ቆሞስ አባ ጳውሊ ከግንባር
አብያተ ክርስቲያናት ቢቃ*ጠሉ ፣ ምዕመናን ቢጨፈ*ጨፉና ቢፈናቀሉ ፣ ካህናትና መነኮሳት ቢታ*ረዱ ፣ ቅርሶች ቢወድሙና ሌሎች ልዩ ልዩ የግፍ አይነቶች ቢደረጉ ምን የማይመስለው ትውልድ ሆኗል:: ለስንፍና ጥቅስ የሚጠቅስ አስመሳይ ትውልድ! ተነሱ ቤተክርስቲያንን ታደጉ ሲባሉ "ሰይፍን የሚያነሱ በሰይፍ ይጠፋሉ" ይላል ወንጌሉ እያሉ ስለምን እንደተባለ እንኳን በውል ሳይረዱ ግደለሽነታቸውን በቅዱስ ቃል ይሸፍናሉ! በመሰረቱ " አት*ግደል" የሚለው የእግዚአብሔር ቃል ስለ ምን እንደሆነና ፍጹም ቤተክርስቲያንን ከመከላከልና ሀገርን ከመታደግ ጋር እንደማይገናኝ ሳታውቁት ቀርታችሁ ይሆናል ብዬ አላስብም!
በቤተክርስቲያን ታሪክ ከጌታችን ከአምላካችንና ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ እስከ 70 ዓ.ም ድረስ ያለው ዘመን ዘመነ ሐዋርያት ፣ ከ70 ዓ.ም እስከ 160 ዓ.ም ያለው ደግሞ ዘመነ ሐዋርያነ አበው ፣ ከ16ዐ ዓ.ም እስከ 312 ዓ.ም ያለው ዘመነ ሰማዕታት በመባል ይታወቃል፡፡ እንደሚታወቀው በመጀመሪያዎቹ ሁለት ክፍላተ ዘመናት የነበረው የቤተክርስቲያን መከራ ከአይሁድ ጋር የተደረገ ተጋ*ድሎ ነው፡፡ ይኸውም ምንም እንኳን እይሁዳዊያን ቃልኪዳን የተገባላቸው፣ ትንቢት የተነገረላቸው በአንድ አምላክ አማኝ የነበሩ ቢሆኑም የክርስቶስን አዳኝነት በመቃወም በክርስቲያን ላይ መከራና ግፍ ሲያደርጉ ነበር:: በዚህም በዘመኑ የነበሩ ክርስቲያኖች ዘመኑን በሚዋጅ መልኩ ያንን የመከራ ዘመን ተሻግረዋል:: ከዚያ በመቀጠል ቅዱሳን አበው ከአላውያን ነገሥታት ጋር ባደረጉት ተጋ*ድሎ የሚዘከር ዘመነ ሰማዕታት ተተካ! በወቅቱም የክርስትና ሃይማኖት በመላው ሮም ተስፋፍቶ ነበር፡፡ /1ቆሮ 7፥22/
በዚህ የተነሳ እንደነ ዲዮቅልጥያኖስ ያሉ ኢአማኒያን/ከሃድያን/ ነገሥታት ስልጣናቸውን መከታ አድርገው ብዙ ክርስቲያኖች በሰማ*ዕትነት እንዲያልፉ ያደረጉበት እኩይ ተግባርን የፈጸሙበት ዘመን ነበር፡፡ ይህም እግዚአብሔር ያስነሳው ደጉ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ መንበረ ሥልጣኑን ይዞ ለክርስቲያኖች ሠላም እስኪያወርድላቸው ድረስ የቀጠለ መከራ ነበር፡፡
ቤተክርስቲያን ምዕመናንን በስጋም በነፍስም መጠበቅ ስላለባት ለምድራዊ ኑሮ ሲባል በተለያየ ሥርዓተ መንግሥት ሥር የሚኖሩ ሰዎችን በሥርዓቷና እና በትውፊቷ እንዲኖሩ ታደርጋለች:: ሆኖም ግን ዋና ዓላማቸው ክርስትናን ለማጥፋት ስለሆነ የጥቃቱ ሰላባ እየሆነች ዘመናትን ተሻግራለች:: ከዚህ በዘለለም የዚህ ዓለም ገዥዎች የቤተክርስቲያን ስርዓት ከአመራራቸው ጋር የማይሄድ ስለሚመስላቸውና ለአምባገነንነት ትውልዱንም ወደ ጥፋት ለመውሰድ ቤተክርስቲያንን እንደ ጠላት በመቁጠር እንደየዘመናቸው ሁኔታ መከራን እያጸኑባት ኖረዋል::
ወደ ቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያ ስንመጣ ከብሉይ ኪዳን ወደ አዲስ ኪዳን ከተሸጋገርንበት 34 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 4ተኛው ክፍለ ዘመን ፈተና ቢኖርም እንደ ሮምና እንደ ሌሎቹ ሀገራት ብዙም የከፋ አልነበረም:: ኢትዮጵያ በብሉይ ኪዳን አምልኮተ እግዚአብሔርን ስትፈጽምና የክርስቶስን መምጣት ስትጠባበቅ ስለነበር ክርስትናን ለማስፋፋት ቀላል ነበር:: በ4ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የሃገሪቱ ብሄራዊ ኃይማኖት ሆኖ በይፋ ታወጀ:: ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ወደ ኢትዮጵያ ትኩረት ተደረገ::
በየዘመናቱም ኢትዮጵያ እንድትናወጽ ከውጭ የቤተክርስቲያን ጠላቶች የጥፋት መረብን ዘረጉ:: ኢትዮጵያ እንድትበታተን ብዙ ስራዎችን አደረጉ:: ሆኖም ግን እግዚአብሔር በላስታ ነገስታት በእነ ቅዱስ ላሊበላ ፣ በእነ አምደ ጽዮን ፣ በእነ ይኩኖ አምላክ ፣ በእነ አጼ ዘርዓ ያዕቆብ ፣ በእኔ አጼ ዳዊት ፣ በእነ አጼ ዮሐንስ ፣ በእነ አጼ ቴዎድሮስና በእነ አጼ ምኒልክ መሰረቷ እንዳይናወጽ አደረጋት! ቤተክርስቲያንም ከሃገሪቱ ተለይታ ስለማታውቅ መከራውን ስትጋፈጥ ዘመናትን ተሻገረች::
ዛሬም የብልጽግና ስርዓት ወደ ስልጣን እንደመጣ በቀጥታ ዒላማ ያደረገው ቤተክርስቲያንን ነው:: ለዕኩይ ስራው ይመቸው ዘንድ ተሰደው በውጭ የሚኖሩ አባቶችን (የውጭ ሲኖዶስ ) ወደ ሀገር እንዲገቡ አደረገ:: ህዝብም ሲኖዶስን አንድ አደረገ ብሎ አጨበጨበ:: ዓላማው ግን ውጭ ሆነው አባቶች ተጽእኖ እንዳያሳድሩበት በአንድ ቁማር ለመብላት ነበር ተሳካለትም:: ከዚያ ቤተክርስቲያንን የፖለቲካ መዘወሪያ መጫዎቻ አደረጋት:: ምዕመናን ፣ ዲያቆናት ፣ ካህናትና መነኮሳት እንደ በግ ታረ*ዱ! ቤተክርስቲያን እንደ ጿፍ ነደደች! ንዋየ ቅዱሳት ተቃጠሉ ተመዘበሩ ግፍ በቤተክርስቲያን ላይ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ተደረገ:: እኛ ግን አንቀላፍተናል:: ማንቀላፋታችን ሳያንስ ደግሞ ነቅተው ቤተክርስቲያንና ሀገርን ለመታደግ የሚጥሩትን እንተቻለን እናሳድዳለን! በጣም ያሳዝናል! በአሁኑ ሰዓት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኝ የሆነ ሁሉ መከራ ውስጥ ነው::
ይህ ለረጅም ጊዜ በዓለም ደረጃ ታስቦበት እየተሰራ ያለ ጉዳይ ነው:: የቤተክርስቲያንን መሰረታዊ አስተምህሮ ከመበረዝ ፣ ልዩ ልዩ የክህደት ትምህርቶችን በመ*ና*ፍ*ቃን ከማሰራጨት ጀምሮ ኃይል በመጠቀም ክርስቲያንን የማ*ጥፋት ስራ እየተከናወነ ነው:: ስርዓተ ትምህርቱንና ፖለቲካዊ መዋቅሩን ቤተክርስቲያን ጠል ማድረግንም ያካተተ ዘመቻ እየተደረገባት ይገኛል:: አብይ አህመድ በስህተት የሚሰራው ስራ እንዳይመስላችሁ:: አቅደውበት በጥናትና ሁሉን ባማከለ መልኩ ነው እየተገበሩት ያሉት:: በተለይ ደግሞ የብሄር ግጭትን በማባባስ ጥላቻ እንዲሰፍን በማድረግ በዚህም ቤተክርስቲያን የጥፋት ሰለባ ማዕከል እንድትሆንና የአንድ ብሄር ብቻ እንደሆነች በማስመሰል ታላቅ ግፍ እየተፈጸመባት ነው::
ቤተክርስቲያንን ለማጥፋት መሰረታዊ የሃይማኖት አስተምህሮትን በመበረዝ ፣ በመቀላቅል ፣ የሃይማኖታችንን ትምህርት አጣሞ አውጥቶ ለወጭ ውሻ*ወች (መ*ና*ፍ*ቃ*ን) በመስጠት የተቃረነና ቤተክርስቲያንን ኢላማ ያደረገ ትምህርት በማስተማር ወዘተ በሌላ ስልትም እያደረጉ ይገኛሉ:: በአሁኑ ሰዓት በብልጽግና መንግስት የሚደገፉ በርካታ ፓስተር ተብየዎች ቤተክርስቲያን ላይ የጥፋት በትር እየዘረጉ ያሉት ዝም ብለው መሰላችሁን?
እኛ ግን ተኝተናል አንቀላፍተናል! ለማንኛውም በመጨረሺያም ልነግራችሁ የምፈልገው ነገር እግዚአብሔር ትላንት ሰውን አስነስቶ ኢትዮጵያንና ቤተክርስቲያንን እንደጠበቃት ሁሉ ዛሬም አስነስቷል:: ብትጮሁ ፣ ብትሳደቡ ፣ ወደ ሰማይ ብትወጡ ወደ ምድርም ብትወርዱ የምትቀይሩት አንዳችም ነገር የለም! እናተ ወታደሮች ፣ ሚሊሻዎችና ሌሎች የመንግስት ኃይላት ተብየዎች ሁላችሁም በከንቱ ስጋችሁንም ነፍሳችሁንም አትጡ:: ምንም የምትቀይሩት ነገር የለም ጸባችሁም ከእግዚአብሔር ጋር ነውና ትወድቃላችሁ! መስዋዕ*ትነታችሁ ለከንቱ ነውና ንቁ! ሁላችሁም ኢትዮጵያውያን እግዚአብሔር ባዘጋጀው መንገድ ካልሄዳችሁ ለነገ ጥላችሁት የምትሄዱት መልካም ታሪክ ብሎም አሁን አፍጥጦ ከመጣው ቁጣም ለመሻገር እድል ፈንታ አይኖራችሁም! ኢትዮጵያን ለማዳን ጫካ ገብተው አጥንታቸውን እየከሰከሱ ደማቸውን እያ*ፈሰሱ ላሉ ለእውነተኛ ኢትዮጵያውያን (አርበኞች) ክብር ይገባቸዋል::
እንደ ትላንት እናት አባቶቻችን ሀገራችንንም ሃይማኖታችንንም እናስከብር ዘንድ ይህን መልእክት አስተላልፋለሁ!
መልካም የጾም ጊዜ!
Blogger Comment
Facebook Comment