በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት አስተምህሮ መሰረት ከሌሎች የሃይማኖት ተቋማት ጋር አብሮ መፀለይ አይፈቀድም።


ቆሞስ አባ ጳውሊ | ከግንባር

አብሮ መፀለይን የሚከለክልበት ምክንያት የሃይማኖትን ንጽህና ከመጠበቅ እና ከመጽሐፍ ቅዱስም በመነሳት ነው። ቅዱስ ጳውሎስ  በመልእክቱ የተናገረውን እንመልከት! " ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው?" ፪ኛ ቆሮንቶስ ፮:፲፬ ከዚህ ጥቅስ በትክክል ከሌሎች ጋር አብረን መፀለይ እንደማይፈቀድ ይነግረናል። ፍትሐ ነገስትም ይህን የእግዚአብሔርን ቃል መሠረት በማድረግ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ምእመናን ከሌሎች በሚስጥራችን ከማይተባበሩ ጋር አብረን መፀለይ እንደማንችል አስቀምጦልናል።  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ መሰረት ሌሎቹ የሃይማኖት ተቋማት ተከታዮች እንዳልዳኑ በእውነትም መንገድ ላይ እንዳልሆኑ ታስተምራለች ትናገራለች። እርሷም ብቻ እውነትና መንገድ እንደሆነች ትናገራለች ይታወቃልም። ስለዚህ አስተምሮቷን ወደ ጎን ትታ ከሌሎች የሃይማኖት ተቋማት ጋር አብራ ከጸለየች በምእመናን ዘንድ ትልቅ ውዝግብ ይፈጥራል። ይህም ሃይማኖታዊ ስርዓቶችን እና እምነትን አንድ ለማድረግ የሚሞክር ይመስላል። በዚህም ምእመናን ሁሉም ሃይማኖቶች እውነት ይኖራቸዋል ወደሚል ስህተት ይጓዛል ማለት ነው። በተለይ በአሁኑ ጊዜ ምን ችግር አለው የሚል ትውልድ በተነሳበት ሰዓት እንደዚህ መደረግ መለመዱ እጅግ በጣም ትልቅ ስህተት ነው። ለነገሩ አሁን ቤተክርስትያን ላይ የተቀመጡት አባቶች የም* ን* ፍ * ቅ*ና  መ*ንፈስ የተጠናወታቸው ስለሆኑ ቤተክርስትያንን ያለ መንገዷ እንድትጓዝ እያስገ*ደዷት ነው።  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች ይህንን ፍፁም ስህተት የሆነ አካሄድ በመለማመድ ህዝቡ ግራ እንዲጋባ እያደረጉ ነው።  ፍተሐ ነገስት ስለዚህ ጉዳይ ከሌሎች አህዛብ ወይንም መ *ና* ፍ*ቃ*ን ጋር መፀለይ እንደማንችል በተለያየ መልኩ አስጠንቅቆናል። ሌሎችንም የቤተክርስትያን አበው ትምህርትና የጥንቷን ጉባኤያት ህጎችን በጥልቀት መመርመር ይገባችኋል።  ይህቺ ቤተክርስትያን "አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት " ኤፎ. ፬፥፭ እያለች እያስተማረች ሌላ ከብዙ ሃይማኖትና ብዙ ጌታ ካላቸው ጋር አብረን መፀለይ እንዴት እንችላለን?  በቃ ማስተዋል አት*ችሉም ማለት ነው?  ይህን ፀሎታችን ብላችሁ የምትቀልዱትንስ ማነው የሚሰማችሁ? አብይ አህመድ ነውን? አስባችሁታል እናንተን በሃይማኖት ዝብርቅርቅ ያላችሁትን እግዚአብሔር ጸሎታችሁን ሲሰማ! በምንም መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ይህንን የክህ*ደት መንገድ በፍጹም አትደግፍም! እናንተ ግን ወንበ*ዴዎች ስለሆናችሁ የፈለጋችሁትን እያደረጋችሁ ነው። ጸሎታችሁ ግን እንኳን ከደመነ በላይ ይወጣ ከተሰበሰባችሁበት አዳራሽ እልፍ አይልም!  ለብልጽግና ጸልዩለት የእናንተ ጸሎት ሲያ*ድነው እንይ! 

በመሠረቱ የእናንተ ዓላማ መንግሥትን እየፀለይንልህ ነው የጥ*ፋት መንገድህን ቀጥልበት እያላችሁ ነው። እናንተ እንደዚህ በእግዚአብሔር ላይ እየተዘባበታችሁ የምታደርጉት ጸሎት ያላችሁት ስላቅ በኢትዮጵያ ላይ የባሰ መከራ ነው የሚያመጣው። እግዚአብሔር ልብና ኩላሊትን የሚመረምር የፍትህ ዳኛ ነው። እያንዳ*ንዳችሁ ከሚመጣባችሁ ፍርድ በፍጹም አታመ*ልጡም። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የበላይ ጠባቂዎች የምንላቸው ቤተክርስትያንን በጣም ከልክ በላይ ተደፋ*ፍረዋታል።  እግዚአብሔር ዝም ያለ ስለመሰላቸው በቃ ልባቸው ደንድኗል። የተዘጋጀላቸው ስላለ ነገ መሪር እንባን ያነ*ባሉ። እግዚአብሔር ቤተክርስትያንን አይተዋትም በቅርብ ያነሳታል። 
ለማንኛውም ውድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ልጆች ሆይ አባቶች የሚያደርጉት ስህተት ስለሆነ የማይመስል እንቅስቃሴያቸውን ስታዩ ቤተ ክርስቲያን የተሳሳተች እንዳይመስላችሁ! ቤተክርስትያን እውነት ናት እስከ ዘለአለምም በእውነት ጎዳናዋ ትመራለች።  ቤተክርስቲያን የምትፈቅደው ሌሎችን አክብሮ መኖርን ብቻ ነው። የሌላ ሀይማኖት ተከታይ የሆኑትን መብታቸውን መጋፋት፣ ማሳደድ፣ ለጥላቻ የሚዳረግ ነቀፌታን አታበረታታም። ‹‹ቢቻላችሁስ ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ›› ሮሜ. ፲፪፥፲፰ ብላ ከሁሉም ሰው ጋር ተስማምተን እንድንኖር ታስተምራለች እንጂ አብራችሁ ፀልዩ ብላ የክ*ፉ መናፍስት መጫወቻ አታደርገንም።  ሌላው ልታውቁት የሚገባ ነገር የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሚባሉት የመንግሥት ስራ አስፈጻሚ ናቸው። ባለፈው በኦሮሚያ ክልል በተካሄደ የዘር ጭፍ*ጨፋ የወጣውን ወንጀል ለመደበቅ የሄዱበትን መንገድ ታስታውሳላችሁ። ስለዚህ እነዚህ የሃይማኖት ጉባኤ በሚል ሰበብ የተሰበሰቡ የወን*በደዎች ጉዳይ አሳስቦኝ ሳይሆን የቤተክርስቲያን ልጆች እንዳይሳሳቱ ይህንን እናገር ዘንድ ፈልጌአለሁ። ሰሞኑን ስራ ስለበዛብኝ በዚህ ጉዳይ ቅድሚያ መናገር ቢኖርብኝም ለምታስተውሉ ሁሉ ይህ መልዕክት ቢዘገይም ይድረሳችሁ።  እግዚአብሔር ጥሩ አባቶችን እስኪአስነሣ ድረስ ጽኑ በርቱ ጠንክሮ። ቤተክርስቲያን እንደወደቀች አትቀርም! ከኢትዮጵያ ጋር አብራ ተነሳለች! 


Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment