ተጠያቂነትንና ፍትሕን ማምጣት የምንችለው እኛ እና እግዚአብሔር አምላክ ብቻ ነን!

✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ 

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የመጨረሻ ሪፖርት ተናገረ፤ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በኢትዮጵያ የዘር ማጥፋት ጦርነት ለተጠቁ ንጹሐን ተጠያቂነትንና ጥበቃን ማረጋገጥ አለበት።

የተለመደውን ጨዋታቸውንና ፌዛቸውን ቀጥለውበታል። ከኢትዮጵያና አርሜኒያ ጉዳይ ርቀው በተለመደው የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳይ ላይ እራሳቸውን ለመዝፈቅ ሲሉ ያወጡ የመጨረሻ ረፖርት መሆኑ ነው። ተመልከቱ ለአሸባሪዎቹ ፍልስጤማውያን ሙስሊሞች ምን ያህል እንደሚቆረቆሩ። መግለጫዎችን በየሰዓቱ ያወጣሉ፣ ለኢትዮጵያ ክርስቲያኖች የምግብ እርዳታ ባቆሙበት ወቅት ለፍልስጤማውያን ሙስሊሞች ግን ወዲያው ሲያቀርቡ ይታያሉ፤ ሩብ ቢሊየን ዶላር ለማዋጣት ተስማምተዋል። ለፍልስጤም ሙስሊሞች የሚወጡትን ምዕራባውያንና ምስራቃውያን ሰልፈኞች ተመልከቱ፣ የአረንጓዴ እና የግራ ፓርቲዎች ሴቶች ካሜራ ፊት እየወጡ እንባቸውን እንዴት እንደሚያጎርፉ እንታዘብ። ግብዞች!

አዎ! በሰይጣን የሚመራው ባለ ሶስት አቅጣጫዊው ዓለም በስጋዊ መንገድ ብቻ ነውና የሚያስበው "የራሴ" ለሚላቸው ሕዝቦችና ግለሰቦች ብቻ ነው የሚቆመው።

በኢትዮጵያና አርሜኒያ ክርስቲያን ሕዝባችን ላይ እየተፈጸመ ላለው ከባድ ግፍና በደል ተጠያቂነትንና ፍትሕን ማምጣት የምንችለው እኛ እና እግዚአብሔር አምላክ ብቻ ነን። ለእነዚህ አረመኔና ጨፍጫፊ ሀገራት፣ ማሕበረሰባት፣ ግለሰቦችና ተቋማት እግዚአብሔር አምላክ የፍርዱን ምልክቶች እያሳያቸው መሆኑን እየታዘብን ነው፤ ፍርዱ አይዘገይም።

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment