ኤረርና ሣልሳዊ ቴዎድሮስ | አለም ላይ ካሉ ሚስጥራዊ ቦታወች አንዱ እና ዋናው ኤረር(የረር)

ስውሩ ከተማ

በተለያየ የዓለም ክፍል ከሚገኙ መንሳዊ ምስጢራዊ መዓከላት አንዱ ነው ቅዱሱ ኤረር ተራራ ከሰሜኑ መአከል የቅዱስ ያሬድ ቀመር ካለበት ከዳሽን ተራራ የሚገናኝበት መንገድ እንዳለ የሚነገር ሲሆን ኤረር የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ቅዱስ ቦታ ነው። በምሥራቅ ኢትዮጵያም ሌላ ምስጢራዊ ቦታ እንዳለ ይነገራል።

በህወኃት ዘመን በኤረር የሚገኙ ባህታውያን ግድያና ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል፦ ይህም የሆነው አንድ ባህታዊ የሣልሳዊ ቴዎድሮስን መምጣት በመናገራቸው ነበር።

አሜሪካ በሩዝቬልት ዘመን በኤረር ተራራ ላይ ዜጎቿን ለማስፈር ሞክራ ነበር።

በዚህ ቦታ እመቤታችን ጌታን ይዛ መጥታ እንደነበር ጌታም ከደቀመዛሙርቱ ጋር እንደነበረበት ይነገራል። አዳም ከገነት ያመጣቸው ቁሶች፣በራሪ ፈረሶች፣ የሙሴ በትር፣ የህይወት መጽሃፍ(መጽሃፈ ራዝኤል) እዚህ ይገኛሉ። ተራራው ውስጡ ከተማ ሲሆን ፒራሚዶችን እንደያዘም ይነገራል።

ከተለያዩ ሰማያትና ፕላኔቶች የሚመጡ እንግዶች እንዲሁም ከአለም ዙሪያ የተውጣጡ መንፈሳውያን ይገናኙበታል ይባላል።

ስለ መምጣቱ በራዕይ ሲኖዳና ሳቤላ፣በገድለ ፊቅጦር፣ በፍካሬ ኢየሱስ የተነገረለት ሣልሳዊ ቴዎድሮስ በየገዳማቱ ትምህርቱን አጠናቆ የሚሾምበት የሚባለው የሰማዕቱ የወታደሩ ቅዱስ ቴዎድሮስ ቤተክርስቲያን ኤረር ተራራ ላይ ይገኛል። የባዕታ ማርያም፣ የሥላሴና ሌሎች ቤተክርስቲያናትም የሚገኙ ሲሆ፤በርካታ ገዳማውያን ዋሻዎች ውስጥ በዓት ሰርተው ይኖራሉ፣ የአብርሃ አጽብሃ ቤተመንግስት ፍርስራሽም በዚህ አለ።

ሣልሳዊ ቴዎድሮስ፦ መልከ መልካምና ረጅም በጡቶቹ መሃል የመስቀል ንቅሳት ያለው ነው ተብሏል...የሮማን ሃይማኖት ሃሰትነት በማረጋግጥ ሥራውን ይጀምራል። በዘመኑ ጠማማ እንጨት እንኳ አይኖርም ተብሏል፤ 40 ዘመን በተድላ በደስታ ይገዛል፤ ከሱ በዃላ ሰባት ነገስታት ይነግሳሉ ሠባተኛው ከጌታ በፊት የሚመጣው ሃሳዊ መሲህ ነው። ከዚያ በዃላ ጌታ ይመጣል አለምም እንዳልነበረች ሆና ታልፋለች።

ታሪካዊና መንፈሳዊ የሆነው ይህ ቦታ ከደብረዘይት ጥቂት ኪሎሜትሮች ርቆ ይገኛል። የታሪኩን ያክል ታዋቂ አለመሆኑ ግርምትን ይፈጥራል።

ከአዲስ አበባ በስተደቡብ በኩል እንደሚገኝ የሚነገረው እጅግ ሚስጥራዊው ኤረር-ተራራ በጥቅሉ የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ቦታ እንደሆነ ድርሳናት ይናገራሉ። በእርግጥ ከዚህ ከፍ ብሎም ኤረር ተራራ የአዳም ርስት ሀገር ማዕከላዊ ቦታም እንደሆነ ይነገርለታል። ኢትዮጵያ የአዳም ርስት ሀገር በምንለው ምድር ወስጥ የምትገኝ እንደመሆኗ በአዳም ርስት ሀገር አሉ ተብለው ከሚነሱ ሰባት ታላላቅ ስፍራዎች መካካል ሶስቱ በኢትዮጵያ ይገኛሉ። እነዚህ ስፍራዎች የጥንታዊ ኢትዮጵያ ስልጣኔ መውጫ ለሆነው መንፈሳዊ ክፍል እንደ ማዕከል የሚያገለግሉ ነበሩ። ከእነዚህ ሶስት ስፍራዎች መካካል የመጀመሪያው በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ሲገኝ ሁለተኛው ምስራቁ የሀገራችን ክፍል ላይ የሚገኝ ሆኖ ሶስተኛው በመካከለኛው ኢትዮጵያ ላይ የሚገኝ መለኮታው ሃይል ያላቸው ቦታቸወች ናቸው።

እንግዲህ ኤረር ከእነዚህ ሶስት ስፍራዎች አንዱ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም የሁሉም ማዕከላዊ ቦታ ነው። ስለ ኤረር ተራራ በርካታ ንግርቶች (Myths) ይነገራሉ። ሆኖም ከእነዚህ ንግርቶች መካካል ትልቁን ስፍራ የሚይዘው አዳም ከገነት ሲመለስ ስድስቱን የክብር ዕቃዎች ከኤረር ማዕከላዊ ስፍራ አስቀምጦታል የሚለው ነው። ይህ በኤረር ተራራ ላይ የምናገኘው ማእከላዊ ስፍራ በተራራው መካካል ላይ የጉልላት ቅርጽ ይዞ ይታያል። ከዚህም ስፍራ አሁንም በርካታ መንፋሳዊ ሰዎች በስውር ይኖራሉ። በዚህ ስፍራ እንዚህን በርካታ የሆኑ መንፈሳዊ ሰዎችን ያሰባሰባቸው ይህ ማዕከላዊ የሆነው ስፍራ ነው። በዚህ ስፍራ ላይ በግልጽ እንዲሁም በስውር ኢትዮጵያኖች እንዲሁም ኢትዮጵያዊያን ያልሆኑ መንፋሳዊ ሰዎች ከአለም ዳርቻ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ተሰባስበው ይገኛሉ። ንግርቱ(Myth) እንደሚለው እውነት አዳም ይዟቸው የመጣው ስድስቱ የክብር ዕቃዎች እዚህ ይሆን የሚገኙት? ይህንን ጥያቄ ይህ ትውልድ ሊጠይቀው እና እውነቱን አነፍንፎ ሊያገኝ የሚጋባ ነው። የዚህ ሚስጥራዊ ኤረር ተራሮችን ለማወቅ የቅድስት ቤተክርስቲያናችንን ህንጻ አሰራር ማወቅ የግድ ይላል፤ በዚህም መሰረት የህንጻ ቤተክርስቲያናችንን ተምሳሌታዊ አወቃቀር ይዘን ኤረር ተራሮች ላይ ስንሄድ ተራራው ሁለት ክፍሎችን ይዞ እናገኘዋለን፤ የመጀመሪያው ክፍል ከተራራው በላይ የሚገኘውና በአይን ሊታይ የሚችለው በሥጋ ባህሪ የሚመሰለው ክፍል ነው።

ሁለተኛው የተራራው ክፍል የውስጠኛው ስውር ከተማ ሲሆን ይሄውም በነፍስ ባህሪ የሚወከልው ነው፤ ወደዚህ ወደ ሁለተኛው ወይንም ወደ ውስጠኛው የተራራው ክፍል ለመግባትም ልክ እንደ ህንጻ ቤተክርስቲያናችን በአጠቃላይ ሦስት በሮችን ይዟል፤ የመጀመሪያው በር በምስራቁ አቅጣጫ የሚገኘውና ከተራራው በላይም የቅዱስ #ቶዎድሮስ ቤተክርስቲያን የሚገኝበት በር ነው፤ ሁለተኛው በሰሜናዊው የተራራው አቅጣጫ የሚገኘውና ከበላዩም በደን የተሸፈነው እንዲሁም የባህታ ለማርያም ቤተክርስቲያን የሚገኝበት ሲሆን ሦስተኛውና የመጨረሻው በር በደቡባዊው አቅጣጫ በኮራ ማርያም ቤተክርስቲያን በኩል ይገኛል። ወደዚህ #ስውር ከተማ በምስራቁ በር ከብሔረ ህያዋን ብሎም በምድር የበቁ ታላላቅ አባቶቻችን የሚጠቀሙበት በር ሲሆን የሰሜናዊውን በር ወንድ ነገስታት እስከ አሥራ ሦስተኛው ክ/ዘመን ድረስ ሲጠቀሙበት ኖረዋል፤ ይህንን በር ለዘመናት ሲናፈቅ የኖረውና የኢትዮጵያን ትንሳኤ ያመጣል ተብሎ የሚጠበቀውና የገዢነት ክብሩን ይዞ የተወለደው ካህኑ #ንጉሥ_ቶዎድሮስ ዳግም ይጠቀምበታል ተብሎም ይነገራል፤ ሦስተኛውን በር እና በደቡባዊው አቅጣጫ በኩል የሚገኘውን በር ሴት ነገስታት ሲጠቀሙበት እንደኖሩ። ይሄንን አቀማመጥ ወደ ህንጻ ቤተክርስቲያናችን ከ300 በላይ የሚሆኑ ዋሻወች እንዳሉና ከመላው አለም የመጡ ቅዱሳን መነኮሳት እግዚአብሄርን እያመሰገኑ እንደሚኖሩበት ይታመናል፡፡ #በአለም ካሉት 7ቱ ሚስጥራዊ ቦታወች 3ቱ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚገኙ ከሶስቱ አንዱም ኤረር ተራራ እንደሆን አየን፡፡ መላእክት ከእግዚአብሄር ዘንድ ሲላኩም ሆነ ለተልእኮ ሲወጡ እና ሲወርዱ ከሚያርፉባቸው 7ት ሚስጥራዊ እና ስውር ስፍራዎች አንዱ ነው።

ምስጢራዊው ስፍራ

√ ይህ ስፍራ በበርካታ የበቁ አባቶች የተከበበ ነው። እነኚህ አባቶች ከመንፈሳዊ ብቃታቸው የተነሳ የተሰወሩ ቅዱሳን ሲሆኑ ብዙሃኑ በአለማዊ የትምህርት ደረጃቸው ዶክተሮች፣ ኢንጀነሮች ፣ ፓይለቶች ወዘተ እንደሆኑ ይመሰከራል።

√ ይህ ስፍራ በጥንታዊ ዋሻዎች የተከበበ ነው። እነኚህ ዋሻዎች በተሰወሩ ጥንታዊ ቅርሶችና መፃህፍት የተመላ ሲሆን በደጉ ንጉስ ዘመን እንደሚገለጡ ይታመናል።

√ ይህ ስፍራ የኢትዮጵያ ትንሳኤን እውን እንደሚያደርግ የሚታመንበት የሀያሉ ንጉስ ቶዎድሮስ ቤተመንግስት የሚሰየምበት እንደሆነ ይታመናል።

√ ይህ ስፍራ ላይ በንጉስ ሳህለ ስላሴ ዘመን አንድ ቤተክርስትያን ተቆርቁሯል። በዚህ ቦታ ላይ የተቆረቆረው ቤተክርስትያን የሮማዊው ቅዱስ ሰማእት ቴዎድሮስ ነው። ቤተክርስትያኑ በቅዱስ ቴዎድሮስ ስም መሰየሙ ንጉሱ ቶዎድሮስ የሚነግስበት ስፍራ ስለሆነ እንደሆነ አለቃ አያሌው ታምሩ ባዘጋጁት የቅዱስ ቴዎድሮስ ገድል ላይ ተፅፏል።

ይህ ስፍራ ከደብረ ዘይት 13 ኪሜ ርቀት ላይ የሚገኘው የኤረር ቅዱስ ቴዎድሮስ ገዳም ነው።

በዚህ ስፍር ክርስቶስ በምድር ሳለ የተገለገለባቸው እቃዎች እቃዎች ይገኛሉ። እጅግ ጥብቅ ቦታም ነው!

ለአሁኑ ግን አዳም ከገነት ያመጣው የክብር ዕቃ ስለ ሶስተኛው የክብር እቃ #ገረረ_ሰረገላ ስለሚባለውና በዚህ  ስፍራ ስለሚገኘው ልንገራችሁ፡፡ ይህ ሰረገላ ለዘመናት ለኢትዮጵያውያን የሃይላቸው ምንጭ ነበር፡፡ በተጨማሪም አሁን ድረስ አንዳንድ ምስጢራዊ መረጃዎች የሚያመለክቱት ሮም ገናና በነበረችበት ወቅት የኃይል ምንጭ ይህ ገረረ ሰረገላ ነበር ኃላ ግን ከባቢሎዋውያን ጋር ውጊያ ላይ በነበሩበት ወቅት ይህ ገረረ-ሰረገላ ሙት ባህር ውስጥ ይገባባቸዋል በዚህ የተነሳም ተሸንፈው ሮም ለመፈራረስ በቅታለች፡፡ ታዲያ ከዚህ ከሙት ባህር ውስጥ እስራኤል አውጥታ በድብቅ እንዳስቀመጠችው መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ይህ ግን ፈጽሞ ከሀሰት የራቀ ታሪክ ነው ምክንያም የምድራችንን ታሪክ የስማዝያ ወገኖች እና አይሁዶች ድጋሜ ሲጽፉት ሁሉንም የራሳቸው ለማድረግ ካላቸው ምኞት የጻፉት የፈጠራ ታሪክ ነው፡፡ ገረረ ሰረገላ አንድ ብቻ ሲሆን ይኀውም አዳም ከገነት አምጥቶ ርስት በሆነችው ቦታ ያስቀመጠው ነው፡፡ ይህ ገረረ ሰረገላ ሃይል ብለን ከጠቀስነው ምስጢረ ጥበብ ጋር ተዋህዶ የሚሰራ ነው፡፡ ይህ ሃይል ያልነው ምስጢረ ጥበብ ደግሞ በዘመናችን ሚሊተሪ የምንለው እንደሆነ ልብ ይበሉ ሀይል የተሰኘውን ምስጢረ ጥበብ እና ገረረ ሰረገላ የተባለውን አዳማዊ የክብር እቃ ጠባቂ በምድር ቶዎድሮስ ሲሆን በሰማይ አባታችን የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡

በአባታችን በቅዱስ ሚካኤል እና ቶዎድሮስ የሚመራው መንፈሳዊ ሃይል ነው ኢትዮጵያን ትንሳኤ ሚያጎናጽፈን!!!

የአባታችን የቅዱስ ሚካኤል ምልጃ እና ተራዳኢነት አይለየን.... " አሜን!


Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment