ወደ ኢትዮጵያዊነታችሁ ተመለሡ!!


ኢትዮጵያ ሲባል ከሐይማኖት የተለየች ሐይማኖት አልባ የሐይማኖት ግፋፎ ገለባ ማጠራቀሚያ አገር አይደለችም፡፡ የተጣራ ሐይማኖት ያላት ከኖህ እስከ ሙሴ ፣ከሙሴ እስከ ክርስቶስ ፣ከክርስቶስም እስከ ዛሬ ያልተለወጠ እውነተኛ ከእግዚአብሔር አንድነት አንድ አድርጓት የኖረ፣ የተጠጣራ ሐይማኖት  አላት፡፡

በዘመንም በትምህርትም አድጎ ፍፁም የሆነ፡፡ ከዚህ ሌላ ሐይማኖት ለኢትዮጵያ አያስፈልጋትም የለምም፡፡ የማያስፈልጋትም ስለሌለ ነው፡፡ ሌላ እውነተኛ ሐይማኖት ስለሌለ ነው፡፡

ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት በስተቀር ፣ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ከምትሰብከዉ የኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት በስተቀር ሌላ ሐይማኖት የሚባል ነገር ስለሌለ የራሷ ሐይማኖትም ደግሞ ከአበው ከነቢያት ፣ ከሐዋርያት ሲወርድ ሲዋረድ መጥቶ እዚህ የደረሠ ሀገሪቱንም በመጠበቅ በማክበር በማበልፀግ የታወቀ ስለሆነ ከዚህ ሐይማኖት የበለጠ ሌላ ሐይማኖት አያስፈልጋትም ፡፡ ያለ ሐይማኖት ደግሞ ሀገር ሀገር ሊሆን አይችልም፡፡

ያለ ሐይማኖት አገር አገር ሊሆን አለመቻሉንም በብሉይ ኪዳን ልዩ ልዩ ታሪክ ማጥናት ይቻላል፡፡  እግዚአብሔር  እሱን የማያመልኩትን ከነአናዉያንን (ነገደ ከነአን) አስወጥቶ እሱን ለሚያመልኩት ለአብርሃምና ለዘሩ ምድረ ፍልስጤምን  እንደሰጠ ግልፅ ታሪክ ተፅፏል፡፡

በዘጸአት ፣ በመፅሐፍ ኢያሱ ማንበብ ይቻላል፡፡ ያቺም አገር ለአማኞች ርስት በመሆኗ ርስቲቱ ለአማኞች ፤ አማኞች ለርስቲቱ ብቻ ሆነው እንደ ሚኖሩም እነዚሁ መፅሐፍት ጥሩ አድርገው ያስረዳሉ፡፡  ከነዚህ ቀጥሎ በሐይማኖት ባለ ርስትነት አብሮ መኖር የኢትዮጵያውያን የግል ሀብታቸው ነው፡፡

ይህ ሥለሆነም እስራኤል በተስፋ የተነገረላቸው አንቀበል ብለው  ክርስቶስን አንቀበልም በማለታቸው፡፡ ከአባታቸው በቃልኪዳን የተቀበሏትን ርስት አተው ከርታታ አውታታ ስደተኛ ሆነው እስከ 48አ.ም ድረስ መኖራቸው ራሡ በቂ ታሪክ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ግን ከ3ሽህ አመት በላይ ፀንታ መኗሯ ራሱ የሐይማኖት ምስክር ነው፡፡ እና ለአንደ ሀገር አንድ ሐይማኖት እንጂ ብዙ ሐይማኖት አስፈላጊ አይደለም፡፡ ለአንድ ሴት ለአንድ ቤት ብዙ ሴቶች እንደማያስፈልጉ ሁሉ፡፡ ለአንድ ሀገር ለአንድ መንግስትም ብዙ ሐይማኖቶች አስፈላጊ አይደሉም፡፡ የሚፈለገው እግዚአብሔርን ማመን ከሆነ ኢትዮጵያ የሚጎድላት ነገር የለም፡፡ የተመሠገነችበት ነው፡፡

እንደውም ጌታ የሳበ ንግስት በፍርድ ቀን ተነስታ ይቺን ትውልድ ትፋረዳታለች በማለቱ  ኢትዮጵያ እውነተኛዋን ሐይማኖት ለመቀበሏ እና ደ የእውነተኛው ሐይማኖት ባለቤት ለመሆኗ በቂ ማረጋገጫ ነው፡፡ ይህ ከሆነ  ኢትዮጵያውያን ሁሉ ለገንዘብ በገንዘብ የሚመጣ ሐይማኖትን ሊገደዱበት አይገባቸውም፡፡ ሞራላቸውን አጠንክረው አገራቸውንና ሐይማኖታቸውን አክብረው መኖር አለባቸው ፡፡

 ሐይማኖት የግል ነው ሀገር የጋራ ነው የሚል አዋጅ ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ግን ያ የ3ሽህ አመት ታሪክ ጠፋቶ እና ተበላሽቶ ፤ እንዳልነበረ ሆኖ ሕዝቡ መብት አልባ ፣ ቤት አልባ ፣ ርስት አልባ ፣ ታሪክ አልባ ፣ የሚቆምለት አልባ ሆኖ ከርታታ ፣ አውታታ፣ ከመሆኑ በየሀገሩ እንደ እስራኤል  የተበተነ ከመሆኑም ሌላ በየሀገሩም ውስጥ የሀገሩ ስደተኛ፣ የሀገሩ እስረኛ ሆኖ ነው የሚኖረው፡፡
ይህንን ልታውቁ ሊያማችሁ ሊያ ቆስላችሁ ይገባል፡፡ የማይደርቅ ቁስል ነውና ልትረዱት ይገባል፡፡ 

መላው ኢትዮጵያውያን በአለም የተበተናችሁ ሁሉ ይህንን ነው እንድታውቁት የምፈልገው አንድ ሆናችሁ አማራ፣ ትግሬ ፣ ኦሮሞ ወይም ሌላ ሳይባል አንድ ሆናችሁ ሀገራችሁን ነፃ አውጡ ፡፡ ሀገራችሁን ከወደቀችበት አንሱ፡፡ ሀገራችሁን ከፈረሰችበት አድሱ አንፁ፡፡ ታሪካችሁን ከፈረሰችበት አድሱ፡፡ አንፁ፡፡ ታሪካችሁን በታሪክ መልሱ አባቶቻችሁ ሠርተው ሄደዋል ምንም የሚጎዳቸው ነገር የለም፡፡ የምታጡ እናንተ ናችሁ፣ ልጆቻችሁ ናቸው፣ አገር አልባ ሆነው የሚቀሩት፡፡

ኢትዮጵያውያን በኢትዮጰያዊነታችሁ እመኑ ሀገራችሁ ኢትዮጵያ እናንተም ኢትዮጵያውያን መሆናችሁን ብትወዱም ባትወዱም አምናችሁ ተቀበሉ፡፡ 
ቅዱስ ጳውሎስ ምን ይላል የማያምኑ ቢኖሩ የነሱ አለማመን እግዚአብሔርን ከመኖር የሚያግደው ነገር ነው ወይ?? ወይስ ሌሎችን ከማመን ይከለክላል ወይ ይላል፡፡

እንግዲያው እናንተ ኢትዮጵያውያን ስትሆኑ ደማችሁ ፣ ቀለማችሁ፣ ሁኔታችሁ እየመሠከረባቸው ኢትዮጵያውያን ስትሆኑ ኢትዮጵያዊነታችሁን ብትክዱ ባእዶች ግን አይደሉም ብለው አይቀበሏችሁም፡፡ የትም ብትሄዱ እንግሊዞች ፣ ጣልያኖች፣ ጀርመኖች፣ ጃፓኖች ናቸው  ብለው የሚቀበልህ የለም፡፡ 

በአሁኑ ጊዜ የመጣ የቀልድ ቋንቋ አለ፡፡ የ 2 አገር ዜግነት መያዝ ፡፡ ይሄ ደግሞ ፍፁም ሞኝነት ነው፡፡ እና በከንቱ አትደለሉበት ያልሆናችሁትን አትሆኑምና ነን አትበሉ ፡፡ አሜሪካውያንም አይደላችሁም ሌላም አይደላችሁም ፡፡ ኢትዮጵያውያን ናችሁ፡፡

ግልፅ ምስክር ደማችሁ ነው፡፡ ነቢዩ ኤርሚያስ ኢትዮጵያዊ መልኩን ነብር ዥንጉርጉርነቱን አይለውጥም፡፡ ነው የሚል፡፡ እና መልካችሁን መለወጥ ስለማትችሉ ማንም ደግሞ ብትዋሹ አምኖ ስለማይቀበላችሁ በከንቱ ጊዜአችሁንም እድላችሁ አታበላሹ ወደ ኢትዮጵያዊነታችሁ ተመለሡ፡፡

እግዚአብሔር ለሁላችሁም አእምሮ ይስጥ! አሜን!
ክቡር አለቃ አያሌው ታምሩ
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment