✍ ቲና በቀለ | ኢትዮጵያ አውታር
ከመጽሐፈ ብርሀን/ ከኢትዮጵያውያን ጥበብ የተሰረቀው
የአልበርት አንስታይን (E=mc^2) ቀመር
መላዕክት ግዮን/አባይ የጣሉት መጽሐፍ...ጊዜን የሚያፈዝ ብርሀን....
አልበርት አንስታይን(E=mc^2) ቀመር በኢትዮጵያን መፃህፍት ላይ በስፍት እና በምላት ተቀመጦ እንደሚገኝ ስንቶቻቹ ታውቃላቹ?!
የአልበርት አንስታይን ሁለት ቲዩሪዎችንን አስቀምጧል አንደኛው general relativity እና special relativity ሲሆኑ አጠቃላይ ሀሳቡ በብርሀን ፍጥነት በምንኖርበት ሁኔታ ላይ የጊዜ ልዩነት እንደሚኖር ያስረዳበት ነው። ይህ ቲዬሪ አልበርት 1905 እ.ኤ.አ ነበር። አገኘሁት ያለው ነገር ግን የኛ አባቶች በአራተኛው(4) ክፍለ ዘመን ከአልበርት 1600 አመታት በፊት ነበር በመፃህፈ አክሲማሮስ ላይ እንዲህ በማለት አባቶቻችን የፃፉት "በላይ ሰማይ ላይ መላእክት ሲሰግዱ አየሁ እነሱ አንድ ሰዓት ሰገዱ በምድር ደግሞ 83 አመት አለፈ" ብርሀን ባለበት ቦታ ጊዜ ይፈዛል ማለት ነው። ብርሀን ያለበት ቦታና ብርሀን የሌለበት ቦታ ሰዓት የተለያየ ነው እንዲሁም Speed(ፍጥነቱ) ይለያያል። አንስታይ time dilution and speed የሚለው ይህን ነው።
Black Hole ምስጢራት ላይ ለሚደረገው ጥናት ለምእራባውያኑ ፍንጭ የሰጠው Einstein's general relativity (GR) ንድፈ ሃሳብ ቢሆንም ከአልበርት አንስታይን ንድፈ ሃሳብ በተሻለ ግን ስለቦታዎቹ ማብራረት የሚቻለው መጽሀፈ-ራዚኤል ወይም የህይወት መጽሀፍ ብለን የምንጠራው ነው። (በነገራችን ላይ ይህ book of life የሚባለው መፀሀፍ በአንድ የሆሊውድ ፊልም the davincis Demons ላይ መጽሀፉን ፍለጋ ወደ አቢሲኒያ የአሁኗ ኢትዮጰያ ገዳማት ላይ ይህንን መፃህፍ ፍለጋ ሲታትሩ ይታያል) ይህ መጽሀፍ በአራቱ ሰማያት መካከል ያለውን የሃይል የጊዜ እና የግዝፈት ልዩነት ያስረዳል፡፡
የእዚህችን ዓለም ምስጢራትና ጥበባት እና በውስጧ ያሉትን የተለያዩ ስውር ሃብታት 12ቱን ወር ሶስት ሶስት ወር በመከፋፈል የሚጠብቁ መልአክት አሉ፡፡ የነገድ አለቃቸው ራዚኤል የተባለ መልአክ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ አናንያኤል ይባላል፡፡
ታዲያ አዳም በድሎ ወደ ምድር ሲጣል ይህ መልአክ አዳም የምድርን ምስጢራትና ጥባበት ይጠቀም ዘንድ በዚች ምድር ላይ ስለሚገኙት ምስጢራትና ጥበባት በመጽሀፍ አዘጋጅቶ ቢሰጠውም ፈቃደ እግዚአብሔርን ባለመጠየቁ ሌሎች መላእክት ይህን መጽሀፍ ከአዳም ተቀብለው ወደ ምድር ይወረውሩታል በቀጥታም ይህ መጽሀፍ ግዮን የተባለ ወንዝ ውስጥ ይወድቃል ይህ ግዮን የተባለው ወንዝ የኛው አባይ ነው፡፡ ከወደቀ በኃላ መልአኩ ራዚኤል ከእግዚአብሔር ይቅርታን በማግኘቱ ይህን መጽሀፍ አዳም ተመልሶ ሊያገኘው ችሏል፡፡
መረጃወች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ይህን መጽሀፍ ከአዳም ቀጥሎ ኖህ፣ ከኖህ ሔኖክ፣ ከሔኖክ ደግሞ ጠቢቡ ሰለሞን እጅ ደረሰ። ይህም መጽሀፍ አዳም የጻፈው መጽሀፍ ሲሆን አዳም የእሳት ዓለማት ውስጥ የሚገኙት ቅዱሳን መላእክት ያስተማሩትን ጥበብ ያሰፈረበት ነው፡፡
አዳም እኛ በምንኖርባት ምድር እና በገነት መካከል ያለውን የሃይል የጊዜ እና የግዝፈት ልዩነት ውጭ ሆኖ በሁለቱም ዓለማት ላይ መኖር የቻለው መላእክቱ ባስተማሩት ጥበብ፡፡ ይህም አዳም ገነት በኖረበት ሰባት ዓመት እና በምድር 2555000 ሚሊየን ዓመት መካከል ያለውን የሃይል የግዝፈት እና የጊዜ ልዩነት አስማምቶ መኖር ችሏል፡፡
በዛም መሰረት አዳም ወደ ምድር ሲመጣ ሰባት አመት እንዳሳለፈ ሰው እንጂ በምድራዊ የጊዜ አቆጣጠር 2555000 ሚሊየን ዓመት እንዳሳለፈ ሰው ሆኖ አይደለም ወደ ምድር የመጣው።
Blogger Comment
Facebook Comment