ገና ብዙ መከራ፣ ገና ብዙ ውጣ ውረድ፣ ገና ብዙ ጦርነት ይፈጸማል።
መንግስት የሆነ ቦታ ላይ ከአቅሙ በላይ መሆኑ አይቀርም። ያኔም የውጪዎቹ መንግስታት ጣልቃ እንግባ ማለታቸው አይቀርም። ከዛም አውሮፓውያን፣ ዓረቦች፣ ወዘተ ወደ ሀገር ውስጥ ይገባሉ...ለዘመናት የተመኙትን ምኞት ሁሉ ይፈጽማሉ። እስከዛም ይህ መንግስት ሀገሪቷን ብርግድግድ አድርጎ ይከፍትላቸዋል።
ከነ አፄ ዘርዓያዕቆብ ዘመን ጀምሮ የነበረውን የ 'Closed door policy' ይህ መንግስት እያፈራረሰው ነው። በሁሉም መልኩ ለውጪዎች እንድትመች ተደርጋ እየተከፈተች ነው ሀገሪቱ። ቀጣይ የብር ዋጋ ወርዶ ወርዶ ከወረቀት ያነሰ ሲሆን ዶላርን ተቀበሉ ተብሎ በግድ ጫና ይደረግብናል። አሁንም ጀምረዋል መንግስት ዶላርን ከብላክ ማርኬት ዋጋ እኩል እንዲያደርገው ተነግሮታል። በቅርቡ 70፣ 80 እያለ 120 እንደሚደርስ ይጠበቃል።
ከዚም በላይ የውጪ ድርጅቶች እዚ መጥተው እንዲነግዱ፣ ቡናና ሰሊጥ ኤክስፖርት እንዲያደርጉ ሁሉ እየተፈቀደ ነው። ከዛም ድሮም ከሌለን ገንዘብ ላይ እቺን ትንሿን መተንፈሻ የምትሆነውን የገቢ ምንጭ እንኳ ጠራርገው ወስደው ይሄዳሉ።
መቼስ ሰው ከውጪ ሲመጣ እኛን ለመጥቀም አይደለም አይደል? ለራሱ ጠራርጎ ለመውሰድ ነው የሚመጣው። አይ ተጨማሪ የወረቀት ብር ያመጣል ብለን የምናስብ ካልሆነ በቀር። የወረቀት ብር ደግሞ ዋጋ እንደሌለው ይታወቃል። እንደፈለገ ቢከማች እሱን ከኋላ የሚደግፈው ሸቀጥ ወይም ማዕድን ከሌለ ባዶ ነው። ሸቀጥና ማዕድኑን ደግሞ መተው እየመዘበሩት ነው።
በግብጽና በቱርክ የተጀመረው የኢትዮጵያን ሀብት የመመዝበር ሂደት እስከ አሁንም አልቆመም። ሀገሪቱ አልቃ ባዶ ሆና እንኳ መዝረፍ መመዝበራቸው አልቀረም። እነ ቱርክ በዐጼ ዓምደ ጽዮን ዘመን 1314 ዓም ጀምረው በግራኝ አሕመድም በደምብ አጧጡፈው በየጊዜው የቻሉትን ያህል ከኢትዮጵያ ወርቁን ብሩን ሀብቱን ሁሉ ሲዘርፉ ኖረዋል። እነ ኢንግሊዝ ፈረንሳይም እነ ጣልያንም አንዴ በጉብኝት ስም ሲመጡ የቻሉትን ያህል ሰርቀው ሲሄዱ፣ አፄ ቴዎድሮስን ሲወጉ፣ ጣልያን 5 ዓመት ስትቆጣጠረን ወዘተ አሁን ደግሞ እነሱን በሚያደርጉት መንግስቶቻችን ምክንያት በግልጽ ሀብታችን እየተዘረፈ ነው። ያ ሁሉ አልበቃቸውም ደግሞ አሁን በይፋ ብርግድ ተደርጎ ተከፍቶላቸው ሁሉንም ነገር መውሰድ ባዷችንን ማስቀረት ይሻሉ።
ልዑል እግዚአብሔር ይፍረድ መቼስ ምን ይባላል።
Blogger Comment
Facebook Comment