የኢትዮጵያውያን የዘመን ስሌት

ጠቢባን የሆኑ አባቶቻችን የዘመን ስሌትን በሚገባ ተንትነው ዘመናዊቷ አለም ከምትጠቀምበት አቆጣጠር ረቀቅ ባለ መልኩ እስከ ሳድሲት ማለትም 0.00000185 ሰከንድ ድረስ አስለተዋል።

መሬት በፀሐይ ላይ የምታደርገው ኡደትን ተረድተው የጊዜ መለኪያ እና መቁጠሪያ አስቀመጠውልናል ....

1ኛ ሳድሲት ይህ ቁጥር 0.00000185 ሰከንድ ነው።
2ኛ ኀምሲት ይህ ቁጥር 0.00011 ሰከንድ ነው።
3ኛ ራብዒት ይህ ደግሞ 0.0067 ሰከንድ ነው።
4ኛ ሣልሲት ይህ ደግሞ 0.4 ሰከንድ ነው።
5ኛ ካልዒት ይህ ደግሞ 24 ሰከንድ ነው
6ኛ ኬክሮስ ይህ ደግሞ 24 ደቂቃ ነው።

60 ኬክሮስ=1 ዕለት ወይም 24 ሰዓት ነው።
ይህ ደግሞ 1 ሰዓት 2.5 ኬክሮስ ነው ማለት ነው።
ጨረቃ በቀን ከፀሐይ 1 ኬክሮስ ከ52 ካልዒት ከ31 ሣልሲት በአነሰ ነው ኡደቷ።

በቀን 1 ኬክሮስ በ30 ቀን 30 ኬክሮስ ይሆናል።

በ2 ወር 60 ኬክሮስ ይሆናል። 60 ኬክሮስ ደግሞ 1 እለት ስለሆነ። በ2 ወር 1 እለት በ12 ወር 6 እለት ታበራለች ማለት ነው።  በ12 ወር ወይም በአንድ ዓመት 5 ቀንና 15 ኬክሮስ ከ1 ሣልሲት ይሆናል።...... የቀረችው 52 ካልዒትን ልቀይረው.... 52 ካልዒት×30 ቀን×12 ወር=18720 ካልዒት በዓመት ይገኛል።

ይህንን ወደ ኬክሮስ ስንለውጠው 312 ኬክሮስ ይመጣል።በመቀጠል 30 ሣልሲት×30
ቀን×12 ወር 10800 ሣልሲት ይመጣል ይህንን ወደ ኬክሮስ ስንቀይረው 3 ኬክሮስ ይሆናል።

ይህ ማለት የ52 ካልዒትየ 30+(1) ሳልሲት ጠቅላላ ስንደምረው ... 312+3=315 ኬክሮስ ይሆናል።

ይህንን ወደ እለት ስንቀይረው 5 ቀን ከ15 ኬክሮስ ይሆናል።....
ይህች 5 ቀን ተሰብስባ ጷግሜን ናት.....።

የተረፈችው 15 ኬክሮስ ለ4 አመታት ስትጠራቀም... በ4 ዓመት 4×15=60 ኬክሮስ ወይም አንድ እለት ይሆናል። በአራት ዓመት አንድ ጊዜ ጳጉሜን 6 የምትሆን በዚህ ምክንያት ነው።.....

ከላይ የ30ዋን ሳልሲት ሰርቸ አንዷን አላሰላሆትም....አንዷ ሣልሲት በ600 ዓመት 1 ቀን ትሆናለች።ይኽውም 1 ሣልሲት×30 ቀን×12 ወር×600 ዓመት 216000 ሣልሲት ይገኛል ይህንን ወደ ኬክሮስ ስንቀይረው 60 ኬክሮስ ይሆናል።

60 ኬክሮስ ደግሞ አንድ ቀን ወይም እለት ነው። ስለዚህም በ600 ዓመት አንድ ጊዜ ጳጉሜን 7 ትሆናለች ማለት ነው።...ወይም በቀላል መንገድ ላሳያችሁ...

አንድ ቀን =365 እለት ከ 15 ኬክሮስ ከ 6 ካልዒት / ወይም 365 ቀን ከ 6 ስዓት ከ 2 ደቂቃ ከ 24 ሰከንድ ነው...36o ቀን + 5 ቀን ጳጉሜ .. ይሆንና 6 ስአት ከ 2 ደቂቃ ከ 24 ሰከንድ ትተርፍለች... የተሰባሰበችው 6 ስአት በ አራተኛው አመት 24 ስአት ወይም አንድ ቀን ስትሆን ጳጉሜ 6 ትሆናለች። ትራፊ 2ደቂቃ ከ 24 ሰከንዷ ትሰበሰባለች ይህ ማለት በ 600 አመት 24 ስአት ወይም አንድ ቀን ትሞላለች።

ይህ በ 600 ኛው አመት ጳጉሜን 7 ያደርጋታል ማለት ነው.....
አበቅቴ እና መጥቅእ አበቅቴ ማለት ተረፈ ዘመን ማለት ነው። ይህም ማለት ጨረቃ ከፀሐይ ባነሰ የምታበራበት የጊዜ መጠን ነው።

ፀሐይ በዓመት 365 ቀን ከ15 ኬክሮስ ከ1 ሣልሲት ታበራለች።
ጨረቃ ደግሞ 11 ቀን አንሳ 354 ቀን ታበራለች። በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት አበቅቴ ይባላል።

ስለዝህ ሊቃውንቱ በተገለጠላቸው መጠን 11 ጥንተ አበቅቴ ይባላል።

#መጥቅዕ ማለት ትረጉሙ ደወል ሲሆን አጽዋማትን እና በዓላትን የሚያስገኝ ነው ከዚህ ላይ ተንተረሰን በዚህ ቀን ይህ ጾም በዚህ ዕለት ይህ በዓል በእንዲህ ቀን ለማለት ያስችላል...።

መጥቅዕ እና አበቅቴ ተደምረው 30 መሆን ስላለባቸው መጥቅዕ 30-11=19 ይሆናል።

#ስለዚህ በመጀመሪያው ዓመት 11 አበቅቴ ከሆነ በሁለተኛው አመት 22 ይሆናል በሦስተኛው 33 ይሆናል። ከ30 በላይ ሲሆን በ30 አካፍለን ቀሪውን እየያዝን አበቅቴን እናወጣለን ስለዚህ 3 ይሆናል። ከዚያ በአራተኛው 3+ 11=14 እያለ ይሄዳል። አበቅቴና መጥቅእ ሁለቱ ተደምረው 30 ስለሚሆኑ አንዱ ከተገኘ ሌላኛውን ከ30 በመቀነስ እናገኘዋለን።

አለም ከተፈጠረች ጠቅላላ ዕድሜ 5500+2016=7514 አመት....ስለዚህ በሚቀጥለው ዓመት ዘመኑ ዘመነ ማን ነው የሚለውን ለማወቅ ስንፈልግ ዓመተ ዓለሙን ለ4 አካፍለን ቀሪው 1 ከሆነ ዘመነ ማቴዎስ ፤ቀሪው 2 ከሆነ ዘመነ ማርቆስ ፤ቀሪው 3 ከሆነ ዘመነ ሉቃስ ያለ ቀሪ ከተካፈለ ዘመነ ዮሐንስ ነው።

የዓመቱ መስከረም 1 ቀን መቼ መቼ ትውላለች?

#መስከረም አንድ ቀን መቼ እንደምትውል ለማወቅ ዓመተ ዓለምን ከመጠነ ራብዒት ጋራ ደምረን በእለታቱ መጠን በ7 አካፍለን ቀሪው 1 ከሆነ ማክሰኞ ፤ቀሪው 2 ከሆነ ረቡእ፤ቀሪው 3 ከሆነ ሐሙስ፤ቀሪው 4 ከሆነ አርብ፤ቀሪው 5 ከሆነ ቅዳሜ፤ቀሪው 6 ከሆነ እሑድ፤ ያለ ቀሪ ከተካፈለ ሰኞ ይውላል። ስለዚህ አሁን ቀጣይ መስከረም 1 መቼ ይውላል የሚለውን ለማወቅ።
(7514+1878)÷7=1341 ቀሪ 5 ይሆናል።

ቀሪው 45 ከሆነ ሐሙስ ይውላል። ስለዚህ መስከረም 1 ቀን 2017 ዓ.ም ሐሙስ ይውላል ማለት ነው።
መስከረም 1 በዋለበት ሚያዝያ 1 ይውላል
ጥቅምት 1 በዋለበት ግንቦት 1 ይውላል
ህዳር 1 በዋለበት ሰኔ 1 ይውላል
ታሕሣሥ 1 በዋለበት ሐምሌ 1 ይውላል
ጥር 1 በዋለበት ነሐሴ 1 ይውላል።
ይህም ማለት ለምሳሌ መስከረም 1 ቀን ሐሙስ ከዋለ ሚያዝያ 1 ቀንም ሐሙስ ይውላል ማለት ነው።

ታህሣሥ 19 ሰኞ ከዋለ ሐምሌ 19ም ሰኞ ይውላል ማለት ነው።.. አጽዋማትና በአላትን ዕለት ለማውጣት የምንጠቀምበት መባጃ ሐመር ይባላል ይህንን ለመቀመር የምናገኘው መጥቅዕ+መጥቅዕ የዋለበት የእለት ተውሳክ አድርገን ማገኝነት ይቻላል!!!

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment