የሰው ልጅ በበደል ምክንያት ከገነት ከተባረረ ጀምሮ የተዘጋጀችው ምድራዊቷ ጊዜያዊ መጠለያችን መሬት ናት። ብዙውን ጊዜ ከገነት ከክብራችን በመዋረዳችንና የእግዚአብሔርንም አዳምን በወዝህ ጥረህ ግረህ ብላ የተባለውን ቃል በማሰብ ሁሌም ምድርን እንረግማለን። ልክ ምድርን እንደ ሲዖል እግዚአብሔርም እኛን ለመቅጣት እንዳዘጋጀት አድርገን እናስባለን። በመሰረቱ ግን ምድር ለሰው ልጅ ውብ የሆነች ጊዜያዊ ስጦታ ናት:: የሰው ልጅ በራሱ የጥመት መንገድ መከራ እንዲፈራረቅባት አደረጋት እንጅ ምድርን ሐመልማላትን እንድታበቅል በውስጧም እጅግ ድንቅ የሆኑ ማዕድናት የሚገኙባት በየብስ የሚሽከረከሩ በባህር የሚርመሰመሱ እንስሳትን፣ በሰማይ የሚበሩ ግሩማን አዕዋፍትንና ልዩ ልዩ ለዓይን የምትማርክ መግለጽ ከምንችለው በላይ ውብ አድርጎ ነው ያዘጋጀልን። ፈጣሪ ዓለማት እግዚአብሔር ምድርን እንዲህ ውብ አድርጎ አስጊጦ ኃጥእን ወይንም ጻድቃን እንዲሁም የሚያምን የማያምን ሳይል ሁላችንም በጊዜያዊነት እንድንኖርባት ሰጥቶናል።
እግዚአብሔር እያንዳንዱ ህያዊት ነፍስ ያለችውንና ግዑዝ የሆነን ፍጥረታት ሁሉ በዓላማ ነው የፈጠራቸው:: በምድር ላይ በቀመር በመቀመር ወቅትና ጊዜ ሰፍሮ በእያንዳንዱ ሰዓትና ዘመን ሥራውን ይሰራል:: በምድር ላይ እርሱ በሚፈቅድባቸው ቦታዎች ለይቶ ስራውን ይሰራል። ለምሳሌ ያክል ብንወስድ ከሦስቱ አካል አንዱ የሆነው ወልድ ዘመኑ ሲፈጸም የሰውን ልጅ ለማዳን ከስጋዋ ስጋ ከነፍሷ ነፍስ ለመንሳት ዓለም ሳይፈጠር ቀድሞ በህሊናው ሲያስባት የነበረችው ድንግል ማርያም በናዝሬት ገሊላ ተወልዳለች (በሊባኖስ ተራራም የሚሉ አሉ)። ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በቤተልሄም ተወልዶ በምድር ላይ ተመላልሶ ከአስተማረ በኋላ ቀራኒዮ ጎልጎልታ በተባለች ቦታ ላይ ተሰ*ቅሎ ዓለምን አድኗል። የክርስትና እምነት ማዕከሉን ቀራኒዮ ላይ በማድረግ በመላው ዓለም ተስፋፍቷል። እግዚአብሔር የሰውን ልጅ በዚህ በምድር እንዲኖር ከፈቀደለት ጀምሮ እስከ ዳግም ምጽአት ድረስ ስራውን የሚሠራባቸው ቦታዎችን አዘጋጅቷል። ልክ ከሰዉ ተለይተው ለሐዋርያነት ወይንም ለክህነት እንደሚመረጡ ሁሉ ሀገራትም እንዲሁ ለክብሩ መገለጫ ሊሆኑ ይመረጣሉ። ከመጽሐፍ ቅዱስ አንጻር ስንመለከታቸው በብሉይ ኪዳን በእግዚአብሔር ሲያምኑ የነበሩ ሀገራት እስራኤልና ኢትዮጵያ ብቻ ነበሩ። ኢትዮጵያ ስንል ኤርትራን፣ ሰሜንና ደቡብ ሱዳንን አብዛኛውን የተነጠቅነውን ጨምሮ ማለት ነው። ኢትዮጵያ በብሉይ ኪዳን ከእስራኤል ይልቅ ለእግዚአብሔር ቅርብ እንደሆነች መጽሐፍ ቅዱስ ቁልጭ አድርጎ ይነግረናል። በትንቢተ አሞጽ ፱፥፯ ላይ "እናንተ እስራኤላውያን ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን?" ብሎ ኢትዮጵያውያን ከእስራኤላውያን ለእግዚአብሔር የሚመቹ እንደሆኑ በማያጠራጥር መልኩ አስቀምጦልናል። መዝ. ፷፰፥፴፩ "ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።" የሚለውን የነብዩ ዳዊትን ቃል በውል ብናጤነው ኢትዮጲያ ምን ያክል በእግዚአብሔር የተመረጠች ሀገር እንደሆነች ሊጠፋን አይችልም ነበር። ይህ ቃል ለእስራኤል ወይንም ዛሬ ኃያላን ብለን ለምንጠራቸው ሌሎች ሃገራት የተነገረ አይደለም። ሀገራችን ኢትዮጵያ ከሌሎች ሀገራት በጣም የተለየች ናት።
ኢትዮጵያ ተራ ሀገር ናት ብለው የሚያቃልሏት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት የምታስተምረውን ትምህርት የሚቃወሙ ናቸው። ሀገራችንን ኢትዮጵያን እንደማንኛውም ተራ ሀገር ናት እያሉ የሚያቃልሉበት ዋነኛው ምክንያት ኢትዮጵያ ሃገረ እግዚአብሔር ናት ከተባለ በተዘዋዋሪ እውነታው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ትክክለኛ ሃይማኖት ናት ስለሚያስብልባቸው እርሱን ለማጣጣል ነው። ምሥጢሩ መጽሐፍ ቅዱሱ ስለ ኢትዮጵያ ስለሚመሰክር የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት እውነተኛ መንገድ መሆኗን ቁልጭ አድርጎ ስለሚያሳይባቸው ነው። ይህም ለልዩ ልዩ የሃይማኖት መፈጠር ማዕከል ለሆኑት ለሩቅ ምስራቅና ለአውሮፓውያን ከባድ ራስ ምታት ነው! ለበርካታ ዘመናት በዚህ ዙሪያ ሴራዎችን ሲሰሩ ቆይተዋል። ቃላትን ከመቀየር ጀምሮ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ኢትዮጵያ ተብላ የምትጠራውን ሀገር ስም እስከ መቀየር ኢትዮጵያውያንንም ስለ ኢትዮጵያና ከእግዚአብሔር ጋር ያላትን ቁርኝት የተሳሳተ ግንዛቤ እንዲወስዱ ብዙ ስራዎችን ሰርተዋል። ኢትዮጵያ ሃገረ እግዚአብሔር ስትባል በርካቶች የሚያቅለሽልሻቸው ለዚያ ነው! ግን ቢመራቸው ይወጡት እንጂ እውነቱን ማንም ሊቀይረው አይችልም።
ኢትዮጵያ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የሰጠውን ቃል ኪዳኑ ሁሉ ተቀብላ ለበርካታ ዘመናት ጠብቃና አስጠብቃ የኖረች ብቸኛ ሀገር ናት። በብሉይ ኪዳን በኖህ ዘመን ለሰው ልጅ ዳግም በንፍር ውሃ እግዚአብሔር እንደማያጠፋን ቃል ኪዳን የተሰጠውን ቀስተደመና ምልክት የሃገሪቱ ባንድራ ከማድረግ ጀምሮ በሲና ተራራ ላይ በእግዚአብሄር ጣቶች የተጻፉ አስርቱ ትዕዛዛት ጽህፈት ያሉበትን የኪዳኑን ጽላት ከነ ታቦቱና በሀዲስ ኪዳንም የመዳናችን ምልክት የሆነውን በቀራኒዮ ላይ የጌታችን የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ደ*ም የፈሰሰበት ስጋው የተቆረሰበት መስ*ቀልን ይዛ ትገኛለች። ልታስተውሉ የሚገባ ነገር ቢኖር የኢትዮጵያን ባንድራ ጨርቅ ነው እያላችሁ የምታቃልሉ እረፉ! ባንድራው ከቀድሞ ከኖኅ ጀምሮ ለእናት አባቶቻችን የተሰጠ የቃልኪዳን ምልክታችን ነው:: ኢትዮጵያ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለም ያለውን ባንድራ ምልክቷ ያደረገችው ከእግዚአብሔር በተሰጣት ጸጋ፣ቃልኪዳንና ጥልቅ መንፈሳዊ ትርጉም እንጅ ዝም ብላ በአጋጣሚ በዘፈቀዴ አይደለም:: አባት እናቶቻችን ከሰባቱ የቀስተና ደመና ቀለማት መካከል ሶስቱ ጎልተው የሚታዩትን ያደረጉበት ምክንያት የራሱ የሆነ ምስጢራዊ ትርጉም ስላለው ነው:: በዚህ ባንድራ ኢትዮጵያውያን በርካታ ታሪክን ሰርተውበታል:: ባንድራውን በመቀየር የኢትዮጵያን ማንነትና ተስፋ ለማጥፋት የሚጥሩት ጠላ*ቶቿ አሁን ለጊዜው የተሳካላቸው ቢመስላቸውም በቅርብ ይህች የሚጠሏት ትክክለኛዋ ባንድራ ከፍ ብላ ትውለበለባለች!
ኢትዮጵያ በዋናነት ልዩ የሚያደርጋት ብሉይና ሀዲስን አስማምታ ቀድማ በብሉይ ኖራ ሀዲስን ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአረገ በአንደኛው ዓመት በኢትዮጵያው ጃንደረባ አማካኝነት የተቀበለች መሆኗ ነው። ይህም እስራኤላውያን ክርስትናን ላለመቀበል ሐዋርያትን በሚያሳድዱበት ጊዜ ነው። የቤተክርስቲያን ጠላ*ቶች በሐሰት ታሪክ ኢትዮጵያ ክርስትናን በ፬ተኛው መቶ ክፍል ዘመን እንደተቀበለች የሚናገሩ አሉ። ሆኖም ግን በ፬ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የሃገሪቱ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ የታወጀበት ነው:: ሐዋ ፰፥፳፮ ላይ ያለውን ታሪክ በደንብ አንብቡት! ኢትዮጵያውያን ብሉይ ኪዳንን የሚያምኑ ክርስትናንም የተቀበሉ ሁለቱን አስማምተው ጠብቀው የኖሩ ናቸው:: ይህም ከዓለም ልዩ ያደርገናል! እንደ እኛ ብሉይ ኪዳንን ስታምን የነበረችው እስራኤል ክርስትናን አለመቀበሏን ስታስቡ ኢትዮጵያ ከፍ ብላ ትታያችኋለች! ኢትዮጵያ መስዋዕተ ኦሪት ሲሰዋባት የነበረች በአዲስ ኪዳንም የጌታችን የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አማናዊ ስጋውና ደሙ የሚፈተትባት ብቸኛዋ ሀገር ናት። ብቸኛዋ ስላችሁ ትክክለኛ እውነት ትክክለኛ መንገድ ያለባት ለማለት ነው። ኢትዮጵያን ከሌሎች ሀገራት ልዩ ከሚያደርጓት መካከል አንዱ ተራራቿ ሁሉ ቅዱሳን የሞሉበት መሆኗ ነው። በዓለም ዙሪያ ያሉ ቅዱሳን የሚሰባሰቡበት ምድራዊቷ ብሄረ ህያዋን ናት:: ፳፬ ሰዓት ሰዓት ምስጋና የማይቋረጥባት በአካለ ስጋ ያሉና ከእኛ እይታ የተሰወሩ ቅዱሳን በፈረቃ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር እያሉ የሚያመሰግኑባት ብቸኛዋ ሀገር ናት። በሰማያዊ በመላእክት ቋንቋ በግዕዝ ፈጣሪዋን የምታመሰግን ምድራዊቷ ገነት ኢትዮጵያ ብቻ ናት! ከኢትዮጵያ ዉጭ ለማንም የሌለው ማኅሌቱ፣ ወረቡ፣ቅኔው፣ ኪዳኑ፣ቅዳሴው፣ በዓላት አከባበሩና ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ክንዋኔው እንደ ሰማያዊ መላዕክት ልዩ የሚያደርገን ነው። አዕምሮአችንን ስላታለልነው እንጂ ኢትዮጵያ በጣም ልዩ የሆነች የተመረጠች ሀገር ናት። ልክ በነብዩ ዳዊት "ለኢትዮጵያ ህዝቦችም ምግባቸውን ሰጠሃቸው" ተብሎ እንደተነገረው በቅዱስ ያሬድ አማካኝነት የመላእክትን ሰማያዊ ዜማን ሌት ተቀን የምንመገብ እኛ ኢትዮጵያውያን ብቻ ነን:: አይደንቅም? ላስተዋለው ሰው በእጅጉ ይደንቃል! ላላስተዋለውና በመንፈስ ለማይረዳው ግን ምንም የማይመስል ሊሆን ይችላል::
ይህችን ለእግዚአብሔር ልዩ የሆነች ሰማያዊ ስርዓቱን የሰራላትን ቅድስት ሀገር ዲያቢሎስ በልዩ ልዩ መልኩ በማዕበል እያናወጻት ለበርካታ ዘመናት አሁን ካለችበት ጊዜ ደርሳለች። አባቶቻችን እና እናቶቻችን ይህችን ቅድስት ሀገር ራሷን ሆና እንድትቀጥል ብዙ መስዋዕትነትን እየከፈሉ በደምና በአጥንታቸው እስካሁን ድረስ አቆይተዋታል። የውጭ ጠላቶች ኢትዮጵያ የምትባልን ለማ*ጥፋት ለበርካታ ጊዜ በቀጥታ በወ*ረራ ሙከራ ያደረጉ ቢሆንም በአባት እናቶቻችን ጥንካሬና በእግዚአብሔር አጋዥነት ኢትዮጵያ ኢትዮጵያን መስላ ከእኛ ትውልድ ደርሳለች። እኛ ትውልድ ላይ የደረሰችው ኢትዮጵያ ግን የትላንቷ ኢትዮጵያ ሆና እንድትቀጥል አላደረግንም:: ማዕበል የሚያማታት የመከራ ማቅን የለበሰች ፣የተጎሳቆለችና የመከራ ቀንበር የከበዳት አድርገናታል። በአውሮፓውያን እና በሩቅ ምስራቅ የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጠላ*ቶች ሁለንተናዊ አጋዥነት ኢትዮጵያ መከራ እየደረ*ሰባት ይገኛል። ይህም አሁን ኢትዮጵያን የሚ*ዋጓት ተወካዮች ሲሆኑ መንግስታዊ መዋቅር በተዘረጋ ስርዓት ነው። ይህም ቤተ ክርስቲያንን (ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖትን) ለማጥፋት ኢትዮጵያን መም*ታት ስላስፈለጋቸው ነው። ለዚህ ይመቻቸው ዘንድ ኢትዮጵያን በብሔር በመከፋፈል ወደማትወጣበት አዘቅት እንድትገባ ማድረግ ነው። ከዚያም ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖትን ለማጥፋት ለዚህ ሃይማኖት መሠረት የሆኑትን የሰሜን ህዝቦችን ለይተው እያ*ጠፉ ይገኛሉ። እነዚህን ህዝቦች ጨ*ቋኝ፣ተም*ክህተኛ ወዘተርፈ የሚል ቅጽል ስም በመስጠት በሌሎች ዘንድ እንዲጠሉ በማድረግ የጥፋት ስራቸውን ይሰራሉ። በዚህ ጉዳይ በተለይ የአማራና የትግራይ ህዝቦች መከራ እየተቀበሉ ይገኛሉ:: በዋናነት እነዚህ ህዝቦች እርስ በእርሳቸው እንዳይስማሙም ስራ ተሰርቷል! ስርዓት በተቀየረ ወቅት የሚመጣው ጥፋት ለሴራ ይመች ዘንድ ፖለቲካዊ መልክ ቢኖረውም ዓላማው የታወቀ ነው:: ከደርግ ጀምሮ እስከ ብልጽግና ድረስ ለኢትዮጲያና ለቤተክርስቲያን ከባድ የጥ*ፋት ዘመናት ናቸው:: ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት የሰው ልጅ በማንነቱም ምክንያት እንዲገለል በፍጹም አታስተምርም። ወንጌል የሚያስተምረው አንድነትን ነው:: ቤተክርስቲያን በፍቅር ወደ እርሷ የሚመጡትን ትቀበላለች ከርሷ ለሚወጡ ትፀልያለች እንጂ አታሳድድም። እግዚአብሔር እኮ ለሚያምኑም ለማያምነውም ነው እኩል ቀንና ሌሊትን የሚያፈራርቀው! ሁላችንም ሰው የተባልን ሁሉ ተመሳሳይ አየር ነው የምንተነፍሰው! ማንም ለእግዚአብሔር ሲል ማስ*ገደድ አይችልም። እግዚአብሔርም እንደዚህ አያዝም! የማያምኑ ወደ እርስዋ ከመጡ ቤተክርስቲያን አምስቱን አዕማደ ምስጢራትና ሰባቱን ሚስጥራተ ቤተ ክርስቲያን አስተምራ ልጆችዋ ታደረጋለች እንጂ በጉልበት ፈጽማ አታውቅም። ሆኖም ግን የውሸት ታሪክ በማንሳት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ጨቋኝ እንደ ነበረች ይከሳሉ። የሚከሱበት ምክንያት ቤተክርስቲያንን ለማ*ጥፋት እንዲያመቻቸው በሴራ ነው።
ኢትዮጵያ ሀገረ እግዚአብሔር ናት ስንል የሚያንገሸግሻቸው እጅግ ብዙ ናቸው። ግን ቢመራችሁ ዋጡት እንጂ እውነታው ኢትዮጵያ ሀገረ እግዚአብሔር ከሀገርም ሁሉ የተለየች ናት! እስኪ በመላው ዓለም ዘወትር ሌሊት ኪዳን ፳፬ ሰዓትም ጸሎት የማይቋረጥበት ዓመቱን ሙሉ ቅዳሴ የሚቀደስበት አንድ የፈረንጅ አገር አምጡልኝ! እስኪ አሜሪካ ወይንም አውሮፓ ውስጥ የምትኖሩ ሞግቱኝ! ምስጢረ ስላሴን ሳያፋልሱ በዶግማ ከእኛ ጋር የሚመሳሰሉ እህት አብያተ ክርስቲያናት ያሉባቸው ሀገሮች ቢሆኑም እንኳን እንደ ኢትዮጵያ በፍጹም አይሆኑም! ወዳጄ ከእኛ እጅ ላይ ብትወድቅም ኢትዮጵያ ልዩ ናት! ምንም እንኳን የመከራዋ ቀንበር ቢበዛባትም ልጆችዋ እሾ*ህ አሜ*ካላ ቢሆኑባትም እግዚአብሔር ሥራውን ሊሰራባት የተመረጠች ስለሆነች ይህን የመከራ ዘመን ትሻገረዋለች። በአሁኑ ሰዓት ስለ ኢትዮጵያ ትንሳኤ ስንናገር የሚያማቸው ጥቂቶች አይደሉም። እነዚህ ኢትዮጵያ ወድቃ እንድትቀር የሚፈልጉ ውድቀቷንም ለማራዘም የሚጥሩ ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ ደግሞ ኢትዮጵያ ትነሳለች ስንል የሚናደዱት ስለ ኢትዮጵያ ምስጢር የማያውቁና ተስፋ የሌላቸው ናቸው። የኢትዮጵያ መነሳት ዘመኑ መድረሱን ያወቀው ጠላት ዲያብሎስ ዋዜማዋን ጠብቆ ሀሳዊያንን (እንደ ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃንና እህተ ማርያም) ያሉትን በማስነሳት ህዝብ ግራ እንዲጋባና እንዳይነቃ ለበርካታ ዘመናት ዓለም የምትጠበቀውን ተስፋ ስለ ትንሳኤ ስናወራ እንዲጸየፉትም አድርጓል:: በነገራችን ላይ እውነት ሊገለጥ ሲል ውሸት ዙሪያውን ይከባል! ጊዜው በመድረሱ እውነት ግን አይቀርም ይገለጣል:: ግን ሁላችሁም እያንቀላፋችሁ መድረሱ ዋጋ የሚያስ*ከፍላችሁ ይሆናል!
ስለ ኢትዮጵያ ምስጢር የተሰወ*ረባቸው በዋናነት የቤተክርስቲያን አገልጋይ ነን የሚሉ ናቸው። እነዚህ የዘመኑ የስልጣን ጥ*ምና ም*ቾት የጋረዳቸው ስለሆኑ ቢቀሰቅሷቸው እንዳይሰሙ ሆነው ተኝተዋል:: አንድ ከክፍለ ሃገር የሄደን መርጌታ ለመቅጠር እስከ አምስት መቶ ሺህ ብር ጉቦ የሚጠይቅ ራሱን የቤተ ክርስቲያን ጠባቂ ያደረገ አካል ስለ ኢትዮጵያና ቤተ ክርስቲያን ምን ያስጨንቀዋል? ግልባጩን ለአዲስ አበባ ቤተ ክህነት አድረሱልኝ! ይገባችኋል ብዬ አምናለሁ አ! በነሳዊሮስ የሚመራው የብልጽግና መፈንጫ የሆነው ቤተ ክህነት ኢትዮጵያ እንድትነሳ አይፈልግም። ፍትህን አምባገነኖችና ሙሰኞች እንዴት ይፈልጉታል? ልታውቁት የሚገባው ነገር እግዚአብሔር ያዘጋጀው ጅ*ራፍ ለቤተ መንግስትም ለቤተ ክህነትም ነው! ወደ ሰማይ ብትወጡ ወደ ምድር ብትወርዱ ከፍርዱ አታመ*ልጡም! ልባችሁ ስለደ*ነደነ አሁን ምንም አይመስላችሁም፤በኋላ ግን መሪር እንባን ታነባላችሁ የተወለዳችሁበትን ቀን ትረግማላችሁ። በኢትዮጵያና በቤተክርስቲያን ላይ የሰራችሁት ግ*ፍ ቀላል እንዳይመስላችሁ! ቤተ ክህነት እንደ ቤተ መንግስት የወንበ*ዴዎች መፈ*ንጫ ከሆነች ቆይታለች። አንዳንድ ሰዎች አባቶችን አትገስጹ ይላሉ። ብሎ ነገር የለም! ይሁዳም ሀዋሪያ አርዮስም ጳጳስ ነበሩ። ከተሳሳቱ ሳቱ ነው። አንዳንድ ሰዎች ጳጳሳትን ከእውነት መንገድ ከመልካም እረኝነት ሲርቁ ስንገስጽ ሲሰሙ ቤተክርስትያንን የሰደብን የሚመስላቸው ስላሉ ማጥራት ይኖርብኛል። ቤተክርስትያን በአምስቱ አዕማደ ምስጢርና በሰባቱ ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን የተመሰረተች ናት እንጅ በአንድ ጳጳስ ወይንም ፓትርያርክ ላይ የተመሰረተች አይደለም። የጳጳሳትንና የፓትርያርክን ስራ ምን እንደሆነ ሁላችንም እናውቃለን። ስለዚህ ለእውነት መቆም ትክክለኛ የበጎች ጠባቂ መሆናቸውንም ማሳየት አለባቸው። ሲቀጥልም ከሙስናና ብልሹ አሰራር መራቅ ነበረባቸው:: ሰማያዊ ንጉስን እንጂ ምድራዊ ንጉስን መፍራት የለባቸውም። እነርሱ ግን የብልጽግና መንግስት ጋር እስካሁን ድረስ የጫጉላ ሽርሽር ላይ ናቸው:: ስለዚህ ህዝብን ከሚጨ*ፈጭፍ አምባገነን አገዛዝ ጋር የሚወግኑ አባቶችን ልክ እንደ አገዛዙ እንታገ*ላቸዋለን። ቤተክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅሯ አሁን ምን ላይ እንደሆነ ለሁላችንም ምስጢር አይደለም! በቤተመንግስት ያለው ሙስናና ብልሹ አሰራር በቤተ ክርስቲያንም ገብቷል። ምክንያቱ ደግሞ መንግስት ቤተክርስቲያንን የፖለቲካ መነሀሪያ ስላደረጋት ነው። በአሁኑ ሰዓት መንግስት ቤተክርስቲያንን በሁለት አይነት መልኩ እየተዋጋት ይገኛል። አንደኛው በቀጥታ ኃይል በመጠቀም ገዳማትን በማ*ፍረስ፣ ካህናትንና መነኮሳትን እንዲሁም ምዕመናንን በመጨ*ፍጨፍ፣ በብሔር በመወሰን በህዝብ ዘንድ ጥላቻን በመዝራት አንድ ሆነው እግዚአብሔርን በፍቅር እንዳያመልኩ በመለያየት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ጠቅላይ ቤተክህነትን በመጠቀም የራሱ የሚላቸውን ሰዎች በማስገባት የቤተክርስቲያንን አስተዳደራዊ መዋቅርን በማዛባት ሃይማኖታችንን ህልውናዋ መፈታተን ነው። በቤተ ክህነት በኩል የመንግስት አካሄድ እጅግ አደገኛ ሲሆን ህዝብንም ግራ የሚያጋባ ተስፋ የሚያስቆርጥ ነው። በብዛት በአሁኑ ሰዓት ህዝበ ክርስቲያኑ ተስፋ ቆርጦ ግደለሽ ሆኖ የተቀመጠው በዚህ ምክንያት ነው። ብዙዎቹ እግዚአብሔር ያስተካክለው እንጂ እኛማ ምን አቅም አለን ብለው ተስፋ ተስፋ ቆርጠዋል። መንግስትም የሚፈልገው ይህን ነበር በእርሱ መንገድ ለጊዜው ተሳክቶለታል:: እግዚአብሔር ግን ለሁለቱም ጅራ*ፍ አዘጋጅቶላቸዋል!
ወደ ቀድሞ ነገራችን እንመለስና ምንም እንኳን መከራ ውስጥ ብትሆንም ኢትዮጵያ መነሳቷ የማይቀር ነው። እግዚአብሔር ኢትዮጵያን የሚያስነሳበት ምክንያት ሥራ ስለሚሰራባት ነው:: ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ግብጽ በተሰደደበት ጊዜ የኢትዮጵያን ኮረብታዎች ማለትም የብሉይ ኪዳን መስ*ዋዕት የሚሰ*ዋባቸው የነበሩትን በጎበኙ ወቅት በፈቃዱ የእናቱ የውርስ ሀገር እንድትሆን አድርጓታል። ይህም ሀገራችን በእመቤታችን ጥላ ከለላ ውስጥ የምትኖር መሆንዋን መዘንጋት የለብንም። ኢትዮጵያ በጨለማው ዘመን ለዓለም ህዝብ ብርሃንን የምትገልጥ ናት። ኢትዮጵያን ተራ ሀገር አድርጋችሁ የምታስቡ ሁሉ የእርሷን ልዕልና ለማየት እድል ፈንታ ይኖራችኋል ብዬ አላስብም። እግዚአብሔር ከሀገር ሁሉ መርጦ ለኢትዮጵያ ለምን የሀገር ትንሳኤ ሰጣት? ብላችሁ ለምታስቡ መልሱ ቀላል ነው:: ሥራ ስለሚሰራባት ነው! ይህቺ ሀገር ለዓለም ሁሉ አምባ መጠጊያ መሸሺያ እንደምትሆን ትውፊት፣አዋልድ መጽሐፍትና መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራሉ። ኢሳ. ፲፰፥፩-፰
ኢትዮጵያ አትነሳም ብሎ የሚያስብን እንዲህ በሉት፡- አትነሳም ያልካትን ኢትዮጵያን አንተ መነሳቷን ማየት እድሉ ላይግጥምህ ይችላል እንጂ እርሷሥ በቅርብ ትነሳለች፤ በቅርብ በጣም በቅርብ! አብዛኛዎቹ ስለ ኢትዮጵያ ትንሳኤ ስንናገር ለምን ዘገየ ታዲያ ወዴት ቀረ እያሉ የሚሳለቁ አሉ። እነዚህ ሰዎች ግን ትንሣኤው እንዲመጣ የበኩላችሁን ምን አድርጋችኋል ስንላቸው መልስ የላቸውም! የኢትዮጵያን ትንሳኤ ለማየት ብዙ መስዋዕት እንዳያስከፍለን ሁላችንም የበኩላችንን ድርሻ መወጣት ይኖርብናል። ከጸሎት ጀምሮ ንስሐ በመግባት፣ከዘረኝነት፣ከስርቆት፣ከሌብነት፣ከክህደት፣ ከዝሙትና ከስልጣን ጥም ወዘተርፈ ልዩ ልዩ ከሆኑ በምድር ላይ ቁጣን ከሚያመጡ የጥፋት ስራዎች በመራቅና ትንሣኤውን ለማምጣት አምባገነኖችንንም ለመግ*ታት እንደ ቀድሞ አያቶቻችን በተባበረ ክንድ በመነ*ሳት የመክራችንን ጊዜ ማሳጠር እንችል ነበር። ግን አሁን እንደምናየው ሁሉም በየፊናው በጥ*ፋት መንገዱ እየነጎደ ይገኛል። ስለዚህ እንደ እስካሁን ከአንቀላፋን ትንሣኤውን ለማምጣት ከፍተኛ ጥፋት ይኖራል ማለት ነው። እንዲህ ስንናገር ለጆሯቸው የሚከብዳቸው አሉ ግን ምንም ማድረግ አይቻልም ሊሆን ግድ ነው!
የኢትዮጵያ ትንሳኤ አንዱን የበላይ አንዱን የበታች የሚያደርግ አይደለም። የኢትዮጵያ ትንሳኤ ፍቅርና አንድነትን የሚያመጣ ሰው ሰብአዊ ፍጡር በመሆኑ ብቻ ተከብሮ እንዲኖር የሚያደርግ ነው። በምድር ላይ ፍቅር ካለ እግዚአብሔር ምህረቱን ያወርዳል:: ያኔ የስጋም የመንፈስም እድገት ይኖራል፤ ትንሳኤ ማለትም ይህ ነው። ለሰው ልጅ ጥፋት ምክንያት የሆኑ አምባገነኖች በኢትዮጵያ ምድር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የ *ሚ *ወ* ገ *ዱ *በ* ት ጊዜው አሁን ስለሆነ ከአንቀላፋንበት ነቅተን በማንኛውም መልኩ ልን*ነሳ ግድ ይለናል። ከአምባገነኑ አገዛዝ ጋር ወግነው ኢትዮጵያ ወድቃ እንድትቀር የሚሰሩ ሁሉ ትንሳኤዋን አያዩም። አንዳንዶች እግዚአብሔር የኢትዮጵያን ትንሳኤ እንዲያይ ቢፈቅድላቸው እንኳን የማይበርድ ጸጸት ይሆናቸዋል በምድርም ዋጋ*ቸውን ይከፍላቸዋል ፤ታሪክም ሲወቅሳቸው ይኖራል:: ሁሌ እንደምናገረው ሰማይ ዝቅ ምድር ከፍ ቢሉ እንኳን ኢትዮጵያ እንደወደቀች አትቀርም። በጊዜያዊ ጥቅምና በተሳሳተ ትርክት ተታላችሁ ከዚህ አምባገነን መንግስት ጎን የሆናችሁ ሁሉ ለራሳችሁ ስትሉ ንቁ። ይህ ስርዓት ለኢትዮጵያውያን የማይበጅ ኢትዮጵያን የሚያ*ፈርስ አንድነታችንን የሚንድ የጥ*ፋት ስርዓት ነው። ሁላችሁም መልካሙን ቀን ማየት የምትሹ ሁሉ ከእውነት ጎን መቆም ይኖርባችኋል። ጊዜው አሁን ነው ፍጠኑ!
አምባገነኖች ይወድቃሉ ኢትዮጵያ ግን ትነሳለች:: ድል ለኢትዮጵያ!
Blogger Comment
Facebook Comment