የተገለባበጠበት ግብዝና ክፉ ዓለም!

✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ 

የአውሮፓ ሕብረት ከሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላዲሚር ፑቲን ጋር ቃለ-መጠይቅ አድርጎ የነበረውን አሜሪካዊ ጋዜጠኛ ታከር ካርልሰን ላይ፤ “ለምን ከዘር አጥፊ ጋር ተገናኘህ” በሚል ክስ ማዕቀብ መጣል ይፈልጋል ፥ በሌላ በኩል ግን አውሮፓ ለዘር አጥፊው ጂሃዳዊ አብዮት አሕመድ ዓሊ ሽልማቶችን ትሰጣለች፣ ጉብኝቶችን ታካሂዳለች!

😈 አንድ የሀገር መሪ ሁለት ወይንም አምስት አስር ሰዎችን ቢገድል፤ ምዕራባውያኑ እና ምስራቃውያኑ ሉሲፈራውያን የዓለማችን ፈላጭ ቆራጮች አጭር የውግዘት መግለጫ በኢንባሲዎቻቸው በኩል ያወጣሉ፣ ለስለስ ያለ ማስጠንቀቂያ ይሰጡታል። (በብዙ ሀገራት እንደሚታየው)

😈 አንድ የሀገር መሪ ሺህ፣ ሃምሳ ሺህ ወይንም መቶ ሺህ ዚጎችን ቢገድል ውግዘቱ ጠንከር ይላል፣ ስለ 'ሰብ ዓዊ መብት ጥሰት' ያጉረመርማሉ፣ የተባበሩት መንግስታት ጸጥታው ምክር ቤት ይጠራል፣ ማዕቀብ ይጣላል። መሪው ግድያውያን ሲያቆም፤ “በቂ ደም አላፈሰስክም!” ብለው ሉሲፈራውያኑ ሠራዊቶቻቸውን “በጸጥታ አስከባሪ” ስም ይልኩበትና ከስልጣን ያስወግዱታል። (በላቲን አሜሪካ፣ በቀድሞዋ ዩጎዝላቪያ፣ በአፍጋኒስታን፣ በሱዳን፣ በሶሪያ፣ በኢራቅ፣ በሊቢያ፣ በማሊ፣ በናይጄሪያ፣ በቡርኪና ፋሶ፣ በጊኒ ቢሳው ወዘተ።

😈 አንድ የሀገር መሪ እስከ አንድ ሚሊየን ወይንም ከዚያም በላይ ዜጎቹን ሲጨፈጭፍ/ሲያስጨፈጭፍ ሉሲፈራውያኑ ለመሪው ባፋጣኝ የሰላምና እርቅ ሂደቶችን ያደርግ ዘንድ ይነግሩትና ውደሳውን፣ ሽልማቱን፣ መሣሪያውንና ገንዘቡን ሁሉ ባፋጣኝ ያጎርፉለታል። (ለግራኝ ኢትዮጵያ + ለዜልንስኪ ዩክሬይን)። እየተፈጸመ ስላለው ግፍና ጭካኔ ዝም ጭጭ ይላሉ። ለዚህም ነው አዲስ አበባ የሚገኙት የተባበሩት መንግስታት፣ የአፍሪካ ሕብረት፣ የአውሮፓ ሕብረት ጽሐፍት ቤቶች እና የምዕራብ ሀገራት ኤምባሲዎች ምንም አይነት ውግዘትና መግለጫ የማይሰጡት። ግልጽ ነው፤ የዘር ማጥፋትን ወንጀል/ የሕዝብ ቁጥር ቅነሳውን (በተለይ የኦርቶዶክስ ክርስቲያኑን) ስለሚፈልጉት ያከብሩታል።

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment