የእግዚአብሔር ሀገር የሆነችውን ኢትዮጵያን የሚንቅ እንደ ጅብ እርስ በእርሱ ከመባላት ዉጭ የትም አይደርስም፦

✍ ሸንቁጥ አየለ

ለጽንፈኛ ብሔርተኛ እንዲሁም ጽንፈኛ የሀይማኖት አክራሪዎች ሁሉ፦

የአክራሪ አልቃይዳ፣ አይሲስ፣ አልሸባብ እና ዋህቢያ ኃይላትን በማጠናከር፣ ሰማይ በማድረስ፣ የሐሰት ጥላቻ በመፍጠር፣ “ተበደላችሁ፣ ተጨቆናችሁ” እያለ ወያኔ ለ27 ዓመታት አሳበጣቸው።

እብጠታቸው አሁንም በኦነግ፣ በኦህዴድ፣ በአቢይ ዘመን እንዲቀጥል ሆኗል። እናም ሚሊዮን ክርስቲያኖችን መጨፍጨፍ፣ ማፈናቀል፣ ቤተክርስቲያናትንም ማቃጠል “መብታችን ነው” እያሉ እያጓሩ ነው።

የኢትዮጵያ ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች ታላቅ ሕዝብ ናቸው፤ ለዘመናት አብረው ኖረዋል፣ ተሳስረዋል፣ ተጋብተዋል፣ ሀገር ጠብቀዋል:: በኢትዮጵያ ውብ ባሕል ውስጥም ካህናት ሙስሊም ሴቶችን፣ ሸኾችም ክርስቲያን ሴቶችን ያገቡበት ታሪክ አለ፤ ሕዝቡም ተዋልዷል፣ ተወዳዷል፣ ተከባብሯል። 

የአክራሪ አልቃይዳ፣ አይሲስ፣ አልሸባብ እና ዋህቢያ ኃይላት ግን እንደ ወያኔ/ኦነግ/ኦህዴድ/ብአዴን/ደህዴን/ብልጽግና እንዲሁም እንደ ብዙ ጽንፈና የጎሳ ድርጅቶች ሀሰተኛ ትርክት ተሸክሞ ኢትዮጵያዉያንን ሊያባላ እየሰራ ነዉ::ይሄ ጽንፈኛ ሀይል ሙስሊምንም ሆነ የተኛዉንም ብሄር አይወክልም::ልክ ጽንፈኛ ጎሰኞች የፖለቲካ ፓርቲያቸዉን እንጂ የህዝብን ፍላጎት እንደማይወክሉት ሁሉ::

ለሱ ብሄር ብቻ ካልተመቸችዉ ጽንፈኛ ሀይል ኢትዮጵያን ማድማት ብሎም ማፍረስ ዋና ግቡ እንደሆነ የአክራሪ አልቃይዳ፣ አይሲስ፣ አልሸባብ እና ዋህቢያ ኃይላትም አንድና ብቸኛ ግባቸዉ ኢትዮጵያ ማዳከም ብሎም ማጥፋት ነዉ::ኢትዮጵያ የእግዚአብሄር ሀገር የሚባል በምድር ላይ እንዳይይኖር መዋጋት የህይወታቸዉ ግብ ነዉ::

የኢየሱስ ክርስቶስ ሙሽራ የሆነችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ለማጥፋት፣ አንዴ “ጨቋኝ ነች”፣ አንዴ “በቅኝ ግዛት ኢትዮጵያን ለመፍጠር ከአማራ ነገሥታት ጋር ተባብራለች” በማለት፣ ለ27 ዓመታት ሲከሳት፣ ሲያዋርዳት፣ ከጠላቶቿ ጋር የኖረው ወያኔ፣ አሁን ደግሞ አቋሙን በመለወጥ “ቅድስት አክሱም” እንዲሁም “ቅዱስ ንጉሥ ዮሐንስ” የሚል ፕሮፓጋንዳ ይዞ ከች ብሏል።

ወያኔ ሆይ፣ ልንገርህ እማ። በትግሬም፣ በደቡብም፣ በአማራም ሆነ በኦሮሞ የተሰለፍክ መርዘኛ እና ጠባብ ብሔርተኛ ሁሉ፣ ስማማ እማ። የእኔ ብሔር ካተረፈ ስለ ኢትዮጵያ አያገባንም የምትል ሁሉ፣ ስማ እማ! 

ኢትዮጵያን አክብረህ ሳታድን፣ የእግዚአብሔር ሀገርነቷንም ሳታከብር፣ ሁላችሁም የትም አትደርሱም። እንደ ጅብ እርስ በርሳችሁ ትበላላችሁ እንጂ!

ኢትዮጵያንስ የሚያድናት አለ። “እኔ መድኃኒዓለም ኢትዮጵያን አድናለሁ” እንዳለ፣ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ይህ ነገድ፣ ያ ነገድ፣ ይህ እምነት፣ ያ እምነት ሳይባል፣ ሁሉም ይድናል።

ኢትዮጵያን ማንኛችሁም አትችሏትም።

ነቢያቱ እንደተነበዩት፣ በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣው ለኢየሱስ ክርስቶስ ኢትዮጵያ ትንበረከካለች። እጇንም ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች። እሱም ያድናታል!

ኢትዮጵያዊ ሁሉ የእግዚአብሔር ልጅ ነውና! ሌላው ዓለምስ የሚል ጥያቄ ካለህም፣ መጽሐፍ ደግሞ ይህን እንዲህ ይልሃል፦

“ከታመነውም ምስክር፣ ከሙታንም በኵር፣ የምድርም ነገሥታት ገዥ ከሆነ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።” የዮሐንስ ራእይ 1፥4-5

እናማ ዓለሙ ሁሉ የኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ኢትዮጵያም።
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment