✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
የፍሎሪዳ የቀዶ ጥገና ጄኔራል/ዋና ሐኪም ዶ/ር ዮሴፍ ላዳፖ፡ "የኮቪድ ኤም.አር.ኤን.ኤ ክትባቶች ከሁሉም ምርቶች ፀረ-ክርስቶሳዊው ናቸው"
የውጭ ዘረመል /ዲ ኤን ኤ (አብዛኞቹ ዛሬ በባቢሎን ዱባይ የተሰበሰቡት የእነ ኤፕሽታይን፣ ቢል ጌትስ፣ ጆር ሶሮስ፣ ክላውስ ሽቫብ፣ ቴዎድሮስ አድሓኖም ወዘተ ዘረመል?) በኤም.አር.ኤን.ኤ ኮቪድ ቫክስ ወደ ሴሎችዎ ገብቶ ዘረመልዎን(ዲ ኤን ኤዎን ) ፥ እና መላውን የሰውን ልጅ፤ የሰው ልጅ ራሱ አንድ ዓይነት አይሆንም ፣ የአዕምሮ ሁኔታው ሊለወጥ ይችላል፤ ለዘላለም? ፥ እብደት ይመስላል። ግን አይደለም! የፍሎሪዳ አጠቃላይ የቀዶ ጥገና ሃኪም ዶ/ር ዮሴፍ ላዳፖ “በፍፁም ይህ ሊሆን ይችላል” ብለዋል። በጣም አስደንጋጭ ግን በጣም ጠቃሚ ውይይት። ይህን በትናንትናው ዕለት የቀረበውን ቪዲዮ በአንዱ መስመር(ቻነል) ብቻ ከሁለት ሚሊየን በላይ ሰዎች አይተውታል። ዩቲውብ ያነሳው እንደሆነ እንከታተላለን!
ደፋሩና ለእውነት የቆመው ክርስቲያኑ የሕክምና ዶ/ር ዮሴፍ ላፓዶ ክትባቱን እንዳንወስድ በተደጋጋሚ ሲመክሩን ፥ የእኛዎቹ እነ ዶ/ር ዘበነ ለማ ደግሞ “ተከተቡ! ምንም አትሆኑም! ቅብርጥሴ” በማለት ብዙዎችን ለማሳሳት ቸኩለው ነበር። ለመሆኑ ተጸጽተዋልን? ይቅርታ ጠይቀዋልን? የለም! ዛሬም እራሳቸውን አምላክ አድርገው፣ ውድ ካባዎችንና ሰዓቶችን አጥልቀው፣ ጢማቸውን እያሰማመሩ ተመሳሳይ የተንቀሳቃሽምሥል መልእክቶችን ማስተላለፉን በድፍረት ቀጥለውበታል።
ሁሉም ድፍረት አንድ ዓይነት አይደለም! ሰው ያልሆኑ ሰዎች ምድሪቷን አጥለቅለዋታል! አንተን ወይንም አንቺን የሚመስል ሁሉ አዳሜ/ሔዋኔ አይደለም!
የልሂቃኑን (የእኛዎቹን ጨምሮ)ለብለብነት፣ ቅጥፈት፣ ግድየለሽነት፣ መቅነዝነዝ፣ መወሻከት፣ ጭካኔ እና አረማዊነት እየታዘብን ነውን? “ዋ! ልሂቃኑን አታምልኩ፣ አብዛኛዎቹን መገናኛብዙኅን አትከተሉ! ባጠቃላይ አትከተቡ! በጣም አስፈላጊ ካልሆነ ወደ ሐኪም አትሂዱ!” ብለናል!
👉 አንድን ሰው እንደተታለለ ከማሳመን ይልቅ ማሞኘት በጣም ቀላል ነው።
🛑 ከቱከር ካርልሰን መስመር(ቻናል) የተመረጡ አስተያየቶች፡-
- ► ከከፍተኛው ተራራ ጫፍ ላይ ሆነህ ይህን ጉዳይ አስተጋባ... አመሰግናለሁ፣ እና እግዚአብሔር ይባርክዎ፣ ዶክተር!
- ► የፍሎሪዳ አጠቃላይ የቀዶ ጥገና ሐኪም ጆሴፍ ላዳፖ በጣም አስደናቂ ሰው ነው! ከእሱ ብዙ መስማት እፈልጋለሁ፣ ስለ መንፈሳዊ ህይወቱ የበለጠ ከእሱ መስማት እፈልጋለሁ።
- ► በዚህ የክትባት ሽንገላ ምክንያት የኢንጂነር ስራዬን አጣሁ፣ ክትባቱን ልወስደው አልፈለግኩምና
- ► ሰዎች ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ማስፈራራት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሕገ-መንግሥታዊ ያልሆነ ኢ-አሜሪካዊ ነገር ነበር።
- ► አሳሳቢው ነገር ይህንን ክትባት ያስገደዱት ሰዎች ወደ እስር ቤት አለመግባታቸው ነው። በዚህ ሥራ የተጠቀሙ ሁሉ የዕድሜ ልክ እስራት ይገባቸዋል።
- ► ይህ ምን ያህል አስከፊ እንደሆነ እንኳን ቃላት አይገልጹም።
- ► ይህንን በግዳጅ በሌላው ላይ የገፋፉ እያንዳንዱ ድርጅት፣ መንግስት፣ ዶክተሮች፣ ሰዎች ሁሉ ተጠያቂ መሆን አለባቸው! ፋይዘር( Pfizer)፣ ሞዴርና (Moderna) እና ዶ/ር ፋውቺ (Fauci) ተጠያቂ መሆን አለባቸው!
- ► በሰዎች ዘንድ የሂሳዊ አስተሳሰብ ችሎታዎች መቀነስን ፣ የታዛዥነት/ባርነት መጨመርን እና በሥራ እና በፍጆታ ላይ ብቻ ትኩረት ማድረግን እየታዘብን ነው። እነሱ ግን ይህን እንኳን አያስተውሉትም!
Blogger Comment
Facebook Comment