ግብጽ ስትረጋጋ ኢትዮጵያ ትናወጣለች፤ ኢትዮጵያ ስትረጋጋ ግብጽ ትናወጣለች!

ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ

“ቤኒሻንጉል” ተብሎ በሚጠራው ሌላው ሰው ሰራሽ አፓርታይዳዊ ክልል በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለው ጽንፈኛ ተግባር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከፍየሏ ግብጽ ጋር የተያያዘ ነው። ገና ከመሠረቱ ይህ ቤኒ ሻንጉል የተባለው ክልል ሲቋቋም ይህን መሰል ችግር እንደሚፈጠር አስቀድመው በማወቅ ነው። ከሃያ ሰባት ዓመታት በፊት ሉሲፈራውያኑ የክልሎችን ካርታ ለህዋሓት እና ኦነግ መንግስት ሲያስረክቧቸው አሁን በሀገራችን እየታየ ያለው ቀውስ እንደሚመጣ ሰለሚያውቁ ነው። ይህ አሁን ግልጽ ነው!የሕዳሴ ግድቡ ሆን ተብሎ ቤኒ ሻንጉል በተባለው ክልል እንዲገነባ መደረጉ አንድ ቀን፡ በጎቹን ተዋሕዶ ኢትዮጵያውያንን ከክልሉ መንጥረው ካስወጡ በኋላ በቀላሉ ሊቆጣጠሯቸው የሚችሏቸውንና የአረብ መጋረጃ በመልበስ ላይ የሚገኘውን “የቤኒ ሻንጉል ጉሙዝ ሕዝብን” ወደ ሱዳን በመጠቅለል በግብጽና አረቦች እጅ ለማስገባት በመሻት ነው። ኦሮሚያ በተባለው ክልል ደሀው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥሮ ግሮ ያጠራቀመውን ገንዘብ የዋቄዮ አላህ ልጆች እንደሚዘርፉት፤ በቤኒ ሻንጉልም ኢትዮጵያውያን ገንዘባቸውን አሰባሰበው እየገነቡት ያሉትን የሕዳሴውን ግድብ እነ ግብጽ ለመውረስ በመዘጋጀት ላይ ናቸው። ለፍየሏ ግብጽ የግዮንን ውሃ ለዘመናት በነጻ መጠጣት ብቻ በቂ ስላልሆን፣ የኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ደም መጠጣት፣ ኩላሊቶቻቸውን መስረቅ ብቻ በቂ ስላልሆነ፡ አሁን ኢትዮጵያውያን ላባቸውን አንጠፍጥፈው ባጠራቀሙት ገንዘብ የገነቡትን ግድብም በቁጥጥራቸው ሥር ለማድረግ ተነሳስተዋል። ልክ በደርግ ጊዜ የሉሲፈራውያኑ ተቋም ሲ.አይ.ኤ (CIA) የኢትዮጵያን ሠራዊት ብትንትኑን ለማውጣት የጦር መሪዎችን እንዲያስወግድና እንዲገድል ኮሎኔል መንግስቱን እንዳዘዙት፤ በሕማማት ሳምንት ሆን ተብሎ (የቤኒ ሻንጉሉ ዕልቂት ታቅዷልና)ከኢትዮጵያ ሹልክ በማለት ወደ ቻይና ሄዶ የነበረውን ኮሎኔል አብዮት አሕመድንም በተመሳሳይ መልክ ሠራዊታችንን እንዲያዳክም፣ ልምዱ ያላቸውን የጦር መሪዎችን እንዲያባርርና በምትካቸው ሴቶችን/እንደ ሴት የሆኑትንና በቀላሉ እጅ የሚሰጡትን ፀረ–ኢትዮጵያውያንን እንዲያስቀምጥ ተደርጓል። ደርግ ሥልጣን ላይ ሲወጣና አሁን በአገራችን እየታየ ያለው ሁኔታ በጣም ተመሳሳይ ነው። ግብጽ በአሁን ሰዓት ወደ ቤኒ ሻንጉል በቀናት ውስጥ ሰተት ብላ በመግባት የሕዳሴውን ግድብ መቆጣጠር ትችላለች። [ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ ፲፱፥] ፩ ስለ ግብጽ የተነገረ ሸክም። እነሆ፥ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና እይበረረ ወደ ግብጽ ይመጣል፤ የግብጽም ጣዖታት በፊቱ ይርዳሉ፥ የግብጽም ልብ በውስጥዋ ይቀልጣል። ፪ ግብጻውያንን በግብጻውያን ላይ አስነሣለሁ፤ ወንድምም ወንድሙን፥ ሰውም ባልንጀራውን፥ ከተማም ከተማን፥ መንግሥትም መንግሥትን ይወጋል። ፫ የግብጽም መንፈስ በውስጥዋ ባዶ ይሆናል፥ ምክራቸውንም አጠፋለሁ፤ እነርሱም ጣዖቶቻቸውን በድግምት የሚጠነቍሉትንም መናፍስት ጠሪዎቻቸውንም ጠንቋዮቻቸውንም ይጠይቃሉ። ፬ ግብጻውያንንም በጨካኝ ጌታ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ ጨካኝ ንጉሥም ይገዛቸዋል ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። ፭ ውኆችም ከባሕር ይደርቃሉ፥ ወንዙም ያንሳል ደረቅም ይሆናል። ፮ ወንዞቹም ይገማሉ፥ የግብጽም መስኖች ያንሳሉ ይደርቃሉም፤ ደንገልና ቄጤማ ይጠወልጋሉ። ፯ በዓባይ ወንዝ ዳር ያለው መስክ በዓባይም ወንዝ አጠገብ የተዘራ እርሻ ሁሉ ይደርቃል፥ ይበተንማል፥ አይገኝምም። ፰ ዓሣ አጥማጆቹ ያዝናሉ፥ በዓባይም ወንዝ መቃጥን የሚጥሉት ሁሉ ያለቅሳሉ፥ በውኆችም ላይ መረብ የሚዘረጉት ይዝላሉ። ፱ የተበጠረውንም የተልባ እግር የሚሠሩ፥ ነጩንም ልብስ የሚሠሩ ሸማኔዎች ያፍራሉ። ፲ ደገፋዎችዋም ሁሉ ይሰባበራሉ፥ የደመወዘኞችም ነፍስ ትተክዛለች። ፲፩ የጣኔዎስ አለቆች ፍጹም ሰነፎች ናቸው፤ ፈርዖንን የሚመክሩ ጥበበኞች ምክራቸው ድንቍርና ሆነች። ፈርዖንን። እኛ የጥበበኞች ልጆች የቀደሙም ነገሥታት ልጆች ነን እንዴት ትሉታላችሁ? ፲፪ አሁንሳ ጥበበኞችህ የት አሉ? አሁን ይንገሩህ፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በግብጽ ላይ ያሰበውን ይወቁ። ፲፫ የጣኔዎስ አለቆች ሰነፎች ሆነዋል፥ የሜምፎስም አለቆች ተሸንግለዋል፤ የነገዶችዋ የማዕዘን ድንጋዮች የሆኑ ግብጽን አሳቱ። ፲፬ እግዚአብሔር የጠማምነትን መንፈስ በውስጥዋ ደባልቆአል፤ ሰካር በትፋቱ እንዲስት እንዲሁ ግብጽን በሥራዋ ሁሉ አሳቱ። ፲፭ ራስ ወይም ጅራት የሰሌን ቅርንጫፍ ወይም እንግጫ ቢሆን ሊሠራ የሚችል ሥራ ለግብጽ አይሆንላትም። ፲፮ በዚያ ቀን ግብጻውያን እንደ ሴቶች ይሆናሉ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ ከሚያንቀሳቅሳት ከእጁ መንቀሳቀስ የተነሣ ይሸበራሉ ይፈሩማል። ፲፯ የይሁዳም ምድር ግብጽን የምታስደነግጥ ትሆናለች፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከመከረባት ምክር የተነሣ ወሬዋን የሚሰማ ሁሉ ይፈራል። ፲፰ በዚያ ቀን በግብጽ ምድር በከነዓን ቋንቋ የሚናገሩ፥ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔርም የሚምሉ አምስት ከተሞች ይሆናሉ፤ ከነዚህም አንዲቱ የጥፋት ከተማ ተብላ ትጠራለች። ፲፱ በዚያ ቀን በግብጽ ምድር መካከል ለእግዚአብሔር መሠዊያ፥ በዳርቻዋም ለእግዚአብሔር ዓምድ ይሆናል። ፳ ይህም ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር በግብጽ ምድር ምልክትና ምስክር ይሆናል፤ ከሚያስጨንቁአቸው የተነሣ ወደ እግዚአብሔር ይጮኻሉና፥ እርሱም መድኃኒትንና ኃያልን ሰድዶ ያድናቸዋልና። ፳፩ በዚያም ቀን እግዚአብሔር በግብጽ የታወቀ ይሆናል፥ ግብጽAውያንም እግዚአብሔርን ያውቃሉ፤ በመሥዋዕትና በቍርባን ያመልካሉ፥ ለእግዚአብሔርም ስእለት ይሳላሉ ይፈጽሙትማል። ፳፪ እግዚአብሔርም ግብጽን ይመታታል፤ ይመታታል ይፈውሳታልም፤ ወደ እግዚአብሔርም ይመለሳሉ እርሱም ይለመናቸዋል ይፈውሳቸውማል። ፳፫ በዚያ ቀን ከግብጽ ወደ አሦር መንገድ ይሆናል፥ አሦራዊውም ወደ ግብጽ፥ ግብጻዊውም ወደ አሦር ይገባል፤ ግብጻውያንም ከአሦራውያን ጋር ይሰግዳሉ። ፳፬፤፳፭ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። ሕዝቤ ግብጽ፥ የእጄም ሥራ አሦር፥ ርስቴም እስራኤል የተባረከ ይሁን ብሎ ይባርካቸዋልና በዚያ ቀን እስራኤል ለግብጽና ለአሦር ሦስተኛ ይሆናል፥ በምድርም መካከል በረከት ይሆናል።
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment