ያሉትን ፍጥረቶች የፈጠረ አለም ሳይፈጠር ሰማይና ምድር ሣይመሰረቱ በአማናዊ ባህሪው በአማናዊ ህዋ ይኖር የነበረ አሁንም የሚኖር አለምንም አሳልፎ የሚኖር የፍጥረታት ጌታ እሱ አብ ወልድ  መንፈስ ቅዱስ አንዱ አምላክ አይደለምን፡፡አብ የወልድና የመንፈስ ቅዱስ ልባቸው ነው፡ወልድ የአብና የመንፈስ ቅዱስ ቃላቸው ነው፡ መንፈስ ቅዱስም የአብና የወልድ እስትንፋሳቸው ነው፡፡እነኝህ ስላሴዎች ከፍ ዝቅ ደሀራይና ቀዳማይ የለባቸውም፡፡የሚሾም የሚሽር፤የሚያበለፅግ የሚያደኸይ፤የሚያሳምም የሚፈውስ፤የሚያድን የሚገድል፤እንደ ሙሴ ግርማ ሞገስ የሚሰጥ የሚነሳ ለብቻው ጥበብ ያለው እሱ ቅድስት ስላሴ ብቻ ነው፡፡ስላሴ የሃይማኖት በር ነውና በእነኝህ በስላሴወች ያመነ የህይወትን ፍሬ የህይወትን ዉሃ ያገኛል፡፡ለአማፅያን ደገሞ ወደ ቀደመ ነገሬ ልመልሳቸው፤ እነዚህ መቅሰፍቶች የበጉ ማህተም ያለባቸውን እየለዩ ሁሉንም ያፀዳሉ፡፡በዚህም በሀገራችን ከሶስት ሰው አንድ ሰው ቢቀር ነው፡፡በአለም ግን ከአስር ሰው አንድ ሰው የሚቀር ይሆናል፡፡እነኝህም ሃይማኖት እንኳን ባይኖራቸው ባላችው በጎነት በሃይማኖታቸው ሳይሆን በህገ ልቦና እሱ በሚያውቀው ይዳኛቸዋል፤ያወጣቸዋል፡፡በግልፅ አማርኛ ሃይማኖቱን ከምግባር የያዘ ቆሎ የቆረጠመ፤የፀለየ እና ንፁህ ዉሃ የጠጣ ይድናል፤እጅግ ጥቂት የሚሆኑ አህዛብ ደግሞ ባላቸው በጎነት በህገ ልቦና ይዳኛሉ ይድናሉ ማለት ነው፡፡ይህም የሟቹን ሞቶ የማይወደው አዛኝ ጌታችን የሚድኑበትን እድል ሲያሰፋላቸው ነው፡፡

ስላሴ ሆይ  
አቤቱ ድምፅህን ሰምቼ ፈራሁ፤ 
አቤቱ በአመታት መካከል ስራህን ፈፅም፤ 
በአመታት መካከል አስታውቃት፤
 በአመት ጊዜ ምህረትህን አስብ፡፡ 
እግዚያብሄር ከቴማን፤ 
ቅዱሱም ከፋራን ተራራ ይመጣል፡፡ 
ክብሩ ሰማያትን ከድኟል፤ 
ምስጋናውም ምድርን መልቷል፤ ፀዳሉም እንደ ብርሃን ነው፤ 

ጨረር ከእጁ ወጥቷል፤ 
ሃይሉም በዚያ ተሰዉፘል፤ 
ቸነፈር በፊቱ ይሄዳል፤ 
የእሳትም ነበልባል ከእግሩ ይወጣል፤ 
በቆመም ጊዜ ምድርን አወካት፤ 
በተመለከተም ጊዜ አህዛብን አናወጠ፡፡ 
የዘላለም ተራሮች ተንቀጠቀጡ፤ 
የዘላለም ኮረብቶች ቀለጡ፤ 
መንገዱ ከዘላለም ነው፤ 
የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ፤ 
የምድያም አገር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ፡፡
በዉኑ እግዚያብሄር በወንዞች ላይ ተቆጥቷልን? 
በፈረሶችህና በማዳንህ ሰረገሎች ላይ ተቀምጠሃልና፤
 ቁጣህ በወንዞች መዓትህም በባህር ላይ ነውን? በቃልህ እንደማልህ፤ 
መቅሰፍትህን አወጣህ ቀስትህንም አነጣጠርህ፤ 
ምድርን ሰንጥቀህ ፈሳሾችህን አወጣህ፤ 
ተራሮች አንተን አይተው ተጨነቁ፤ የዉሃ ሞገድ አልፏል፡፡ 
ቀላዩም ድምፁን ሰጥቷል፡፡ 
እጁንም ወደላይ አንስቷል፤ ፍላፆችህ ከወጡበት የተነሳ፡፡ 
ከሚንቦገቦገውም ከጦርህ ፀዳል የተነሳ፤ 
ፀሃይና ጨረቃ በመኖሪያቸው ቆሙ፡፡ የነብዩ የእንባቆም ፀሎት
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment