✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
በሊቢያ ከፍተኛ የጎርፍ መጥለቅለቅ ከደረሰ በኋላ ከሁለት ሺህ በላይ /+2000 ሰዎች ሞተዋል የሚል ስጋት ደርሷል።
“ዳንኤል” የተሰኘው የሜዲትራኒያን ባሕር አውሎ ነፋስ ነው ከባድ ጎርፍ ያስከተለው።
በዚሁ አካባቢ ነበር ከስምንት ዓመታት በፊት ሰላሳ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያን ወንድሞቻችን በመሐዳውያኑ ታርደው የሰማዕትነት አክሊልን የተቀዳጁት።
የሚገርም ነው፤ “ዳንኤል” የሚል ስያሜ የተሰጠው አውሎ ንፋስ፤ ቃኤላዊውን ጋንኤል ክብረትን አስታወሰኝ። ይህ ወራዳ ከሃዲ በውንድሞቻችንን ሬሳ ላይ ለመነገድ ከአራት ዓመታት በፊት በአረመኔው ግራኝ ወደ ሊቢያ ተልኮ ነበር።
ያኔ ዜናው እንዲህ ብሎን ነበር፤
“የጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ አማካሪ ዳንኤል ክብረት ወደ ሊቢያ አቅንተው በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እውቅና ከተሰጠው መንግሥት የውጭ ጉዳይ ምኒስትር መሐመድ ሳያላ ጋር በሊቢያ መረጋጋት እና የሁለቱ አገሮች ግንኙነት ላይ ተወያይተዋል።”
ኢየሱስ ክርስቶስ ፥ አንድ እና ብቸኛ ኃያል እግዚአብሔር አምላክ ፥ ነፍሳቸውን ይማርላቸው መጽናናትን ይስጣቸው!
Blogger Comment
Facebook Comment