ምዕራፍ ሁለት ~ የተባበሩት መንግሥታት - የተ.መ. (UN)
ሚያዚያ 17/1937 (25th April, 1945) በሳን ፍራንሲስኮ የሃምሳ ሀገራት ልዑካን የተባበሩት መንግሥታት የዓለም አቀፍ ድርጅት አንድነት (United Nations Conference on International Organisation) ብለው በሰየሙት ስብሰባ ተገናኙ። ከዘጠኝ ሳምንታት ኃይለኛ ውይይት በኃላ ባለ አሥር ሺህ ቃል ቻርተር በሁሉም ልዑካን ፀድቆ አለፈ። ልክ በአራት ወሩ ጥቅምት 14 (October 24th) አባላቱ ሁሉ ከተፈራረሙ በኋላ የተባበሩት መንግሥታት በይፋ ተቋቋመ። የዚህ ድርጅት ርእይ በጥቅሉ “ሰብዓዊነትን በአንድ ጎጆ” (“humanity under one roof”) እና በመሳሰሉት መልካቸውን ባሳመሩና መልካም አስተሣሰብ ያላቸው ሰዎች በምንም መልኩ ሊቃወሟቸው በማይችሏቸው መፈክሮች የተሸፈኑ ናቸው። የዚህም ድርጅት የተከለሰና ዓለም አቀፋዊ የሆነውን ርዕይ በ1940 ዓ.ም. (1948) “የሰብዓዊ መብቶች ሁለንተናዊ መግለጫ” (Universal Declaration of Human rights) በማለት ይፋ ያደረገ ሲሆን አሁንም እንደተለመደው የተጠቀሙት ቋንቋ የሚቃወመውን ማንኛውም ሰው እንደግብዝ እና ቅንነት እንደጎደለው አድርጎ በሚያስቆጥር መልክ በጥንቅቃ የተዘጋጁ ነበሩ። የተ.መ. ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ በማንኛውም የተፈጥሮ አደጋም ሆነ “አምባገነን መንግሥታት” በሕዝቦቻቸው ላይ “ከመጠን ያለፈ ኃይል” በሚጠቀሙበት ወቅት በቅድሚያ የሚጠራ ደርጅት ሆኗል። ይህ መልካም ዓላማ እንደ ቢቢሲ ባሉ “ተዓማኒ” ምንጮች [ድብቅ አጅንዳቸውን ለማያውቅባቸው ብዙኃን ሕዝብ ተአማኒ የሆኑ] የሚቀርብ ነው። በመሆኑም ምርመራ በማይደረግባቸው የተቋማትና ቡድኖች በኩል የተ.መ. በእያንዳንዱ የሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ ራሱን ማስገባት ችሏል። ነገር ግን በቀጣይ እንደምንመለከተው እውነታው በእጅጉ ከዚህ የራቀ ነው። የተ.መ. የተቋቋመው እንደ የሉሲፈር ትረስት (Lucifer Trust) መሥራች ኤሊስ ቤይሊ (Alice Bailey) ያሉና ሌሎች ዓላማዋን በሚደግፉ መሰል ሰዎች ነው። እነዚህ ሰዎች ማስፈን የሚፈልጉት የአዲሱ ዘመን መርህ (New Age principles) የተባሉና ከክርስትናና ከማንኛውም ሰብአዊ አስተምህሮ የሚቃረን ፍልስፍና ላይ የተመሠረተ ነው።
ያህል ሰብአዊ ሕግን ብንደነግ ለዚህ ዓለም ሰላምን ልናመጣ አንችልም። [የሰው ልጅ ጦርነት ለመጀመርና ለማካሄድም ስሜቱን በመከተል አንደየርእዮተ ዓለሙ “ጦርነት የመጀመርና የመዋጋት ሕግ” ብሎ ይጽፋል ይገብራል።] ግጭትን ሊያርቅ የሚችለው በውስጣችን ገብቶ ሥራውን በሚሰራ በመንፈስ ቅዱስ ብቻ ስለሆነ። የተ.መ. በተመሠረተበት ቻርተር ራሱን “የሰው ልጅ ከጦርነት መከራ የሚድንበት ብቸኛው መንገድ” በማለት ይሰይማል። ስለዚህም የሰውን ልጅ በሰው ልጅ ጥረት ለማዳን ይጣጣራል። ተ.መ. የሰው ልጅ ፍላጎቱን የተሟላ ማድረግ የሚችለው አመክንዮአዊ አቅሙን በመጠቀም ብቻ ነው ይላል [ይህ ምልከታ የመገለጥ እውቀትን እና የመንፈስ ቅዱስን ሥራ የዘነጋ ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅ የፍላገቱና የስሜቱ ሎሌ በመሆን የመኖር ትርጉሙ ሁሉ ሥጋዊ ፍላጎቱን ማሟላት ብቻ አንደሆነ የበየነ ነው]።
አንድን የዓለም አቀፍ ሕግ ከሌላው ሁሉ በላይ እንደሆነ ተቀብሎ የበላይነቱን ለማስከበር መላው ዓለም የሚስማማበት እውነት፣ እውነት የምትገለጥበት እሴት፣ የእውነት ምንጭና ባለቤት ላይ መስማማት ያስፈልገዋል። ታድያ ክርስቲያናዊ እሴቶች ከዚህ ዓለም ሊሆኑ ስለማይችሉ ክርስቲያኖች ከዚህ ዓለም የአገዛዝ ሥርዓት ጋር መቃረናቸው አይቀሬ ነው። እዚህ ላይ ጥንቁቅ ልንሆን ይገባናል፣ ምክንያቱም “እውነት ከሰላም የበለጠ ዋጋ አለውና” ። በተ.መ. መርህ መሠረት የዓለም አቀፍ ሕግ መደንገግ የሚገባው የሰው ልጆች ፍላጎትን ለመፈጸም በሚያስችል እሴት ላይ በመመሥረት ሲሆን ይህ ክርስቲያናዊ [ኦርቶዶክሳዊ] ከሆነ እሴት ጋር ፈጽሞ ይጋጫል፡፡ ምክኒያቱም ከእግዚአብሔር የተገኘ የተፈጥሮ ሕግ መኖሩን ፈጽሞ የሚክድ በመሆኑ ነው። በእርግጥ የወደቀውና የጎሰቆለው የሰው ልጅን ፍላጎቱን ለመሙላት በሚያወጣው ሕግና በእግዚአብሔር ፈቃድ መካከል ምንም አይነት መጣጣም ሊኖር አይችልም። በተ.መ. ዶግማ መሠረት ግን የጎስቋላውን የሰው ልጅ ዕሳቤ ሕግ አድርጎ በዓለም ሁሉ ላይ ሊጭን ይታገላል። [ለዚያውም እንዚህ ሕግ አውጭዎች ከመነሻቸውም እግዚአብሔርን ከሰው ልጆች የአስተዳደር ሚና በማሰወገድ በአውሮፓው የ17ኛውና 18ኛው መቶክፍለዘመን የአብርሆት ምርህ እየተመሩ የሚደነግጉትን ሕግ ከሁሉ በላይ እንዲሆን አገራት በጦርነት እስከማፍረስ ይራመዳሉ።] እዚህ ላይ ነው ክርስቲያኖች አደገኛ የሆነ ወጥመድ የሚገጥማቸው ። ይህን ልዩነት ለማስወገድ የተ.መ. በሕጎቹ ውስጥ የተለያዩ የምንፍቅና አይነቶችን ብቻ ሳይሆን የሁሉንም እምነቶች መርህ ለማርካት ይጥራል። የተ.መ. የተለያዩ ሥራዓተ እምነቶች ያሏቸውን እሴቶች ቀስ በቀስና ደረጃ በደረጃ በመጣል እንዲጠፉ የሚሠራ አካል ነው። ይሀን ለማስፈጸም የተለያዩ ስምምነቶችን በመንግሥቶቻቸው በኩል ያስፈርማቸዋል ። ስምምነቶቹን ሲፈጽም ዓለም አቀፋዊ ሊያደርገው የሚፈልገውን እሴት በራሳቸው እንዲተኩ ያስገድዳል። አይነኬ ከሆነው ቀኖናቸው ጋር ጥብቅ ቁርኝነት ያለቸው የእምነት ተቋማት የተ.መ.ን እሴቶች እና ፍላጎቶች የማይቀበሉ ከሆነ የወንድማማችነትን፣ የአንድነትን እና የፍቅርን እሴት የማይቀበሉ ተደርገው እንዲታዩ ማድረግ አንዱ ስልቱ ነው። በቀጣይ እንደምናየው “የእምነቶች የአንድነት ጉባኤ” የኦርቶዶክሳዊነትን የተለየ መልዕክት ለማጥፋትና ክፉ ገፅታ ለመስጠት ሆን ተብሎ የተመሠረተ ነው።
ማስተዋል ማጣት የተ.መ.ን የዓለም አቀፍ ሕግ መሠረታዊ አካል የሆነውን የጋራ እሴትን የመያዝ አስተሳሰብ ወደ መቀበል ይመራናል። ሀገራት የራሳቸውን የእምነት ሥርዓትና የሥነ-ምግባር መሠርት የሚያስቀጥሉ ከሆነና የአንዱ ሀገር ከሌላው ጋር ፈጽሞ የሚፃረር ከሆነ በምን መልኩ ነው ይህ ዓለም አቀፍ ሕግ ወደ አዲሱ የማኅበረሰብ ሥርዓት ሊጠቀልላቸው የሚችለው? መሠረታዊው ጥያቄ ሕግ “አውጪዎቹ የጋራ መሠረት የሚሆናቸው እሴትና ርእዮት የሚያገኙት ከየት ነው? እነዚህስ ሕጎች ሊመሠረቱበት የሚገባው የጋራ እሴት ምንጭና ይዘት የትኛው ነው? የሚለው ነው። ቻይና ከብዙ ምዕራባውያን ሀገራት ጋር የምትጋራው እሴት ባይኖራት እንኳን ኃያል ሀገር በመሆኗ በተ.መ. የራሷን ሚና ትጫወታለች። ምክንያቱም ይህ ዓለም አቀፍ ሕግ እንዲሠራ ኃያል ሀገራት በጫዋታው ተሳታፊ ሊሆኑ ይገባል። ይህ አሠራር የዓለም አቀፉ ሕግ መሠረቱን የጣለው በጋራ እሴትና መርህ ላይ ሳይሆን በአሸናፊዎች ፍላጎትና ፈቃድ ላይ መሆኑን ያመላክታል። የተ.መ. ሥነ-ምግባርን እና እውነትን መሠረት ያደረገ ሳይሆን የኃይል አጠቃቀም ላይ ያተኮረ ነው። [የኃይሉ ምንጭ ምንም ይሁን ምን፣ የሚገኘው ከዘረፋ፣ ዘር ከማጥፋት፣ አገራትን ቅኝ ከማድረግ፣ ሰውን ባሪያ አድርጎ በመግዛት፣ በማታለልም ይሁን “ኃይለኛ” (ሌላውን ማሸነፍና ማዋረድ መቻል) የሆነ አገር የሚመሩ የፖለቲካ ልሒቃን የተሸናፊዎቹን አገር የፖለቲካ ልሒቃን በውክልና እየተጠቀሙ ዜጎችን እሴት፣ እምነት፣ ባህልና ሥርዓት፣ የአስተዳደርና የፍትሕ መንገድ ሁሉ ይደመስሱታል።]
የተ.መ. መሠረታዊ ችግር ተቃውሚ እንዳይገጥመውና ድብቅ አጀንዳውን ለማስተግበር የግድ ራሱን “ሰብዓዊነት” በሚል ጥላ ሥር ቆሞ መገለጥ መሆኑ ነው። ሰብዓዊነት (Humanism) ደግሞ የሰው ልጅ ፍላጎቱን ለሟሟላት ዓለምን በራሱ በተረዳው እይታ መጠንና መንገድ የመቅረጽ አቅም አለው ለሚለው የአብርሆት ዕሳቤ ነፀብራቅ ነው። የተ.መ. ቻርተሮች “ሁሉም የሰው ልጅ የተ.መ.ን መርህ ተቀብሎ በእርሱ መኖር አለበት” በማለት ገልጦ ያስቀምጠዋል። በቻርተሩ ላይ ፊርማቸውን ያላኖሩ ሀገራት እንኳን ተገደው በዚህ መርህ መሠረት እንዲንቀሳቀሱ ይደረጋል። ለምሣሌ የተ.መ. “የሰብዓዊ” “መብት” መግለጫ እንደሚያስቀምጠው በአንድ ሀገር ባሉ እምነቶች መካከል እኩልነት ሊኖር ይገባል ይላል። ታድያ እያንዳንዱ ሀገር የራሱ የሆነ በሕግና በባሕል የተገለጠ የእምነት መዋቅሮች እና የማንነት ልዩነቶች አሉት። ነገር ግን የተ.መ. ዓለም አቀፋዊ ያለውን አይነት የሰው ልጅ ማንነት ለመጫን ሲል እነዚህን ሁሉ ደምስሶ ያጠፋል። ሰብዓዊነት የተለያዩ እምነቶች እና ሥነ-ምግባራት መኖራቸው የሰው ልጆችን ይከፋፍላል የሚል አቋም አለው፤ የሰው በአንድ ቋሚ ሥርዓት ወይም ቀኖና መጓዙ እንዲሁም በአንድ ብሔራዊ ማንነት መወሰኑ መልካምነቱን እንዲያጣ ያደርገዋል ብሎ ያምናል።
ዲግሪ ፍሪሜሰን (thirty-second degree Freemason) ፎስተር ቤይሊ (Foster Bailey) የተባለ ሰው የብሔራዊ ቲኦሶፊካል ማኅበር ዋና ጸሐፊ ሆነ [ፍሪሜሰን፦ በ14ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ የተመሠረተ ማኅበር ነው። ትልቅ እና ዓለም አቀፍ ምሥጢራዊ ማኅበር ሲሆን በእንግሊዝ ሥርወ መንግሥት ጋር አብሮ የተስፋፋ ነው። አባላቱ በዓለማችን ትላልቅ የሚባሉ ቦታዎችን እንዲሁም ስልጣኖችን የያዙ ናቸው]። ቤይሊ የሚያናግራት ድምጽና የሚጎበኛት መንፈስ የቲቤት የቡድሃ መምህራን መንፈስ እንደሆነ በእርግጠኝነት ትናገር ነበር። ይህም ከማኅበሩ ለመለየቷ ምክንያት ሲሆን ነገር ግን የማኅበሩን አስተሳሰቦች ማስተዋወቋን እና ማራመዷን ቀጥላበታለች። ቁልፍ ከሆኑት አመለካከቶቿ ውስጥ አንደኛው የሰው ልጆች የአዕምሮ ዝግመተ ለውጥ ከሃይማኖት በላይ ነው ብላ ማመኗ ነው። እንደውም ለሰው ልጆች መከፋፈል ምክንያቱ ክርስትናና ሌሎች እምነቶች ናቸው በማለት ትከራከር ነበር። መሠረታዊ አስተምህሮዋ ኢኪውሚኒዝም ነበር፤ ይህም ማለት በእምነት ተቋማት ውስጥ ከሚታየው ልዩነት በበለጠ አንድነቶቻቸው እና የጋራ እሴቶቻቸው የጠነከሩ ስለሆኑ አንድ ሊሆኑ ይገባል የሚል ነው። በዚህ እምነቱዋ መሠረት አንድ የዓለም ሥርዓት ለማምጣት ያስችላል ያለችውን ባለ አሥር ነጥብ እቅድ ነድፋለች። ከታሪኳ እንዲሁም ከአመለካከቷ ስለማንነቷ ከተረዳን ዛሬ በዓለማችን እየተፈፀመ ያለውና ]በተ.መ. ሕጎችና መርሆዎች የተካተቱት አንጾች] ከአሊስ ቤይሊ እቅድ ጋር ምን ይህል የተቆራኘ እንደሆነ እንመለከታለን።
የቤይሊ የመጀመርያ ነጥብ እግዚአብሔርንና ወደርሱ የሚደረግ ማንኛውም ጸሎት ከሁሉም ትምህርት ቤቶች እንዲወገዱ ማድረግ ያስፈልጋል የሚል ነው። ይህ በአሜሪካ የተሳካ ሲሆን በእንግሊዝ በአብዛኛው ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ ተደርጓል።[በኢትዮጵያም ከ1966ቱ ዓ.ም. አብዮት ወዲህ ተግባራዊ ተደርጎ እስከ ዛሬዋ ኢትዮጵያ ቀጥሏል።] የዚህን ተግባር ዓላማ “ሕፃናት ክርስቲያናዊ ከሆነ ባህል ጋር ቁርኝነት እንዳይኖራቸው ማረጋገጥ ነው” በማለት ትገልጸዋለች። ዓላማው በእግዚአብሔር ማመን አንደትርፍ እንዲቆጠርና በትምህርት ቦታዎችም ትኩረት እንዳይሰጠው ማድረግ መሆኑን በግለጽ ትሞግታለች፣ [የተ.መ. የሳይንስ፣ የትምህርትና የባህል (ዩኔስኮ) ይህንኑ መርህ እንደሚከተል አሁን በዓለም ዙሪያ በታዳጊ አገራት ላይ የሚጫነው የትምህርት ፖሊሲ ይመሰክራል።]።
ሁለተኛው ነጥብ ወላጆች በልጆቻቸው ላይ ያላቸውን ሥልጣን መቀነስ ነው። የእዚህ ዓላማው በእሷ አገላለጽ “በወላጆችና በልጆች መካከል ያለውን ትግባቦት መስበር” ብላ ታስቀምጠዋለች። የክርስትና እምነት አስተምህሮ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፈው በዋናነት በቤተሰብ በኩል [በትውፊት፣ በክርስቲያናዊ አኗኗር፣ በታላቅና ታናሽ የመከባበርና የመደማመጥ ሥርዓት] በመሆኑ የቀደሞውን ለማጥፋት አሁን ያለውን ማጥቃት በሚል አስተሳሰብ ታምናለች። የሚያስገርመው የእንግሊዝ መንግሥታት ጥሩ የሆነ የህፃናት እንክብካቤ እንዲኖር የሚያመቻቹ ሲሆን ከዚህም ባለፈ በእናትና በልጅ መካከል ያለውን ትስሥር ለመበጠስ ታልሞ ልጅ ወልዶ ለማሳደግ የሚሆነውን የቤተሰብ ገቢ ከመጨመር ይልቅ የሰው ልጅ ወስደው ለሚያሳድጉ የገንዘብ ድጋፍ ይደረጋል።
ሶስተኛው የቤይሊ ነጥብ ባህላዊ የሆነ ክርስቲያናዊ የቤተሰብ መዋቅርን የማፍረስ አስፈላጊነትን የሚገልጽ ነው። ባህላዊ የቤተሰብ ሥርዓት በልጆች ላይ ጫናና ቅጣቶችን የሚያበዛ ነገር ግን ለሀገር ግንባታ መሠረት እንደሆነ ታምናለች። ሰዎችንም ከቤተሰቦቻቸው ነፃ በማውጣት የሀገርን መፍረስ ማየት እንደሚቻል ታምናለች። ይህም ዓላማዋ ግብ እንዲመታላት በመገናኛ ብዙኃን በኩል ከበርካታ ሰዎች ጋር ወሲብ መፈጸምን ወይም አመንዝራነት እንዲስፋፋ ትሠራ ነበር። ቴለቪዥንን እና ማስታወቂያዎችን ብንመለከት ይህ ነጥብ ምን ያህል እንደተሳካላት እንረዳለን።
አራተኛው የቤይሊ ነጥብ ውርጃን ለሁሉም ሰው ተደራሽ ማድረግን የተመለከተ ነው። የውርጃ ክሊኒኮች እንዲሁም ተማሪዎች አገልግሎቱን እንዲያገኙ የሚያማክሩ የጤና አማካሪ ክሊኒኮች በየትምህርት ቤቱ ሊከፈቱ ይገባል በማለት ትከራከራለች። አንዳንድ የእንግሊዝ ትምህርት ቤቶች የእርግዝና መከላከያ እንክብሎችን ከቤተሰብ እውቅና ውጪ ለተማሪዎች በነፃ እንደሚያቀርቡ ይፋ አድርገዋል። ቤይሊ ወጣቱ የአመንዝራ ህይወት እንዲኖር ካስፈልግ ይህ አገልገሎት ሊሟላለት እንደሚገባ ተረድታለች። በተጨማሪም ክርስትና ለውርጃ ያለው አመለካከት የሰዎችን መብትና ፍላጎት የሚጋፋ ነው ብላ ታምናለች።
አምስተኛው ነጥቧ ሰዎች በህይወታቸው በጋብቻ ከመወሰን እንዲለዩ ማደረግ ነው። ይህን ዓላማ ባደረገ መልኩ ቤይሊ ቀላልና ፈጣን ፍቺዎች እንዲደረጉ የሚያስችሉ ሥርዓቶችን ታበረታታ ነበር። በዚህ መልኩ የጋብቻ ክብር እንዲሁም ዓላማ ቀሎ እንዲታይ ለማድረግ ያስችላል ብላ ታምናለች።
የቤይሊ ስድስተኛ ነጥብ ግብረሰዶማዊነት እንደ አንድ የአኗኗር ዘይቤ እንዲወሰድ ማድረግ ነው። አሁንም የክርስትናን እሴት እና አስተምህሮ እንደ ጨቋኝ በማየት ሰዎች ነጻ መሆን አለባቸው [በእግዚአብሔር አርአያ የተፈጠሩና በምድር ሲኖሩ ዓላማቸው አምላካቸውን ለመምሰል እና ወደ እርሱ ለመድረስ መሆኑን እንዲዘነጉ ሊደረጉ ይገባል የሚል መርህ አላት] ትላለች፤ ስለዚህም ስምምነት እስካለ ድረስ ከማንኛውም ሰው ጋር ተራክቦ መፈጸም ይችላሉ ትል ነበር። ይህ ከራስ ቤተሰብ ጋር የሚደረግን ተራክቦን እና በአመንዝራነት የተመሠረቱ መቀራረቦች እንዲስፋፉ ይረዳል ብላ ታምናለች። ይህ ደግሞ ከግብ ሚደርስበት ብቸኛው መንገድ “መቻቻል” እና “አቃፊነት” በሚሉ ቋንቋዎች ሲሸፈን እንደሆነ ትገልፃለች። ዋና ዓላምው ግን የፆት ልዩነቶችን ማጥፋት ነው። ታድያ ቀደም ሲል እአአ በ2017 ዓም ፆታ አካላዊ ወይም የተፈጥሮ ጉዳይ ሳይሆን የምርጫ ጉዳይ ተደርጎ ሊወሰድ ይገባል የሚሉ የኢቀኖናውያን ድምጾች ተሰምተዋል።
የእቅዷ ሰባተኛው ነጥብ ኪነጥበብን ማበላሸት የሚል ነው። ኪነጥበብ የማኅበረሰብን ባህል የሚቀርፅ መሣሪያ እንደሆነ በመረዳት የተበላሸ ኪነጥበብን [ከባህል ከወግ እንዲሁም ከሃይማኖታዊ እሴቶች ውጪ የሆኑ ይዘቶችን የያዙ የኪነጥበብ ውጤቶች] በመጠቀምና ለዘብተኛ ሰው በመፍጠር ነባርና ተቀባይነት ያላቸውን የማኅበረሰብ ሥርዓቶች እና እሴቶችን ማጥፋት እንደሚቻል ገልፃለች። ዓይነ ህሊናን በመበከል የሰዎችን አዕምሮ አስሮ ይዟል ካለቻቸው “ጊዜ ካለፈባቸው አስተሳሰቦች” [በእምነት እና በባህል ላይ ከተመሠረቱ አስተሳሰቦች] ማላቀቅ ይገባል በማለት ትከራከራለች። ባህላዊ ኪነጥበብ ሰዎችን መንፈሳዊ ወደሆነ ስሜት ሊያደርስ ይችላል ብላ በማመን ሊወገዱ ይገባልም ትላለች።
የቤይሊ ስምንተኛ ነጥብ የሰዎችን አስተሳሰብ በመገናኛ ብዙኃን በኩል መቀየር ነው። “የሕይወት ዋና ዓላማ መደሰት ነው” የሚል አስተሳሰብ (hedonism) በሰዉ ዘንድ በማስረፅና የቀደመውን ሃይማኖታዊውን የሕይወት ዓላማ በማስጣል አዲስ የሆነ የኑሮ ዘይቤ እንዲፈጠር ጥራለች፣ [ተሳክቶላትም]። “ዊል ኤንድ ግሬስ (Will And Grace)” የተሰኘ ተከታታይ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጆች ሰዶማዊ ገጸባህሪያትን በመጠቀማቸው ከትምህርት እና ከፖሊሲዎች በበለጠ ግበረሰዶማዊነት በአሜሪካ ማኅበረሰብ ተቀባይነት እንዲኖረው ተጽዕኖ መፍጠር እንደቻሉ ተናግሯል።
ዘጠነኛው ነጥቧ ዓለም አቀፍ የሆነ የእምነቶች ጥምረት ንቅናቄ መፍጠር ነው። በዚህ መንገድ ክርስትና የተለየ ነው የሚለውን አስተሳሰብ ማጥፋት ይቻላል ብላ ታምናለች። በተጨማሪ የመቻቻልን ቋንቋ በመጠቀም እምነቶች ሁሉ እኩል ናቸው የሚል ዕሳቤን በተለይ በህፃናት አዕምሮ ላይ ማስረፅ እና ቀጣዩ ትውልድ አንድ የዓለም እምነት እንዲቀበል ማድረግ ይቻላል ትላለች። ይህ እቅድ ምን ያህል እየተተገበረ እንደሆነ ኦክላሆማ (Oklahoma) የሚገኝ አንድ የሰይጣን ቤተመቅደስ ያወጣው መግለጫ አመልካች ነው። መግለጫውም በከተማው በሚገኝ ጥንታዊ አሥርቱ ትዕዛዛትን በሚያሳይ ሐውልት አጠገብ ሁለት ሜትር የሚሆን የሰይጣን ሐውልት ማቆምን በተመለከተ ነው። የከተማው ባለሥልጣናትም ምክንያታዊ ነው ብለውታል። ይህ የሰይጣን አምላኪ ቡድንም “ዓላማችን የሌላውን እምነት ለማንቋሸሽ አይደለም። ይህን ብናደርግማ የትምህርት ሥርዓቶቻችንን እንጻረራለን። ነገር ግን የተለያዩ ሥርዓቶችን እና የእምነቶችን ታሪክ መማርና ተሞክሮ መውሰድ ያስፈልጋል።” ሲሉ ገልጸዋል።
በ2017 ፕሬዝዳንት ፑቲን ለሀገሩ ዜጎች ባደረገው የገና የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቱ ለምዕራባውያን መውደቅ ምክንያት ከሆነው ውስጥ አንዱ በመቻቻል ስም ክርስትናን ከሰይጣን አምልኮ ጋር እኩል የሚያደርግ ፖሊሲ መከተላቸው ነው ሲል ገልጿል። ይህ ፖሊሲ የቤይሊን እቅድ ወደ ተግባር የተረጎመ መሆኑን ፑቲን ንግግሩ የበለጠ አጋልጦታል።
አሥረኛውና የመጨረሻው ነጥብ ሌሎቹ ዘጠኝ ነጥቦች የመንግሥታት ሕግ ሆነው ሊደነገጉና ክርስቲያናዊ በሆኑ አካላትም ተቀባይነት እንዲያገኙ ሊደረግ ይገባል የሚል ነው። ዓላማው ክርስቲያኖች እምነታቸውን እና በክርስትና ላይ የተመሠረቱ እሴቶቻቸውን ማስጣል ሲሆን ይህን ግን ዕውን ለማድረግ የሚቻለው እነዚህን ዘጠኝ ነጥቦች ተግባራዊ በማድረግ ነው ብላለች። በአጠቃላይ ሥራዋ ጠላት ያደረገችው ሌሎች እምነቶችን ወይም ደግሞ ንጹሐኑን የሚጨፈጭፉ የአክራሪ ቡድኖችን አይደለም ክርስትናን እንጂ። [በዚህም ዝንባሌዋ ለሠይጣን የተገዛችና በእርሱ ማኅደረነት እንደምትሠራ ማወቅ ይቻላል። የእርሷን መርሆዎች ሳይሸራርፍ ፖሊሲ በማድረግ በመላው ዓለም ላይ የሚጭኑት የተ.መ. የተለያዩ ድርጅቶችም በአሊስ ቤይሊ አድራሽነት የሰይጣን አገልጋይ ተቋማት ሆነው እየሠሩ ይገኛሉ።]
ምዕራቡ ምን ያክል የቤይሊን መንገድ ይዞ ወደ አዲሱ የዓለም ሥርዓት እንደተጓዘ ስንመለከተው በጣም የሚያስጨንቅ ነው። ከነጥቦቿ ውስጥ በማኅበርሰባችን መካከል ተፈጻሚ ያልሆነ የለም። የቤይሊ ዕቅዶች በብዙ ሰዎች በማይታይ መልኩ ተግባራዊ ተደርገዋል ፤ አየተደረጉም ነው። እነዚህ ሃሳቦች በጥልቀት የተተከሉ በምዕራቡ ዓለም ሲሆን በእስያ፥ በአፍሪካ እና በደቡብ አሜሪካ እስካሁን በጥልቀት መሠረት እና ሥር አልያዙም። በእንግሊዝ የአንግሊካን ቸርች (Anglican Church) ትላልቅ ጉባኤዎች በሚደረጉበት ወቅት ሚድያው ሲንሰፈሰፍና በወቅቱ ያለው የአንግሊካን ቸርች ዋና መሪ ከአፍሪካ ለመጡ የሃይማኖቱ መሪዎች የምዕራባውያንን አመለካከት በተለይም ፆታዊ ጉዳዮችን ሊሰብኳቸው ሲጣጣሩ ይታያል። የእንግሊዞቹ የአፍሪካዎቹን አቻዎቻቸውን እምነት እና አስተሳሰብ እንደ ኋላ ቀር በመቁጠር በአንድ ቤተክርስቲያን አባልነት በመገኘታቸው ያፍሩባቸዋል። በመሆኑም ምዕራባውያኑ በዓዲሱ ዓለም ሥርዓት የታደሰውን ዘመናዊውን የአንግሊካን ቸርች ገፅ በአፍሪካዎቹ ላይ ለመጫን ይሞክራሉ።
ቤይሊ ከ1945 ጀምሮ ላለው የምዕራባውያን ባህል ለውጥ ፕላን ነድፋ ተግባራዊ እንዳስደረገችው ማየት እንችላለን። አመለካከቷ በተ.መ. ልብ የተተከለ ብቻ ሳይሆነ ድርጅቶቿ ምን ያህል ሥራቸውን አስፍተው በተ.መ. የተወካዮች ስብሰባ ላይ ተጽዕኖ እንደሚፈጥሩ እንመልከት። የሉሲፈር ማተምያ ድርጅት በ1920 በቤይሊ የተቋቋመ ሲሆን መጠሪያ ስሙ ግን አጋላጭ ነው በሚል ወደ የሉሲ ትረስት ተቀየረ። ዛሬ የሉሲ ትረስት በተ.መ. የአማካሪነት ሥልጣን አለው። ይህ ሥልጣን ለአባላቶቹ በሳምንታዊው የተ.መ. ስብሰባ ወንበር የሚሰጥ ሲሆን በቀጥታ በተ.መ. አባላት ላይም ሆነ በራሱ በተ.መ. እንቅስቃሴ ላይ ተጽዕኖ ለመፍጠር አስችሎታል። ነገር ግን የሉሲ ትረስት ተጽዕኖ የሚፈጥረው በተ.መ. መቀመጫው ብቻ አይደለም፤ እንደራሴዎቹ በሆኑ እንደነ ጆን ሮክፌለር (John Rockefeller)፣ የቀድሞው የአሜሪካ አምባሳደር ቶማስ ዋትሰን (Thomas Watson)፣ ሄነሪ ኪሲንጀር (Henry Kissinger) እና ሌሎች እነርሱን በሚመስሉ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ምክር ቤት አባላቶች በኩል ነው። በተጨማሪም ዊንድሶር ባንክ (The Windsor bank) የሉሲ ትረስት አስተዋፅዖ አድራጊ መሆኑን አምኗል (በአሁን ወቅት ባንኩ በድህረገፁ የነበረውን ዝርዝር መረጃ አውርዷል)። የቀድሞው የተ.መ. ረዳት ጸሐፊ የነበረውና የዩኔስኮ የሰላምና የትምህርት ሽልማት ባለቤት ሮበርት ሙለር (Robert Muller) ትምህርት ቤት የከፈተ ሲሆን ሥርዓተ ትምህርቱ የአሊስ ቤይሊ እንደሆነ በይፋ ተናግሯል። የቤይሊን አስተሳሰብ ለመዝራት በህፃናት አይምሮ ላይ በስፋት ይሠራል።
የምዕራብ ጀርመን ገዥ ከነበረው ከሄልሙት ስክሚዲት (Helmut Schmidt)፣ የቀድሞው የኦውስትርያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ከማልኮም ፍራሰር (Malcom Fraser)፣ ከሺሞን ፐረዝስ (Shimon Peres) እንዲሁም ከጂሚ ካርተር (Jimmy Carter) ጋራ ሥምምነት ያለው ዘወርልድ ጉድዊል ድርጅት (The World Goodwill organisation) የተመሠረተው በ1932 በሉሲ ትረስት አባላት ሲሆን በተ.መ. የኤን.ጂ.ኦ ደረጃነት ተሰቶታል። ግቡ በግልጥ መናፍስታዊ ሲሆን ዓላማውም ሰይጣንን በመጠቀም ፖለቲካን ወደ አንድ የዓለም መንግሥት መምራት ነው። ዘወርልድ ጉድዊል ድርጅት ከዓለም ጤና ድርጅት፣ ከቴይል ሃርት ማእከል (Teilhardt Centre) እንዲሁም የዓለም የዱር እንስሳት ፈንድ ጋር ጥብቅ ትሥሥር አለው ። ይሄው ድርጅት ለዪኒሴፍ፣ ለቴድ ተርነር (የሲ.ኤን.ኤን (CNN) መሥራች)፣ ለአሜሪካ ተልዕኮ በተ.መ. እንዲሁም ለአምነስቲ ኢንተርናሽናል ድጋፍ እና እውቅና ይሰጣል። ልክ እንደ የሉሲ ትረስት ዘወርልድ ጉድዊል ድርጅት በተ.መ. የአማካሪነት ሥልጣን ተሰጥታል። ድርጁቱም ራሱን ሲያስተዋውቅ የሚሰራው “በሰው ልጆች መንፈሣዊ ዝግመተለውጥ” ላይ እንደሆነ ይናገራል። ይህ አሊስ ቤይሊ በጽሑፏ “ታላቅ የሆነው ሲመጣ [ሃሳዊ መሲህ] በፍሪሜሶናዊነት ተጠብቆ የነበረው ሃይማኖት ለሕዝብ ይፋ ያደርጋል” ብላ ከገለጸችው ሀሳብ ጋር አንድ ነው። ሌሎች በሉሲ ትረስት አባላት ከተመሠረቱ ድርጅቶች ውስጥ ፊንድሆርን ፋውንዴሽን (Findhorn Foundation)፣ በተ.መ. የኤን.ጂኦ ደረጃ የተሰጠው ዘቴምፕል ኦፍ አንደርስታንዲንግ (The Temple of Understanding)፣ የዓለም የመንፈሳዊ እና የፓርላማ መሪዎች መድረክ (Global Forum of Spiritual and Parliamentary Leaders፤ የዚህ መድረቅ ከተወሰኑ ውሳኔዎች ውስጥ ቀዳሚው የዓለምን የሕዝብ ብዛት መቀነስ ነው)።
በ2017 ፕሬዝዳንት ፑቲን ለሀገሩ ዜጎች ባደረገው የገና የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቱ ለምዕራባውያን መውደቅ ምክንያት ከሆነው ውስጥ አንዱ በመቻቻል ስም ክርስትናን ከሰይጣን አምልኮ ጋር እኩል የሚያደርግ ፖሊሲ መከተላቸው ነው ሲል ገልጿል። ይህ ፖሊሲ የቤይሊን እቅድ ወደ ተግባር የተረጎመ መሆኑን ፑቲን ንግግሩ የበለጠ አጋልጦታል።
ምዕራቡ ምን ያክል የቤይሊን መንገድ ይዞ ወደ አዲሱ የዓለም ሥርዓት እንደተጓዘ ስንመለከተው በጣም የሚያስጨንቅ ነው። ከነጥቦቿ ውስጥ በማኅበርሰባችን መካከል ተፈጻሚ ያልሆነ የለም። የቤይሊ ዕቅዶች በብዙ ሰዎች በማይታይ መልኩ ተግባራዊ ተደርገዋል ፤ አየተደረጉም ነው። እነዚህ ሃሳቦች በጥልቀት የተተከሉ በምዕራቡ ዓለም ሲሆን በእስያ፥ በአፍሪካ እና በደቡብ አሜሪካ እስካሁን በጥልቀት መሠረት እና ሥር አልያዙም። በእንግሊዝ የአንግሊካን ቸርች (Anglican Church) ትላልቅ ጉባኤዎች በሚደረጉበት ወቅት ሚድያው ሲንሰፈሰፍና በወቅቱ ያለው የአንግሊካን ቸርች ዋና መሪ ከአፍሪካ ለመጡ የሃይማኖቱ መሪዎች የምዕራባውያንን አመለካከት በተለይም ፆታዊ ጉዳዮችን ሊሰብኳቸው ሲጣጣሩ ይታያል። የእንግሊዞቹ የአፍሪካዎቹን አቻዎቻቸውን እምነት እና አስተሳሰብ እንደ ኋላ ቀር በመቁጠር በአንድ ቤተክርስቲያን አባልነት በመገኘታቸው ያፍሩባቸዋል። በመሆኑም ምዕራባውያኑ በዓዲሱ ዓለም ሥርዓት የታደሰውን ዘመናዊውን የአንግሊካን ቸርች ገፅ በአፍሪካዎቹ ላይ ለመጫን ይሞክራሉ።
Blogger Comment
Facebook Comment