እስራኤል ማን ናት? አይሁዶችስ እነማን ናቸዉ?

ክፍል ፩ (1)

1.መግቢያ

በብዙ ምክንያቶች የምናጠናዉን ርእሰ ጥናት በማብራራት መጀመር አለብን፤እስራኤል ማን ናት? አይሁድስ እነማን ናቸዉ? እብራዉያንስ እነ ማን ናቸዉ?

2.እስራኤል ማን  ናት?

ሀ. ሕዝብ እንዴት ይጠራል?

በመጽሐፍ ቅዱስ ዉስጥ ብዙ ጊዜ ሕዝቦች የሚወሰኑት በተፈጥሮአቸዉ በወንድ የዘር ሐረግ ነዉ፤ በመጽሐፍ ቅዱስ ዉስጥ በወንድ የዘር ሐረግ ለመጠራቱ ግልጽ ነዉ፤ ለምሳሌ ዘፍ 10፡5 ከእነዚህም የአሕዛብ ደሴቶች ሁሉ በየምድራቸው በየቋንቋቸው በየነገዳቸው በየሕዝባቸው ተከፋፈሉ፤  ከዚህ ቁጥር በፊት በኋላም ያለዉን ክፍል ስንመለከት በወንድ የዘር ሐረግ ሲጠራ እናያለን፤ ለምሳሌ ቁ.6  የካምም ልጆች ኩሽ፥ ምጽራይም፥ ፉጥ፥ ከነዓን ናቸው።

ኩሽ፡- የዘር ሐረጉ ከኑቢያ እና ኢትዮጰያ ጋር ይገናኛል

ምጽራይም፡- የታወቀ የእብራዉያን ስም ሲሆን በላይኛዉና በታችኛዉ ግብጽ…ይህም የሚገኘዉ በሰሜን አፍሪካ…ከነዓን እርሱም የከነናዉያን አባት ነበር፤

በመጽሐፍ ቅዱስ ዉስጥ የካም ልጅ ማለት የቀደሙ ሕዝቦች አባቶች ነበሩ ብዙ ጊዜ ‹‹ሕዝብ›› የሚለዉ ቃል ከአገር ጋር የሚያያዝ ሲሆን በዚህ የጥናት መጽሐፍ ግን ሕዝብ  የሚለዉ በመጀመሪያ የሰዉ ዘር በሙሉ ከአንድ የጋራ አባት እንደመጣ እንመለከታለን፤

ለ.የእስራኤል ሕዝብ እንዴት ተመሰረተ?

የእስራኤል ሕዝብ በወንድ የዘር ሐረግ የተወሰነ ነዉ፤ እግዚአብሔር አብርሃምን ጠራዉ እና ከእርሱ ጋር ቃልኪዳን አደረገ በእርሱ ታላቅ ሕዝብ እንደሚፈጠር ተናገረ (ዘፍ 12፡1-2) ከአብርሃም ልጆች በመቀጠል ወደ ይስሀቅ ተሻገረ (ዘፍ 26፡2-5) የይስሀቅ ልጆች ያዕቆብና ኤሳዉ ከዚያም እግዚአብሔር ወደ ይስሀቅ ልጅ ከያዕቆብ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ( ዘፍ 28፡13-15) በመቀጠልም የያዕቆብ ስም እስራኤል ሆኖ ተለወጠ ( ዘፍ 32፡28) ከዚያ ጀምሮ እስራኤል በወንድ የዘር ሐረግ ሲጠሩ  በእስራኤል ሲጠራ የነበረዉ ስም ዘሮቹ ደግሞ እስራኤላዉያን ተባሉ፤ይህም አገሪቱ የምትጠራበት ስም ሆነ የእስራኤልም ልጆች ለእህል ሸመታ ከመጡቱ ጋር ገቡ፤ በከነዓን አገር ራብ ነበረና (ዘፍ42፡5፣ 45፡21፣46፡5 ዘጸአት23፡17፣ 1ዜና 2፡1) ከዚያም ሕዝቡ  እርሱ በሕይወት በነበረ ጊዜ ‹‹እስራኤል›› ተባለ፤( ዘፍ 34፡7)

ነገር ግን አንድ ሰዉ እናቱ እስራኤል ሆና አባቱ አሕዛብ ቢሆንስ? በርግጥ ይህ ሰዉ በአባቱ አገር ነዉ የሚጠራዉ አንድ ሰዉየዉ ግን ራሱን ከእስራኤል ጋር ራሱን ማመሳሰል ከፈለገ በእግዚአብሔር አይን ሲታይ እስራኤል መሆን ይችላል፤ ለምሳሌ ጢሞቲዎስን መመልከት እንችላለን (ሐዋ 16፡1-3)

ጳዉሎስ በነጻነት ጢሞቲዎስን አስገረዘዉ ምክንያቱም እናቱ አይሁድ ነበረችና መገረዝ ደግሞ የግድ ነዉ ምክንያቱም እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር የገባዉ ቃል ኪዳን ስለሆነ ዘፍ (17፡12-14)

( የሙሴ ኪዳን በመስቀል ላይ አይሰራም ወደዚህ መጥቶ ሊሰራ አይችልም የአብርሃም ኪዳን እስካሁንም ይሰራል) በሚያከራክር መልኩ ጳዉሎስ  ቲቶን ለማስገረዝ እምቢ አለ፣ ምክንያቱም ከአይሁድ የሆነ ቤተሰብ ስለሌለዉ ነዉ፤( ገላ 2፡1-5 ቁ.3) አንድ ሰዉ አይሁድ እናት ኖሮት አባቱ ግን አሕዛብ ከሆነ  እርሱ ወይም እርስዋ ወደ እስራኤል ሕዝብ የመቀላቀል እድል አለዉ በእግዚአብሔር አይን ሲታይ እስራኤል እንደሆነ ነዉ፤ በወንድ ጉዳይ መቀላቀል የሚችለዉ በመገረዝ ነዉ፤እርሱ ወይም እርስዋ እስራኤል መሆን ካልፈለገች በአባትዋ ወንድ የዘር ሐረግ አሕዛብ ሆኖ ይቀራል፤

ሁሉንም ወደ ቤት ለማምጣት አንድ  ሰዉ እስራኤላዊ ለመባል የአብራሃም የይስሀቅና ያዕቆብ ዘር ሆኖ በወንድ የዘር ሀረግ መጠራት አለበት፤ አንድ ሰዉ ግን አይሁዳዊ እናት ኖሮት አባቱ አሕዛብ ከሆነ እና ራሱን ከእስራኤል ጋር ካመሳሰለ ይህ ሰዉ በእግዚአብሔር አይን ሲታይ እስራኤል ነዉ፤ እስራኤላዊ ለመሆን መገረዝ  የግድ ነዉ፤

አይሁዳዊነት ከመጽሐፍ ቅዱስ ዉስጥ ከተጠቀሰዉ የሚለየዉ ነገር አለ፤ ማህበራዊም ነዉ፣አይሁዳዊነት ብሔር ነዉ፤አይሁዳዊነት ከብሔር በተጨማሪ ራሱን ከአይሁድ ሕዝብ ጋር ማመሳሰል ያስፈልገዋል፤ ከአይሁድ ሕዝብና ባህል ጋር ራሱን አብሮ ማስኬድ ይኖርበታል፤ ይህ ራስን ማመሳሰል ወደ አይሁድነት የመመለስ አንዱ ምልክት ሊሆን ይችላል፤ከአይሁድ ሕዝብ ጋር በጋብቻ መጣመር፣በማደጎ የአይሁድ ቤተሰብ እንዲሆን በማድረግና የመሳሰሉት፣ መጽሐፍ ቅዱስ ከሁለቱ አንደኛዉን መንገድ ብቻ የሚከተል ነዉ፤ ማህበራዊዉ ትንታኔ አልተጠቀሰም፤እንደ መጽሐፍ ቅዱስ የአብርሃም፣ የይስቅና ያዕቆብ ዘር የሆነ ብቻ አይሁዳዊ እንደሆነ ነዉ የሚናገረዉ፤ እንደ ማህበራዊ ጥናት ትርጉም አንድ የአየርላንድ ዜጋ  የሆነ ሰዉ ከአይሁድ ቢያገባና ወደ አይሁድነት ቢለወጥ በተመሳሳይ የአየርላንድን ባህል ሊይዝ ይችላል፤ባህሉና ከአይሁድ የወረሰዉ ነገር ተጋብተዋል እንደገና የተለወጠበት ባህል አለ፤ እርሱ በማህበራዊ ነገር አይሁዳዊ ነዉ ወይስ አየርላንዳዊ ነዉ? እንደጠያቂዉ ሁኔታ ይወሰናል!

ቁልፉ ነጥብ የተነሳዉ በማህበራዊ ትርጉም አይሁዳዊነት ሲተረጎም ነዉ፤ በማህበራዊ ጥናት አይሁዳዊነት የማይጠቅምና ትርጉም አልባ ነዉ፤ መጽሐፍ ቅዱሳዊዉ አይሁድነት ትርጉሙ እንደሚከተለዉ ይቀርባል፤እግዚአብሔር እንዳለዉ በደም አይሁዳዊ መሆን ለሁሉም ሰዉ የሚሆን አይደለም፤ በማህበራዊ ጉዳይ አይሁዳዊ የሆኑ ግን የአብርሃም፣ይስሀቀና ያእቆብ በደም ያልተገናኙ ሊሆኑ ይችላሉ፤

ይቆየን...


Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment