ዘረ-ደሸት | በሚስጥር የሚንቀሳቀሱት ጥንት ኢትዮጵያዊያን የመሰረቱት የሊቃውንት ስብስብ

ሕዋሳትን ማደስ | ዕፀ ተሐድሶ

አሁን ባለችው ዓለም  ያልተሰራ ነገር የለም።  እግዚአብሔር ለሰው ልጆች  በሰጠው  ንቃተ ህሊና ተጠቀሞ የሰው ልጂ  እጂግ ለማመን የሚከብድ የምርምር  ስራወች  ምድራችን ላይ እየተሰራ ነው። ይህ ሁሉ የቴክኖሎጂ  ምጠቅት እያለ የሰውን ልጂ ማከናወን የተሳነው አንድ ነገር አለ Cell (ህዋሰትን) ማደስ አለመቻል።

አለም በሰፊው ከሚመራመርባቸው ታላላቅ ምርምሮች ዋናው የሰውን ልጅ ህዋሳት አንዳያረጁ ራሳቸውን እንዲተኩ ማስቻል ሲሆን ይህም እውን ከሆነ የሰው ልጅ ሁሌም ጠናካራ ሁኖ በሞት ላይ ድል በማድረግ ለበርካታ ዓመታት መኖር ማስቻል ነው።

ዘረ ደሸት የሚባል ጥንት ኢትዮጵያውያን የመሰረቱት የሊቃውነት ስብስብ አለ።

በእርግጥ አሁን ላይ ይህ ዘረ ደሸት በሚስጥር ከሚንቀሳቀሱ ሚስጥራዊ ማህበር አንዱ እና እውነተኛው የኖህን እውቀትና ጥበብ እንደ ዘር ውርስ እየተወራረሱ ለበርካታ ሺ አመታት  ጠበቀው ካቆዩት ሚስጥራዊ ማህበራት አንዱ ነው።

በዚህ ማህበር  በርካታ ባህላዊ ምርምሮችን ይሰራሉ። ከእነዚህ  ውስጥ አንዱ እና አለም በሰፊው ከሚፈልገው ጥበብ ዕጸ ተሐድሶ የተባለ ወይም ህዋሳትን በማደስ የሰው ልጅ ለበርካታ አመታት ሳያረጁ  መኖር  ማስቻል ነው። እንደሚታወቀው  በየፋርማሲው  የሚሸጡ መዳህኒቶች ዋና ግባዕታቸው  የተለየዩ ሃይል ያላቸው አጽዋቶች በላብራቶሪ ዳብርው  ነው። እንደ ዘረ ደሸት ምርመር ከሆነ ዕጸ-ተሐድሶ በመባል የሚታወቁና ለህክምና አገልግሎት የሚውሉ በርከት ያሉ እጸዋት አሉ! #ለምሳሌ እጸ መና፣ እጸ መንስኤ፣ እጸ ስግው፣ እጸ ሶባ፣ እጸ በሃ እና መሰል እጸዋትን መጥቀስ የምንችል ሲሆን እነዚህ እጸዋት የተዳከሙ ሴሎችን የማከም፣ የማደስና የማብዛት ታላቅ ኃይል ስላላቸው በጥቅሉ እጸ ተሐድሶ በመባል እንደሚጠሩ የዘርፉ ሊቃውንት ይናገራሉ። ታዲያ እነዚህ ሊቃውንት የዘረ መል ህክምናን በዚሁ እጸ ተሐድሶ በተባለ እና በአባይ ሸለቆዎች ብቻ ሊበቅል በሚችል አንድ እጽ አማካኝነት ከገብስ ጋር በማደባለቅ በአጥሚት መልክ ለታካሚዎች እንደሚሰጡና እንደሚያክሙ ይናገራሉ።


Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment