✍ ቆሞስ አባ ጳውሊ | ከግንባር
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፈተናዎች እስከ 2030 እንደ ኢሮፓዊያን አቆጣጠር የተዘረጉ ስልታዊ የመንግሥት ውጥኖች:-
በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ እየታየ ያለው ሁለንተናዊ ምስቅልቅል እና ጂኦፖለቲካዊ ውጥረት በአገራችን በኢትዮጵያም ላይ ጥልቅ የሆነ መዋቅራዊና ርዕዮተ-ዓለማዊ ጫና እየፈጠረ ይገኛል። በተለይም መንግሥት ከዓለም አቀፍ ኃይሎችና ከሚስጥር ማህበራት ጋር በመተባበር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን እና የሀገሪቱን ታሪካዊ መሠረቶች ለማክሰም እስከ 2030 እጅግ ስልታዊ በሆኑ መንገዶች እየሰራ ነው:: በዚህ የጥፋት ዘመቻ መጀመሪያ ላይ በርካታ ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት በከባድ መሣሪያና በድሮን እየፈረሱ ንጹሐን ምዕመናንም ያለ ምህረት እየተጨፈጨፉ የሚገኙበት አሰቃቂ አካሄድ የዕቅዱ ግልጽ ማሳያ ነው። ይህ አካሄድ ሃይማኖታዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ እሴቶችን ጽንሰ-ሀሳባዊ በሆነ መንገድ ለመሸርሸር ያለመ ትልቅ መረብ ነው። ይህ የአገዛዙ የጥፋት መንገድ ቤተክርስቲያንን በቀጥታ እንዲህ ከመዋጋት ጀምሮ ልዩ ልዩ ስልታዊ በሆኑ ሁኔታ ለማጥፋት ተግቶ እየሰራ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው::
የዚህ ስልታዊ ውጥን ዋነኛ መሠረት ከጅምሩ መንፈሳዊ ግብረ-ገብነትን እና ጤናማ እሴቶችን ከህብረተሰቡ የኑሮ ዘይቤ ማስወገድ ነው። ኦርቶዶክስ አርጅታለች ቁሞ ቀር ሆናለች የሚል የተሳሳተ ንግግር አብይ አህመድ ከመናገር ጀምሮ ፓስተሮቻቸው በቤተክርስቲያን ላይ እያካሄዱት ያለው ትልቅ ዘመቻ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናን በእምነታቸው ላይ ጥርጣሬ እንዲያድሩበት ማድረግ እና የቤተክርስቲያቱን ጠንካራ የእምነት መንፈሳዊ መሠረት መንቀል የዘመኑ ዋና ተግባር ተደርጎ ስለተያዘ ነው። ከዚህም አልፎ መንፈሳዊ ህጎችና ደንቦች እንዲለወጡ ግፊት ማድረግ፣ የክርስቲያን ምዕመናንን ህብረትና ማህበራት አንድነት ማፍረስ፣ እንዲሁም የክህነትን ክብር በማራከስ በምዕመናንና በቤተክርስቲያን አባቶች መካከል ጥርጣሬና መለያየትን መፍጠር የዕቅዱ አንዱ አካል ነው። መንግሥት በቤተክርስቲያን አስተዳደር ውስጥ ተቀባይነት የሌላቸውን እና መንፈሳዊነት የጎደላቸውን ሐሰተኛ አባቶች የቤተክርስቲያን ጠባቂ በማድረግ ቤተክርስቲያንን ከውስጥ ለማፍረስ በተዘዋዋሪ መንገድ እነሱን በንቃት እየተጠቀመባቸው ይገኛል። በዚህም የተነሳ ህዝቡ በቤተክርስቲያን አባቶች ላይ ተስፋ ቆርጦ ከቤተክርስቲያኑ ፊት እንዲያዞር የማድረግ ስራዎች በስፋት እየተከናወኑ ይገኛሉ።
ሌላው አሳሳቢ ጉዳይ የሀገሪቱን የጥንት ስሞች፣ ምልክቶች እና የማንነት መገለጫዎች ላይ የሚደረገው ዘመቻ ነው። ከጥንት ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን የአለባበስ፣ የአመጋገብ እና አብርሃማዊ የሆነውን የእንግዳ ተቀባይነት ባህል ማስወገድ እንዲሁም እነዚህን እሴቶች የአማራ ባህል ናቸው በሚል ጠባብ ትርክት በመስጠት በሌሎች ብሄሮች ዘንድ እንዲጠሉት ማድረግና በውጭ እንግዳ ባህሎች መተካት የዕቅዱ ማዕከል ነው። ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ናት የሚለውን እውነት ለማጣጣል እና ሀገሪቱ ወደ እግዚአብሔር እጆቿን የመዘርጋት ታሪካዊ ጸጋ እንዳላት የሚያሳየውን እውነት ለማጥለላት ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል። የሀገሪቱን ታሪካዊ መሠረቶች በመናድ የጥንታዊቷን ኢትዮጵያ ባንዲራ ጭምር ለማጥፋት የሚደረገው ጥረት የዚሁ መዋቅራዊ ጥፋት ማሳያ ነው።
የቅዱሳንን ምልጃና ጸሎት ማራከስ፣ ዓመታዊ በዓላትንና የህዝብ እንቅስቃሴዎችን መገደብ፣ እንዲሁም የቤተክርስቲያን የበዓል ማክበሪያ ይዞታዎችን በመንጠቅ ምዕመናን ጎልተው የሚታዩበትን መንገድ ማጥበብ እንዲሁም የኢኮኖሚና የማህበራዊ ጫና ማድረግ ለጥፋት መንገዱ ትልቅ መሣሪያ ሆኗል። በቤተክርስቲያናዊ የጋብቻ ስርዓት ላይ የሚደረገው ዓለማዊ ጣልቃገብነትም ክብሩን በማሳጣት መንፈሳዊም ሆነ ዓለማዊ ፋይዳ የሌለው ድብልቅ ስርዓት እንዲሆን በማድረግ የሰዎችን ግንዛቤ ለመበከል እየተሰራ ይገኛል። አጠቃላይ አገዛዙ የቤትክርስቲያንን ከእምነት እስከ ስርዓት ያሉትን መሰረቶች በማናጋት ስራውን እየሰራ ይገኛል:: በማንኛውም መንግሥታዊና መንግሥታዊ ባልሆኑ የስራ ገበታዎች ላይ የሚገኙ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞችን ማግለል፣ ኢኮኖሚያዊ አቅማቸውን ማዳከም እና በስደት እንዲሰቃዩ ማድረግ የህዝብ ቁጥራቸውን ለመቀነስና ጽናታቸውን ለመፈተን የታለመ አደገኛ ስልት ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃም የሰዎች ሰብዓዊ መብት ሲረገጥ ዝምታን በመምረጥ ሆን ተብሎ የሚፈጸመው ግፍ ምዕመናን ተስፋ ቆርጠው ሃይማኖታቸውን እንዲቀይሩ ወይም ሀገራቸውን ጥለው እንዲሰደዱ የማድረግ ራዕይና ተልእኮ አለው። እግዚአብሔር እንዳይታረቀን ፍጹም ሰላሙም እንዳይወርድ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ንጉሳዊ የአስተዳደር ስርዓት እንዳይመለስም በታላቅ ሴራና ፍርሃት እየሰሩ ይገኛሉ:: ይህም ትክክለኛው የእግዚአብሔር ፍጹም ሰላም የሚገኝበትን ሰላማዊ እሴቶችን በማጥላላት ህዝቡ ለአምባገነናዊና ጨካኝ የውጭ አገዛዝ ስርዓቶች እንዲገዛ ማድረግ እና በመጨረሻም ህዝቡን ከሃይማኖታዊ አምድ ነቅሎ ለመጭው የጥፋት መንገድና እየመጣ ላለው ለሀሳዊ መሲህ አሰራር ማዘጋጀት የዚህ ሁሉ ዓለም አቀፍና ፖለቲካዊ ሴራ ማጠቃለያ ግብ ነው። ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ኢላማ ያስገቡበት ዋነኛው ምክንያት እውነት ስለሆነች እውነትን እንዳትገልጥባቸው በማሰብ ነው:: ይህ ሁሉ የሰሜኑ ጦርነት ልክ እንደ ፈሊጣዊ አነገገር ሰምና ወርቅ አለው:: ፖለቲካዊ መልክ ቢይዝም ዋና ጥፋቱ ሳይታለም የተፈታ ነው!
ውድ የቤተክርስቲያን ልጆች ሆይ እኛ ምዕመናን ስለ ሃይማኖታችን ልንቆም ግድ የሚለን ሰዓት ላይ እንገኛለን! ምዕመናን ስለ ቤተክርስቲያን ታሪክ፣ ቀኖና እና ዶግማ ጥልቅ ግንዛቤ እንዲኖራቸው መሠረታዊ የሰንበት ትምህርት ቤቶችና የስብከተ ወንጌል መድረኮች መጠናከር አለባቸው። ወጣቱ ትውልድ በዘመናዊ እውቀትና በመንፈሳዊ ጥበብ ታንጾ የውጭ ርዕዮተ-ዓለሞችን ተጽዕኖ መመከት እንዲችል መደረግ አለበት። የሃይማኖት አባቶች ልዩነቶችን በትዕግስትና በፍቅር በመፍታት ከግል ጥቅሞች ይልቅ የቤተክርስቲያንን ህልውናና የህዝቡን መንፈሳዊ ደህንነት ማስቀደም ይኖርባቸዋል። የውስጥ መከፋፈል ለጠላቶች በር የሚከፍት በመሆኑ ጠንካራና የማይበገር የአስተዳደር አንድነት መፍጠር ግድ ይላል።
ምዕመናን እርስ በእርሳቸው የሚደጋገፉበትን የንግድና የኢኮኖሚ አውታሮችን በጋራ የሚያጠናክሩበትን አሰራር መዘርጋት ያስፈልጋል። ቤተክርስቲያንም የልማትና የበጎ አድራጎት ተቋማቷን በማጠናከር የተቸገሩ ምዕመናንን ከድህነትና ከስደት አደጋ መጠበቅ ትችላለች። ኢትዮጵያዊና ክርስቲያናዊ የሆኑትን የአለባበስ፣ የእንግዳ ተቀባይነት፣ የአብሮነት እና የሞራል እሴቶች በትውልድ መካከል በኩራት እንዲቀጥሉ መስራት ይገባል። የሀገርንና የቤተክርስቲያንን ታሪክ በጽናት መያዝ እና የውጭ ዘመናዊነትን ሽፋን አድርገው የሚመጡ አጥፊ ባህሎችን በንቃት መቃወም ተገቢ ነው። በመጨረሻም የሚደርሰውን ሁሉ መከራ በትዕግስትና በጸሎት ለማለፍ መንፈሳዊ ህብረትን ማጠናከር ይገባል። ታሪክ እንደሚያስተምረው ቤተክርስቲያን የበርካታ መከራዎች ማዕበልን በድል አቋርጣለችና በፅናት፣ በህብረትና በእግዚአብሔር ርዳታ አሁንም ያሉትን ፈተናዎች ማለፍ ይቻላል። ሌላውና አሁን እየፈተነን ያለው አስተምህሮ ላይ ማትኮር አለብን:: በሰላምና በመከራ በጭንቅ ጊዜ የምናስተምራቸውን ትምህርቶች በሚገባ መረዳት አለብን:: አሁን ትውልዱን ቤተክርስቲያኑንና ሀገሩን እንደቀድሞ አባት እናቶቹ እንዲታደግ ማድረግ አለብን:: በከንቱ ጽድቅ በሚመስል ስንፍና ሀገርም ቤተክርስቲያንም ሲጠፉ እያየ የሚያንቀላፋ ትውልድ መቅረጽ የለብንም! ምን ማለት እንደፈለኩ ገባችሁ? ቤተክርስቲያንን መጠበቅ ባለብን መንገድ ሁሉ መጠበቅ ጽድቅ እንጅ ኃጥአት አይደለም! አንዳንድ የመንግሥት ደጋፊ የሆኑ ሆ*ዳም ሀሳዊ መምህራንን አትስሙ! ህዝቡ ላይ የፍርሃትና የድካም አዚም ዱካክ በመጫን ለአገዛዙ በስውር እየሰሩ እንደሆነ አትዘንጉ::
ቤተክርስቲያንን እንጠብቅ ርስት ጉልታችን ሃይማኖታችን እናስከበር ቅድስት ሀገራችንን እንታደገ!
ድል ለኢትዮጲያ ድል ለቤተክርስቲያን!
Blogger Comment
Facebook Comment