ክፍል ፪ (2)
ሐ.በምን ታሪካዊ ቅኝት ነዉ እስራኤል የተፈጠረችዉ?
1.እስራኤል መቼ ተፈጠረች?
እስራኤል ከተመሰረተች በግምት 2000 ዓ/ዓ አካባቢ በአብርሃም፣ ይስሀቅ እና ያዕቆብ ነዉ
2.ይህቺ የተፈጠረች እስራኤል መቼ ነዉ የጠፋችዉ?
ይህ ሁለት ነጥቦችን ያሳየናል፤
1.አይሁዳዊነት የተገለጸዉ ወደፊት በሺህ አመተ መንግስት ጊዜ የሚሆነዉን ጊዜ ነዉ ለምሳሌ (ዘካርያስ 8፡23) ፡-‹‹በዚያ ዘመን ከአሕዛብ ቋንቋ ሁሉ አሥር ሰዎች የአንዱን አይሁዳዊ ሰው ልብስ ዘርፍ ይዘው፦ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዳለ ሰምተናልና ከእናንተ ጋር እንሂድ ይላሉ››
1.ኢሳ 65፡20 በሺህ አመቱ ጊዜ የሚወለዱ ልጆች፡-…‹‹ወይም ዕድሜውን ያልፈጸመ ሽማግሌ አይገኝም’’
ከእነዚህ ነጥቦች የተነሳ እስራኤላዉያን እስከ ሺህ አመተ መንግስቱ ጊዜ ድረስ ልጆችን ይወልዳሉ፤
የእስራኤል ሕዝብ የተጀመረዉ በ2000ዓ/ዓ ሲሆን እስከ ሺህ አመቱ ድረስ ይቀጥላል
3.አይሁዶቸ እነማን ናቸዉ?
‹‹አይሁድ››እና ‹‹እስራኤል›› የሚሉትን ቃላት እየቀያየርሁ እጠቀማለሁ፤ ይህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጠቀሜታ አለዉን?
1. የ ‹‹አይሁድ›› ትርጓሜ
ዮሐ 4፡9 ‹‹ለዚህ ሳምራዊቲቱ፦ አንተ የይሁዳ ሰው ስትሆን ሳምራዊት ሴት ከምሆን ከእኔ መጠጥ እንዴት ትለምናለህ? አለችው፤ አይሁድ ከሳምራውያን ጋር አይተባበሩም ነበርና›› በዚህ ክፍል ዉስጥ አሕዛብ ኢየሱስን የሚያዩት አይሁዳዊ እንደሆነ ነዉ እርሱም አልካደም፤ እስራኤላዊዉ ዮሐንስም ኢየሱስን ሲገልጸዉ የኢየሱስ ብሔር አይሁድ እንደሆነ ነዉ፤ ዮሐ 18፡35 ጲላጦስ መልሶ፦ እኔ አይሁዳዊ ነኝን? ወገኖችህና የካህናት አለቆች ለእኔ አሳልፈው ሰጡህ፤ ምን አድርገሃል? አለው። እዚህ ጋ እንደምናየዉ ኢየሱስ ብሔሩ አይሁድ እንደሆነ ነዉ እርሱም አልካደም፤
ሐዋ 21፡27-28 ሉቃስ አይሁዶች እስራኤላዉን እንደሆኑ ተናግሯል ሰባቱ ቀንም ይፈጸም ዘንድ ሲቀርብ ከእስያ የመጡ አይሁድ በመቅደስ አይተውት ሕዝብን ሁሉ አወኩና፦ የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ እርዱን ሕዝብን ሕግንም ይህንም ስፍራ ሲቃወም ሰውን ሁሉ በየስፍራው የሚያስተምረው ሰው ይህ ነው፤ ጨምሮም የግሪክን ሰዎች ደግሞ ወደ መቅደስ አግብቶ ይህን የተቀደሰ ስፍራ አርክሶአል ብለው እየጮኹ እጃቸውን ጫኑበት።
ያ በጥላቻ የተሞላዉ ሕዝብ ጳዉሎስም ራሱን እንደ እስራኤል ሰዉ አድርጎ ነበር በመጮህ አይሁዳዊ ነኝ አለ (ቁ. 39) እና ፊሊ 3፡5 ላይ ራሱን ሲገልጽ በስምንተኛ ቀን የተገረዝሁ የእስራኤል ወገን…
በእነዚህ ክፍሎች ዉስጥ ግልጽ በሆነ ሁኔታ በአሕዛብ አስተሳሰብ፣የማያምኑ አይሁዳዉያን፣የኢየሱስ ደቀመዛሙርት፣ እና ኢየሱስ ራሱ አይሁዳዊ እና እስራኤላዉያን አንድ አይነት መሆናቸዉን ነዉ የሚያዉቁት፤ ጳዉሎስን ከመስቀሉ በኋላ የሆነ አማኝ ማለት ተገቢ አይደለም፤ የአሕዛብ ሐዋርያ ቢሆንም ራሱን አይሁዳዊና እስራኤል አይሁድ አድርጎ ነዉ፤
አይሁድ የእስራኤል አባልና ወገን ነዉ፤ አይሁድ ማለት ሰፋ ባለዉ በመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ከእስራኤል አገር/ወገን/ ጋር ተመሳሳይ ነዉ፤
ይቆየን...
Blogger Comment
Facebook Comment