የፈውስ ምልክቱ እባብ ለኢትዮጵያ!!


✍ ይታገሡ በቀለ | ኢትዮጵያ አውታር | ሰላቢ እጆች


መድሃኒታችን ክርስቶስን መፈለጋችን ያስከፈለን ዋጋ!!
የሰለሞናዊ ግብጻዊው አገዛዝ ማብቃት!!
የኢትዮጵያ ጊዜ!!

አማራ ለሦስት ሺህ ዓመታት በኢትዮጵያ ነግሶ እንደቆየ እና የስልጣን ጥመኛ እንደሆነ የሚነገረው ሃሰት ነው። ከኢትዮጵያ ነገስታት ከአጼ ቴዎድሮስ ውጪ አማራ የሆነ የለም፤ ሁሉም ከይሁዳ ወገን የሆኑ ሴማውያን ናቸው።

አማራ ሌሎችን ወደ ስልጣን በማምጣት ነው የሚታወቀው፤ ላሊበላን፣ ይኩኖ አምላክን...የይሁዳን ወገን ሴማውያንን ደግፎ ሲሾም መኖሩ የታወቀ ነው። አማራ አይሁድን የሚወድ Jew Sentiment ያለው ብቸኛ ብሔር ይመስላል፤ አማራ ሴሜቲኮችን ደገፈ እንጂ እንደ ኦሮሞ ኩሸቲክ የሆነ ነው፤ አማራም ኦሮሞም ከደሸት ነው የተገኙት።

ኦሮሞ ከቀዳማዊ ምኒልክ ጀምሮ ከሴማውያኑ ሰለሞናውያን ጋር ስምም አይደለም።

ንግስት ሳባ የመጨረሻዋ የኩሽ ነገስት ናት የአክሱም(አ-ክሹ/ኩሽ-ም) ስልጣኔም የኩሾች ነው።

ንግስተ ሳባ የሰለሞንን ጥበብ በአጋጣሚ አየች እንጂ ዋና አላማዋ ከእሥራኤል ይመጣል የተባለው  ክርስቶስ መጥቶ እንደሆነ ሰለሞንም መሲሁ እንደሆነ ለማረጋገጥ ነው ወደ እሥራኤል የተጓዘችው።

በሰለሞናዊ ነገስታትና በግብጽ ጳጳሳት መተዳደር ከመጀመራችን በፊት፤ ንግስናን ከክህነት ያዋኻደ ከመልከጸዴቅ የተገኘ ከሰለሞናውያኑ የተሻለ ሥርወ መንግስት ነበረን።

ሰለሞናዊው-ግብጻዊ አሥተዳደር ሲያበቃ...ወደ ደሸት..መልከ ጸዴቅ... ኢትዮጵ ...እሥያኤል...ሳባ ሥርወ መንግስት እንመለሳለን ማለት ነው...ይህም የኢትዮጵያ ጊዜ ይሆናል፤ የእሥራኤል-ግብጽ አገዛዝ አብቅቷል።

ሃኪም አበበች "ኢትዮጵያን ጣጣ ውስጥ ያስገቧት ሴሜቲኮቹ ናቸው" ሲሉ ተደምጠዋል፤ #ፍቅሬ_ቶሎሳ የኦሮሞና አማራን ወንድማማችነት መስክረዋል፤ እውነተኛው ታሪክ በቀዳማዊ ምኒልክ እንዲጠፋ ተደርጎ ነበር። የተሰወረውን መረጃ ያቀበሉን ደግሞ መሪራስ አማን በላይ የተባሉ ድንቅ ግለሰብ ናቸው።

ሰለሞናውያኑ የኩሾቹን ታሪክ ብቻ ሳይሆን በወንድሞቻቸው በዛግዌ ነገስታት ጊዜ የተጻፉ ድርሳናትንም አስወግደዋል፤ ዛጉዌዎች ላሊበላን፣ ይምርሃነ ክርስቶስን የመሣሠሉ ቅዱስ-ንጉሶች በማፍራታቸው ክህነትን ከንግስና ያስተባበረው የመልከ ጸዴቅ ኢትዮጵያዊ አሠራርን የተቀበሉ ይመስላል፤ ጻድቁ አባታችን ተክለ ሃይማኖት ይኩኖ አምላክን ወደ ስልጣን ሲያመጡ፤ አማራም ዛጉዌንም ሰለሞናውያንን ሲደግፍ የቆየበት ምክንያት ይኖራል፤ አሁን ግን ጊዜው ያንን አልፈቀደም።

እንግዲህ የክርስቶስን መምጣት የምንጠባበቅ ታላቅ ህዝቦች ነበርን፤ ንግስት ሳባ የክርስቶስን መምጣት ለማረጋገጥ ወደ እሥራኤል ብትኼድ ከሰለሞን አርግዛ ተመለሰች፤ የተወለደው ልጅ ምኒልክም የከመልከጸዴቅ፣ ከደሸት የተገኘውን ኢትዮጵያዊ ሥርወ መንግስት አውድማው፤ ክርስቶስን ፍለጋችን ያስከፈለን ሌላ ዋጋ ደግሞ ከግብጽ ጳጳሳት ለማግኘት ብለን መገበራችንና የግብጽ ነገስታት ሴራ ሰለባ መሆናችን ነው።

ኢትዮጵያ ግብጻዊ ጳጳሳትንና አይሁዳዊ ነገስታትን በፍቃዷ ስትሾም የኖረች ነጻ ሃገር ስትሆን፤ እሥራኤልና ግብጽ ግን በሁሉም ሃያላን መንግስታት ሊባል በሚችል መልኩ ቅኝ የተገዙ ነበሩ።

#ኢትዮጵያ ክርስቶስን ፍለጋ ዋጋ ስትከፈል እሥራኤል ግን ክዳዋለች፤ እሥራኤል አሁን ድረስ ጸረ-ሃይማኖት ሳይንቲስቶችን ስትፈለፍል፤ ኢትዮጵያ በርካታ ቅዱሳንን አፍርታለች። እንግዲህ ክርስቶስን ፍለጋና እንግዳ አክባሪነት ይህንን ዋጋ አስከፍለውናል፤ ያተረፈነው ነገር እንደተጠበቀ ሆኖ።

እሥራኤል ከኢትዮጵያ ያላት ብልጫ ምንድነው!?

እሥራኤል እንደ ኢትዮጵያ ምንጭ ናትን!?

#አዳም ኢትዮጵያ ውስጥ እንጂ እሥራኤል ውስጥ ላለመፈጠሩ ኢትዮጵያ የሰው ዘር ምንጭ መሆኗን የሚያስረዳው ሳይንስ ምስክር ይሆናል። አዳም...ኖህ...ኢትዮጵያ ውስጥ ለመኖራቸው ማረጋገጫዎች ተገኝተዋል።

እሥራኤል የሚለው ሥያሜ ራሱ" አይሲስ"ና" ራ"ከተባሉ የግብጽ አማልዕክት የተቀዳ ነው፤ ካባላህ የሚባለው እውቀቷ የግብጽ ነው፤ መጽሃፍ ቅዱስም ከኢትዮጵያ የተቀዳ ነው።

ክርስቶስን በማስገኘት ነው!?

ታዲያ ከነቢያቶቿ እንኳ አልቆጠረችውም፤ ሙስሊሞች የሰጡትን ቦታ እንኳ አልሰጠችውም።

በእመቤታችን ምክንያት ነውን!?

#አይሁድ ድንግል ማርያምን ከነ ልጇ ማሳደዳቸውና፤ ግብጽ የነበረው ኢትዮጵያዊ ንጉስ እንደተቀበላቸው ታሪክ አስቀምጦታል። አሁንም ከእሥራኤል ይልቅ የእመቤታችን ርስት ኢትዮጵያ መሆኗ የታመነ ነው። ዛሬም ስሟ የሚጠራው እሥራኤል ውስጥ ሳይሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ነው።

በተወዳጅነት ነው!?

ኢትዮጵያ በሁሉ ዘንድ ምስጉን፤ አይሁድ በሁሉ የተወገዙ ናቸው፤ እንዲያውም የአይሁድ ፍቅር ያላችሁ ይህቺው ተዓምረኛዋ ኢትዮጵያ ናት።

በቀዳሚነት ነው!?

አብርሃምን የቀባው ኢትዮጵያዊው መልከጼዴቅ፣ ሙሴን ያስተማረው ኢትዮጵያዊው ዮቶር እንዲያውም ሙሴ ስልጣን ያገኘው ኢትዮጵያዊቷን በማግባቱ ነበር።

መጽሐፍ ቅዱስን ስለሰጡን ነው!?

የኢዮብ፣ የኢሳይያስ፣ የኼኖክ፣ የዘፍጥረት ...ታሪኮች የኢትዮጵያ እንደሆነ ተረጋግጧል፤ ይህንንም የባለቤትነት ታሪክ የአይሁድ ካህናት እንዳጠፉት ታውቋል።

በጀግንነት ነውን!?

እሥራኤልን ያልወረረ ልዕለ ሃያል አልነበረም፤ ኢትዮጵያን የገዛ አንድም ልዕለ ሃያል ሃገር ግን አልነበረም።

አሁን ጊዜው የአይሁድ ይመስላል፤ በዓለም ላይ በሁሉም ነገር ቁንጮነቱን ይዘውታል፤ ግን ታሪኩ መቀየር ጀምሯል፦
ኢትዮጵያውያን ቀዳሚና መሪነታቸውን ታሪካቸውን በሚመጥን ሁኔታ መልሰው ይቀዳጃሉ። በቀዳማዊ ምኒልክ የተደመሠሠው ኢትዮጵያዊነትም ተመልሶ ይለመልማል፤ በሴማውያኑ የጠፋው ታሪክም ይወሳል ይነሳል።

የእሥራኤል-ግብጽ አገዛዝ አብቅቷል፤ ኢትዮጵያዊው ሥርወ መንግስት ዘእምነገደ ደሸት ይቀጥላል፤ ይህም የኢትዮጵያን ችግሮች የሚፈታ ይሆናል።

የዘረደሸት አርማ ሳባውያን ነገስታት ሲጠቀሙበት የነበረው የዘንዶና የሰው ቅርጽ ያለው ኮከብ(መስቀል) ነበር፤ ይህ የይሁዳ አንበሳን የሚተካ ነው፤ ዘንዶው የሚመለክ ሳይሆን መጽሃፍ ቅዱሳዊ ትርጉም ያለው ነው፦ሙሴ የዘንዶ ቅርጽ በበረሃ ሰቅሎ ያንን ያዩት የተፈወሱበት፤አሁንም የፈውስ ምልክት የሆነው፤ ጳጳሳት በሚይዙት ዘንግ ላይ ያለውን የፈውስ ትርጓሜ የሚይዝ ነው(ብዙ መድሃኒቶች ከእባብ ከጊንጥ እንዲሁም ከሌሎች መርዛማ ነፍሳት መርዞች እንደሚሰሩ ይታወቃል)ኢትዮጵያ፦ የምጣኔ፣የፈውስ ምድር፤መዛባትን መቃወስን ጽንፈኝነትን የምትሽር፣ ተቃራኒዎች የሚታረቁባት፣ዋናው ጤና የምትል ብቸኛ ሃገር ናትና የፈውስ ምልክቱ እባብ ይገልጻታል። ይህም ከመጥፎም ጥሩ፣ ከማይበጅ የሚጠቅም የመገኘቱ ምሳሌ ነው።

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment