✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ከ ፩/1 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችን የጨፈጨፉት የክርስቶስ ተቃዋሚዎች እንዲህ አብረው ያፍሩ እና ይዋረዱ ዘንድ ግድ ነው።
ሉሲፈራዊ የጆ ባይደን አስተዳደር በአሜሪካን በዓለም ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት መገመት ከባድ ነው።
ከእስራኤል ጋር የቅርርቦሽ ድርድር ካቋረጠች በኋላ ሳዑዲ ዓረቢያ ዩናይትድ ስቴትስን በድጋሚ አሸማቀቀቻት። ዋሽንግተን ፖስት እንደዘገበው በሪያድ የሳዑዲው አልጋ ወራሽ እባቡ ልዑል መሐመድ ቢን ሳልማን የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ምሽት ላይ ሊደረግ ነው ተብሎ የሚገመተውን ስብሰባ ለብዙ ሰዓታት ሲጠብቅ ቆይቶ ግን መሐመድ በማግስቱ ማለዳ ላይ ብቻ መገኘቱን ዘግቧል። ይህ ከጥቅምት ፯/7ቱ የአሸባሪው ሐማስ ጥቃት በኋላ እስራኤል በጋዛ ላይ ምላሽ ጥቃት በምትፈጽምበት በዚህ ሞቃታማ ወቅት መከሰቱ የሚያስገርም ነው።
ዓለምን በማመስ ላይ ያለው የእስማኤል እና የዔሳው ሕብረት መፈራረሱ አይቀርም።
ከአረመኔው ግራኝ ጋር የተገናኘ ሁሉ፡ ማፈሩ፣ መፈራረሱና መውደቁ የማይቀር ነው።
ግን እነዚህ የዓለማችን ግብዝ ፈላጭ ቆራጮች ለእነዚህ ከንቱ ለሆኑ የመካከለኛው ምስራቅ ሕዝቦች ምን ያህል እንደሚጨነቁላቸውና እንደሚሳሱላቸው አብረን እንታዘበው። የኛዎቹም ከሕዝባቸው መከራ፣ ስቃይና ሐዘን ይልቅ የዓረቦቹና የአይሁዶቹ ጉዳይ በልጦባቸው ጊዚያቸውንና ጉልበታቸውን በከንቱ እንደሚያባክኑ እያየን እንዘን፣ እንቆጣ! ራሱን የማይወድ ሌላውን ሊወድ ብሎም በሌላው ሊወደድ ይችላልን? በጭራሽ አይችልም!
Blogger Comment
Facebook Comment