እስራኤል እና ኢትዮጵያ አሁን

✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ አውታር 

ምንም እንኳን እኛ የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ለሦስት ሺህ ዓመታት ያለምንም ገደብ ለእስራኤል (ያዕቆብ)እና በየአህጉሩ ለሚበደሉት አይሑዶች ብንጸልይ እና ድጋፍ ብንሰጥም፤ እስራኤል ግን ከኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ጎን ለመሰለፍ ፈቃደኛ አይደለችም። ዛሬ ሙስሊሞች እና ፕሮቴስታንቶች በኢትዮጵያ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ላይ በሚያካሂዱት የዘር ማጥፋት ጂሃድ የእስራኤል መንግስት፣ ልክ እንደ ሩሲያው እና ዩክሬይን መንግስታት ከዘር አጥፊው የኢስላም-ፕሮቴስታንት ጋላ-ኦሮሞ አገዛዝ እና ቱርክ፣ አዘርበጃን፣ ኢራን እና ዓረቦች ጎን መስለፉን መርጧል። በጥንታውያኑ አረመናውያኑ ክርስቲያን ወገኖቻችንም ላይም ያየነው ይህን ነው። እስራኤል ከሺያ ሙስሊም አዘርበጃን ጎን ሆና በአርመኒያውያን ክርስቲያኖች ላይ የዘር ማጽዳት ወንጀል ፈጻሚ አካልም ለመሆን በቅታለች።

እስራኤላውያን እና መገናኛ ብዙኀኖቻቸው ባለፉት አራት ዓመታት በኢትዮጵያ በአስቃቂ ሁኔታ ለተጨፈጨፉት ከሁለት ሚሊየን በላይ ለሚሆኑትና ጽላት ሙሴን ለሦስት ሺህ ዓመታት ተንከባክበው ለያዙት ተዋሕዶ ክርስቲያኖች በጭራሽ ድምጽ ሆነውለት አያውቁም። የእስራኤል መንግስት በኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ላይ የሚፈጸመውን ጀነሳይድ ተከትሎ ይህ አሳዛኝ ሁኔታ ተገቢ የሆነውን የዓለም ዓቀፍ ማሕበረሰብ ትኩረት እንዳያገኝ እና የኢትዮጵያውያን ድምጽም እንዳይሰማ ዓለም በዩክሬን እና ሩሲያ እንዲሁም በእስራኤል እና 'ፍልስጤማውያን/ዓረቦች' ግጭት ላይ ብቻ ሁልጊዜ ይጠመድ ዘንድ መርጠዋል። ምክኒያታቸው ምን ይሆን? ምንድን ነው የሚፈልጉት? ሃቁ ይህ ነው! ይህ የአብራሐም፣ ይስሐቅ እና ያዕቆብ አምላክ ፍላጎት ነውን? አይመስለኝም! ምክኒያቱም እስኪ ማን ከማን ጋር ለምን እንደተሰለፈ እንመልከት።

እስራኤል የሱኒ እስላም እሳሜላውያን በሆኑት በግብጽ፣ በሳውዲ ዓረቢያ፣ ኳታር እና የተባበሩት የዓረብ ኤሚራቶች ተደግፋ በሺያ እስላም እስማኤላውያን በሆኑት በኢራን፣ በሊባኖን እና በየመን ላይ ጥቃት እየፈጸመች ነው። መፈጸሟ ተገቢ እና አስፈላጊ ቢሆንም፤ የሱኒ እስላም እስማኤላውያኑ ግን ይህን ጥቃት የሚገልጉት በሺያ እስልምና ላይ ከፍተኛ ጥላቻ ስላላቸው እና እራሳቸው ብቻ የበላይ ሆነውና ተስፋፍተው መኖር ስለሚፈልጉ ብቻ ነው። ለሱኒ እስልምና ሃገራት እስራኤል ልክ እንደ ጠቃሚ ደደብ/ Useful Idiot ሆና ነው የቀረበችው። የእስራኤል መንግስት ምን ስላቀደ/ስለተመኘ ይሆን? የቃልኪዳኑን ታቦት? ወይንስ እስከ ዓባይ ወንዝ ምንጮች የሚዘልቁትን እንደ ኢትዮጵያ እና ታንዛኒያ ያሉትን ሃገራት፤ ልክ የዩሮ-እስያ አንድ አህጉር ለመፍጠር እንድሚያስበው የሩሲያ መንግስት የእስራኤል መንግስትም በታላቂቷ እስራኤል ላይ እየሠራ ነው?
የዛሬይቷ እስራኤል ልክ እንደ መሐመዳውያኑ ሃገራት በሃጋር እና ልጇ እስማኤል መንፈስ ሥር የወደቀች እስራኤል ዘ-ስጋ ናት። መሐመዳውያኑ፤ “First The Saturday People (Jews), Then The Sunday People (Christians)” መጀመሪያ የቅዳሜ ሰዎች (አይሁዶች)፣ ከዚያም የእሁድ ሰዎች (ክርስቲያኖች)እንደሚሉት፣ የዛሬዋ እስራኤልም፤ ““First The Sunday People (Christians), Then The Friday People (Muslims)” መጀመሪያ የሰንበት ሰዎች (ክርስቲያኖች)፣ ከዚያም የዓርብ ሰዎች (ሙስሊሞች)ማለቷ ይሆን ዛሬ የክርስቲያኖች እና አይሁዶች ቍ. ፩ ታሪካዊ ጠላት ከሆኑት ሱኒ እስላም ሃገራት ጋር 'የአብርሃም ስምምነት' ተብሎ በሚጠራው ዓለማዊ የስምምነት ሰበብ ይህን ያህል ተባባሪ ሆና የተገኘችው? ከሺያ አዘርበጃንም ጋር ሆና በአርሜኒያ ክርስቲያኖች ላይ ታሪክ የሚዘግበው ብዙ ግፍና በደል ለመፈጸም በቅታለች። ለምን? ከክርስቲያን ጎረቤት ሙስሊም ጎረቤት መርጣ? ይህ እኮ እግዚአብሔርን በጽኑ የሚያስቆጣ ትልቅ ስህተት ነው? እግዚአብሔር አምላክን የያዘ እኮ የማንንም እስማኤላዊ እርዳታና ድጋፍ በፍጺ፣ አይሻም! እንዲያ ከሆነማ ይህ የአብርሐም ስምምነት' የሃገር + እስማኤል/ የኤሳው/ኤዶም ስጋዊ ስምምነት ነው ማለት ነው። በዚህ ደግሞ እስራኤልም፣ ቱርክም፣ አዘርበጃንም፣ ኢራንም፣ አረቦቹም፣ ሩሲያም፣ ዩክሬንም፣ አውሮፓም፣ አሜሪካም ከፍተኛ ዋጋ ይከፍሉ ዘንድ ግድ ነው። 

❖❖❖[ትንቢተ አሞጽ ምዕራፍ ፱፥፯፡፰]❖❖❖

“የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን? ይላል እግዚአብሔር። እስራኤልን ከግብጽ ምድር፥ ፍልስጥኤማውያንንም ከከፍቶር፥ ሶርያውያንንም ከቂር አላወጣሁምን?

እነሆ፥ የጌታ የእግዚአብሔር ዓይኖች በኃጢአተኛ መንግሥት ላይ ናቸው፥ ከምድርም ፊት አጠፋታለሁ፤ ነገር ግን የያዕቆብን ቤት ፈጽሜ አላጠፋም፥ ይላል እግዚአብሔር።”


Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment