♰ የሺህ አራት መቶ/ 1400 አመት እድሜ ያለው መስቀል የኢየሱስን ስቅለት የሚያሳይ ቦታ በዘር አጥፊዋ በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ተገኘ



✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ አውታር    

☪ እስልምና፤ ሙስሊሞች ክርስቲያኖችን ሁልጊዜ ገድለዋል፣ እየጨፈጨፏቸውም ነው።

👹 ሳሂህ ሙስሊም 1767a (መፅሐፍ 32 ሀዲስ 75) 11703

👹 የጂሃድ መጽሐፍ እና ጉዞዎች (21)

ምዕራፍ፡ አይሁዶችንና ክርስቲያኖችን ከዓረብ ባሕረ ገብ መሬት መባረር (21)

" ዑመር ብን አል-ከቲብ ዘግበውታል የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ሲሉ ሰምተዋል፡- አይሁዶችንና ክርስቲያኖችን ከዓረብ ባሕረ ገብ መሬት አወጣለሁ ከሙስሊም በስተቀር ማንንም አልለቅም።"

👹 በባቢሎን ኤሚራቶች ዋና ከተማ በአቡ ዳቢ አቅራቢያ ጥንታዊ የክርስቲያን ቅሪቶች ተገኙ

ሲር ባኒ ያስ በተባለ አቡ ዳቢ አቅራቢያ በምትገኝ ደሴት ላይ የተገኘው ይህ ቅሪት፣ በጭቃ ቡኪት የተሰራ የመስቀል ቅርጽ ነው። ቅርሱ የሺህ አራት መቶ/1400 ዓመታት ታሪክ እንዳለው ተነግሯል። ግኝቱ ወንጌል ወደ ምስራቅ የዓለም ክፍል እንዴት እንደተስፋፋ ፍንጭ ይሰጣል ተብሏል።

ቅሪቱ የተገኘበት አካባቢ ጥንታዊ የአብያተ ክርስቲያን እና ገዳማት ፍርስራሽ ይገኛል። ግኝቱ በአካባቢ እስልምና ከመስፋፋቱ በፊት በአካባቢው ተስፋፍቶ የነበረውን ክርስትና ያሳያል ተብሏል።

ቅሪቱን ያገኙ አርኪዮሎጂስቶች ክርስትና በአካባቢውመኖሩን ብቻ ሳይሆን በስፋት እንደነበረ ያሳያል ብለዋል። ቅርሱ ሃያ ሰባት/27 ሳንቲም በአስራ ሰባት/17 ሳንቲም የሆነ እና ሁለት/2 ሳንቲም ስፋት ያለው እና ይንጠለጠል የነበረ መሆኑን ያሳያል።

በአቡ ዳቢ አካባቢ የነበሩ ክርስቲያኖች ከእየሩሳሌም እስከ ህንድ እና ቻይና የተዘረጋው ክርስትና መሸጋገሪያ ነጥብ መሆናቸውን ያሳያል ተብሏል። ከስፍራው ወንጌል ከዓረብ ባህረ ሰላጤ በኩል አድርጎ ወደ እስያ ለመስፋፋቱ መነሻ ስፍራ ነበረ ተብሏል።

በአካባቢው በ፲፱፻፺/1990ዎቹ የክርስትና እምነት ቅሪቶች መገኘት የጀመሩ ሲሆን፣ በ፳፻፳፪/2022 በዚያው አቡ ዳቢ አካባቢ፣ ኡም አል ቁዋይን በተባለ አካባቢ ጥንታዊ ገዳማት መገኘታቸው ይታወሳል። ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው ገዳማት በኩዌት፣ ኢራን እና ሳውዲ ዓረቢያ ተገኝተዋል።

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment