የምድር እምብርት (የረር) እና የኢትዮጵያ ትንሣኤ፤ በአክሱማውያኑ የተሠራው የረር ሥላሴ



✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ 

ዙሪያዋን በአሕዛብ ሀገራት ተከብባ እርሷ ግን በአራቱም ማዕዘኗ መስቀሉን ከፍ አድርጋ ሰቅላ ኢየሱስ ጌታና መድኃኒት ነው ብላ በዓቢይ ቃል እየሰበከች ያለች ድንቅ አፍሪካዊ ሀገር ኢትዮጵያ ናት።

በ፬/4ኛው ምዕተ ዓመት ላይ በኢትዮጵያና አካባቢዋ ነግሥው ሲያስተዳድሩ የነበሩት አብርሃወአጽበሃ በሥላሴ ስም ይህችን ቤተከርስቲያን አሰርተዋት እንደነበር አሁን በደንብ ለማወቅ ተችሏል። ባካባቢው ገና ብዙ ምስጢራዊ የሆኑ ነገሮች እንደሚገኙ ይታመናል። ሣርና ዛፎች በሚገኙበት ቦታ ላይ ከየት እንደሚመጣ የማይታወቀው የሚጤስ ዕጣን ሽታ አልፎ አልፎ እንደሚሸታቸው ሰዎች ይናገራሉ። በጣም ቅዱስ የሆነ ጽላትም አሁን ቤተክርስቲያን የተሰራበት ቦታ አካባቢ ጥልቅ መሬት ውስጥ ተደብቆ እንደሚገኝ ነገር ግን እሱን እስካሁን ለማውጣት እንዳልተቻለ የኃይማኖት መሪዎች አውስተውኛል።

ንጉሥ ኢዛና በ፬/4ተኛው ምዕተ ዓመት(፫፻፴/330 እስከ ፫፻፷/360)ላይ እግዚአብሔር የጠቆማቸውን “ኢትዮጵያ” የሚለውን መጠሪያ ለአክሱም ሥርወ መንግሥት ተጠቀሙ። እስከ አዲስ አበባ(የረር ተራሮች)፣ ሐረር፣ ነቀምት፣ ጣና ሐይቅ ወዘተ የሚዘልቁት ቦታዎች ሁሉ የእነ አብርሃ ወአጽበሐ ግዛቶች ናቸው። በዝቋላ እና ዝዋይ ሐይቅ አካባቢ የሚገኙት ዓብያተ ክርስቲያናት እና ገዳማት ሁሉ በአክሱማውያን የተመሠረቱ መሆናቸውን አንርሳው!

ቅዱሳን መላእክት አባታችን አዳምን የምድራዊ ሰማያትን እና የሰማያተ ሰማያትን ምስጢራት እና ጥበባትን አስተምረውታል፡፡ ታዲያ አባታችን አዳም ርስት ተደርጋ በተሰጠችው ኢትዮጵያ እና የምድር ማእከላዊ ስፍራ በሆነው የረር በሚገኘው ተራራ ላይ ለኢትዮጵያውያን ልጆቹ ያገኘውን የረቀቀ የሰማያተ ሰማያትና የምድራዊ ሰማያትን ጥበቦች ስላስተማራቸው በዘመናቸው ሃያል እና ገናና ህዝቦች ሆነው አልፈዋል፡፡ ኢትዮጵያውያን እስከ ሁለተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጨረሻ ድረስ ሀያላን ሆነው የዘለቁበት ምክንያት ለዚህ ትውልድ እና ለተቀረው ዓለም የተሰወሩትን ስድስቱን ምስጢራትን ተረድተው በመጠበቃቸው ነው፡፡ እነዚህ ስድስቱ ምስጢራተ ጥበባት ሰማያዊ የሆነው ምስጢር በመያዛቸው የዓለማችን የሃይል ሚዛን የመቀየር አቅም አላቸው ቢሆንም ግን ከሶስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኃላ ከስድስቱ ምስጢረ ጥበባት ወጥተን እንደራሳችን ሀሳብ መራመድ ስንጀምር ነገሮች ሁሉ ተሸፈኑብን ወደ ስድስቱ ምሲጢረ ጥበባት የሚያደርሰን መንገድም ተዘጋብን፡፡

ይህ ቢሆንም ግን ሀገራችን ኢትዮጵያን ከሌላው ሀገራት ለየት የሚያደርጋት ሌሎች ነገሮች አሉ ይህም ደግሞ የሀገራችንን ታሪክ ብቻ ሳይሆን የዓለማችን ታሪኮች መዝግባ ይዛ ለዚህ ዘመን ማድረስ መቻሏ ነው፡፡
 ለዚህም ትልቁን የአንበሳ ድርሻ የምትይዘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትን ናት፡፡ ኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ሲሆኑ አብዛኛውን የዓለማችንን የተነገሩም ያልተነገሩ ታሪኮችን ይዛ ያቆየቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ናት፡፡

ኢትዮጵያ በአንድም በሌላው መልኩ ስልጣኔን በዓለማችን ላይ ያስፋፋች ቀዳሚ ሀገር ስትሆን ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ሰዎች ወደሃገራችን በመምጣት ፍልሰፍናን የአስተዳደር ስርአተን ሃይማኖታዊ ትምህርቶችን የጊዜ አቆጣጠርን እና ሌሎች በርካታ ጥበቦችን ከአባቶቻችን በመማር ወደተቀረው የዓለማችን ክፍሎች አስፋፍተዋል፡፡

ቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያ ፈጣሪዋን አውቃ በሶስቱም ህግጋት እግዚአብሔርን ስታመልክም ማንም ቀዳሚ አልነበራትም ዓለም ሁሉ በአምልኮ ጣዖት ባህር ውስጥ ሲዋኝ በሞራል ስብራትና ስነልቦናዊ ውዥንብር ውስጥ ተዘፍቆ አምላኩን ሲያሳዝን በነበረት ዘመን ሁሉ እንደ ርእሰ አበው እንደ አብርሃም በተፈጥሮ ባገኘችው እውቀት የእግዚአብሔርን ሀልዎትን አውቃ ከኔ በቀር ሌላ አምላክ አታምልክ የሚለውን አምላካዊ ቃልና ሌሎችን ትእዛዛት ተቀብላ የኖረችበት በእግዚአብሔር ፈቃድም በቀዳማዊ ምንሊክ አማካኝነት ታቦተ ጽዮንን አምጥታ ለመስዋእተ ኦሪት የኖረች የክርስቶስን የባህርይ አምላክነት በፍጹምነት አምና በመቀበል በእግዚአብሔር ትእዛዝ በሐዋርያው በፊሊጶስ እጅ የተጠመቀች ሀገረ እግዚአብሔር መሆኗም በቅዱሰ መጽሀፍ በብዙ ስፍራ የተረጋገጠላት የቅዱሳን ማረፊያ የምስጢራት ምድር ጥናታዊት ሀገር ናት፡፡

ታዲያ የኢትዮጵያ ገናናነት እና ሃያልነት ከቅርብ መቶ ዓመታት ወዲህ እየተዳከመ ጥበቦቿ እና ምስጢራቶቿ እንዲሁም ስልጣኔዋ እየደበዘዘ መጥቷል ለዚህም ዋነኛው ምክንያት ከቅዱሳን መላእክት ያገኘነውን የምድራዊ እና የሰማያዊ ሰማያትን ጥበባት በአንድነት ጠቅልለው የያዙትን ስድስቱን ምስጢረ ጥበባት ችላ ከማለታችን በተጨማሪ በእግዚአብሔርና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የማያቋርጥ ፍቅር እና ትስስር ችላ በማለት በምዕራባውያን ባህል እና የፖለቲካ ፍልስፍና በመተካታችን ነው፡፡ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች [መዝ ፷፰፥፫፡]የሚለውን መጽሀፍ ቅዱሳዊ ቃል ዘንግተን እጃችንን ለልመና ወደ ምዕራባውያን ሀገራት መዘርጋት የጀመርን ጊዜ ባለፈው ሃያል እና ገናና በነበረው እና በዚህ ትውልድ መካከል የነበረው አሻጋሪ ድልድይ ተሰበረ ሰፊ የትውልድ ልዩነትም ተፈጠረ፡፡ እግዚአብሔርን ሳይሆን ገንዘብን ማምለክ ጀመርን በምዕራባውያን ላይ አድሮ የሚሰራው የሉሲፈር መንፈስ በኛም ላይ እንዲሰራ ራሳችንን አስገዛንለት በዚህም የተነሳ ከሰማይ ከሰማያዊ ሃይላት ያገኘነው እውቀት ጥበባት ሃብታት ሁሉ እየተሰወሩብን እና እየደበዘዙብን ሄዱ ዓምላክም በዚህ በማዘኑ አሳልፎ ሰጠን፡፡
ዓለም ገና ጨለማ ውስጥ በነበረችበት ወቅት የእውቀት ብርሃን ፈነጥቆባት የነበረችው ኢትዮጵያ ዛሬ ዛሬ በልጆቿ ጨልሞባት የራሳችን ትተን እውቀት ፍለጋ የምእራባውያንን ጭራ እየተከተልን እንገኛለን፡፡
ይህ በምዕራባውያን ማንነቱን የተሰለበ አራተኛውና የመጨረሻው ትውልዳችንን ከሞራል ስብራትና ዝቅጠት ውስጥ ለማውጣት ብሎም ብቁ መንፈሳዊ ዜጋ በማድረግ ኢትዮጵያን ሀገረ እግዚአብሔር ለማሰኘት ብሎም የጥንቷን አክሱማዊት ኢትዮጵያ ዳግም ለመመልከት የአባቶቻችን ዕውቀቶች እና ጥበቦች ማጋራት ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ነገር ነው፡፡ የአባቶቻችን አስተምህሮት የሆነውን አምሳላዊ ንድፈ ሀሳብ መሰረት በማድረግ ስለ አስራ ሁለቱ ሰማየ ሰማያት እና ምድራዊ ሰማያት እና ከየረር ተራራና ከሌሎቹ ስድስት የክብር ቦታዎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት መመልከት አለብን፡፡

በተምሳሌታዊ እውቀት ትንታኔ መሰረት ማንኛውም ፍጥረት የተፈጠረበት በፍጻሜ ላይ የሚገኝ አሳብ አለው በዚህ መሰረትም ምድራዊ ሰማያት የሰማያተ ሰማያት አምሳል ናት፡፡ በመሆኑም በሰማያተ ሰማያት የሚገኙ ስፍራዎች የፈጣሪያችን መገኛ የሆነውን ማእከላዊ ስፍራ በአራት አቅጣጫ ከበውት እንደሚገኙ እንዲሁ የምድራዊ ሰማያት ክፍል የሆኑት አስራሁለት ስፍራዎች በአራት አቅጣጫ የፈጣሪ ማደሪያ አምሳል በሆነችው ጸሀይ ዙሪያ ይገኛሉ፡፡ ይህን በተምሳሌታዊ ንድፈ ሃሳብ መሰረት ድርሳነ ዑራኤልን ጨምሮ በተለያዩ ቅዱሳን አዋልድ መጻህፍት እና አባቶች የምድር እምብርት ተብሎ የተጠቀሰው በየረር ተራሮች መሃከል የሚገኘውን ምስጢራዊ ተራራ መሀከል አድርገን ስናጠና ቦታውን በአራት አቅጣጫ የሚከቡትን የምድራዊ ሰማያት አቀማመጥ እንረዳለን፡፡

አባታችን አዳም አትብላ የተባለውን እጽ በልቶ ከገነት በተባረረበት ወቅት ቅዱሳን መላእክት በምድራዊ ሰማያት በሁለተኛው ምድብ ከሚገኘው ስፋራ ወደአንደኛው ምድብ ወደምትገኘው ወደዚች ምድር በመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል አማካይነት ሲመጣ መጀመርያ ያረፈውና መጽናኛ ትሆነው ዘንድ ርስት ተደርጋ የተሰጠችው ስፍራ በየረር ተራሮች መካከል በምትገኘው እና የምድር እምብርት በሆነችው ተራራ ላይ ነው፡፡ ይህን ተራራ መሀከል አድርገን በስተሰሜን ስንመለከት የበርካታ ቅዱሳን አባቶች መገኛ የሆነው ደን እና ዋሻዎች እናገኛለን እነዚህ የበቁ የተሰወሩ አባቶች የሚገኙበት ስፍራ በሁለተኛው የምድራዊ ሰማያት ምድብ በሆነው ክፍል ብሄረ ህያውን የሚገኝበት ቦታ እንደሆነ ልብ ይበሉ በተጨማሪ ሰባቱ ምድራዊ ሰማያት የበርካታ አእዋፋት መኖርያ ሲሆን በዚሁ አቅጣጫ በርካታ አሞሮችና አእዋፋት ወደየረር ማእከላዊ ቦታ ይመጣሉ ይህም አዳም ገነት በነበረበት ወቅት ከሌሎቹ ሰማያት ሊጠይቁት እንደሚመጡት ማለት ነው፡፡ ይህን አንድምታ ስንፈታው በዚህ ተራራ ስር ከሚገኙት ዋሻዎች በአንዱ የሚገኘውን የበቃ ባለትንቢቱን አባት ለመጠየቅ እና ለመመልክት ከቅዱሳን ስፍራ አእዋፋት እና ቅዱሳን ይመጣሉ፡፡

የተለያዩ ከብሔረ ህያዋን የሚመጡ ቅዱሳን አባቶችን ጨምሮ ቅዱሳን መላእክት ለመልእክት ወደምድር ሲመጡ የሚያርፉባቸው ሰባት የተመረጡ ቦታዎች አሉ፡፡ እነዚህ የክብር ቦታዎች በሰማያተ ሰማያት እና በምድራዊ ሰማያት መካከል ግንኙነት የሚፈጠርባቸው ታላቅ መንፈሳዊ ቦታዎች ናቸው፡፡ ከእነዚህ ሰባት የክብር ቦታዎች መካከል አራቱ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን አንደኛው የመን ውስጥ ሌላው በሲና በርሃ የተቀረው ደግሞ በእስራኤል ምድር ውስጥ ይገኛል፡፡ እነዚህ የተቀሩት ቦታዎች ቀድሞ በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙት የክብር ቦታዎች ዋንኛውና አንደኛው በየረር ተራሮች መካከል የሚገኘውና በበርካታ ቅዱሳን መጽሃፍት የምድር እምብርት በተጨማሪም የአዳም ርስት ሃገር ብለን የምንጠራው ስፋራ ነው፡፡ ይህ የምድር እምብርትና ከሰባቱ የክብር ቦታዎች አንዱ የሆነው የአዳም ርስት ቦታ ሶስት ስፍራዎችን በአንድነት ይዟል፡፡
የመጀመሪያው የዋሻዎቹ መገኛ ስፍራ ሲሆን ሁለተኛው ከዚህ ተራራ ባሻገር የሚገኘው የረር ብለን በምንጠራው ተራራ መካከል ላይ የሚገኝ ስፍራ ነው ይህም ስፍራ በስተደቡብ የሚገኘውና እመቤታችን ልጇን ይዛ በተሰደደችበት ወቅት ከዚህ ስፍራ ተገኝታ ነበር፡፡ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ሀገራችን ኢትዮጵያን አስራት ሀገር አድርጎ የሰጣት በዚህ ስፍራ ላይ ነው፡፡ በዚህም የተነሳ ለስም አጠራሯ ምስጋና ይድረሳትና አሁንም ድረስ የእመቤታችን በረከት ከቦታው ላይ አልተለየም፡፡

ሶስተኛው ክፍል በዋሻዎች መገኛ በምድር ውስጥ የሚገኘው ስፍራ ነው፡፡ የዚህን ተራራ ምስጢር ለመረዳት የቤተክርስትያናችንን አሰራርን ምሳሌ በማድረግ እንመልከት፡፡ በዚህ አካባቢ የሚገኘው ይህ ቤተክርስትያን ሁለት ክፍል ያለው ሲሆን ከመሬት በታችችና በላይ የሚገኘው ክፍል ነው፡፡ ይህ ቤተክርስትያን በሁለት አስተዳዳሪዎች ይመራል የመጀመርዎቹ በአካል የምናገኛቸው አስተዳዳሪዎች ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ በምስጢር ቤተክርስትያኗን እያስተዳደሩ የሚገኙት የተሰወሩ አባቶች ናቸው በዚህ መሰረት የአዳምን ርስት ቦታ የሆነውን ክፍል ስንመለከት ከውጭ በሚገኘው የተራራው ስፍራ በሰሜን በደቡብ እና በምስራቅ በኩል የሚገኙ ዋሻዎች የሚገኙ ሲሆን የታራራው ሌላኛው ክፍል ደግሞ ከተራራው የውስጠኛ ክፍል እና ምድር ውስጥ የሚገኘው የተሰወሩት ከተሞች ናቸው፡፡ በዚህ የውስጠኛው የተሰወረው የከተማው ክፍል ውስጥ አባታችን አዳም ከገነት በተመለሰ ወቅት ለኛ ለህዝቦቹ ቅዱሳን መላእክት ያስተማሩትን የሰማያተ ሰማያት እና የምድራዊ ሰማያት ምስጢራትና ጥበባት እንዲሁም የምድራችንን የሃይል ሚዛን ጠቅልለው የሚይዙት ስድስቱን የክብር እቃዎች ያስቀመጠበት ቦታ ነው፡፡ እነዚህ ሶስት ስፍራዎች በአጠቃላይ የአዳም ርስት ሃገር እንብርት ተብለው ይጠራሉ፡፡

ታዲያ ወደዚህኛው የተራራው ውስጠኛው ስውር ከተማ ለመግባት ሶስት በሮች የሚገኙ ሲሆን የመጀመርያው በምስራቅ በኩል በቴዎድሮስ ቤተክርስትያን ይገኛል፡፡ በዚህኛው መግቢያ በር መጠቀም የሚችሉት ከብሔረህያዋን የሚመጡት ብሎም በዚህ ምድር የሚገኙ ግን የበቁ ስዉራን አባቶች የሚጠቀሙበት በር ነው፡፡ ሁለተኛው መግቢያ በር በምድራዊ ሰማያት ሁለተኛው ምድብ የሚገኙበት እና ጠባቂያቸው ንስር አሞራ በሚገኝበት ስፍራ የሰሜን አቅጣጫ ይገኛል፡፡ በዚህ ስፍራ ሲጠቀሙበት የነበሩት ከሁለተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አስቀድሞ የነበሩት የኢትዮጵያውያን ነገስታት ሲሆኑ ከዚህ በኃላ የገዥነት ክብሩን ይዞ የሚመጣው ንጉሳችን ቶዎድሮስ የሚጠቀምበት መግቢያ በር ነው፡፡ ሶስተኛው መግቢያ በር በስተደቡብ በኩል በእመቤታችን ቤተክርስትያን በኩል ይገኛል፡፡ በዚህ መግቢያ በር የሚጠቀሙት ሴት ነገስታት ናቸው፡፡
ሁለተኛው መግቢያ በር በሚገኝበት እና በርካታ አእዋፋት በሚገኙበት ስፍራ በርካታ የተሰወሩ ቅዱሳን አባቶች የሚገኙ ሲሆን ከእነዚህ አባቶች መካከል በስጋዊ ህይወታቸው ስኬታማ የነበሩና በዓለማዊ ትምህርታቸው እስከ ሶስተኛ ድግሪ የዘለቁ ቢሆንም ግን ይህን የምእራባውያንን ጥበብ በመናቅ ስድስቱን ምስጢረ ጥበባት ለማጥናት ራሳቸውን ያስገዙ ናቸው፡፡ እነዚህ አባቶች መካከልም የኢትዮጵያን ትንሳኤ ሳያዩ እንዳይሞቱ ቃልኪዳን ተገብቶላቸው ከሁለት መቶ ሀምሳ አመት በላይ እድሜ ያስቆጠሩ አባቶችም ይገኛሉ፡፡ ሌላው የሚስደንቀው የኢትዮጵያ ትንሳኤ ቅርብ እንደመሆኑ የዓለማችንን የሃይል ሚዛን ዳግም ለመቀልበስ ስድስቱ ምስጢረ ጥበባት ላይ ሰፊ የሆነ መንፈሳዊ ስራን የሚሰሩና ከስማዝያ ወይም ከምስጢር ሰዎች ገዥ ከሆነው ክፉ መንፈስ ጋር ጦርነት ገጥመው እያሸነፉ ያሉ የቅዱሳን አባቶች ህብረት የሚገኝበትም ስፍራ ነው፡፡ ይህን የሚያውቁ አንዳንድ ዓለምዓቀፍ ተቋማትም ሆኑ የውስጥ አካላቶች ቦታው ላይ እና የአባቶቻችን ህብረት ላይ ጥቃት በመሰንዘር የአካባቢውን ምስጢር ለመቆጣጠር ቢሞክሩም የረር ግን ራሱን ይጠብቃል ምንም ማድረግ አልቻሉም፡፡

አባታችን አዳም ይህችን ቦታ ርስት አድርጎ ካገኘበት ጊዜ ጀምሮ በምድራችን ላይ የነበሩት አባቶቻችን በየረር በሚገኘው የምድር ማእከል ስር የተቀመጠላቸውን ስድስቱን ምስጢረ ጥበባት እና ስድስቱን የክብር እቃዎች አንድ ላይ ባዋሃዱበት ምስጢራት በመመራት እና በጥበቦቹ ጸንተው በመኖር ታላቅ ህዝቦች ሆነው አልፈዋል፡፡ እነዚህ ስድስቱ ምስጢረ ጥበባት ከሰው አእምሮ የሚረቁ ጥበቦች የያዙ ሲሆን ከሁለተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጨረሻ በኃላ በተለያዩ ምክንያች ስድስቱን ምስጢራተ ጥበባቶች ችላ በማለታችን ከፍ ካልንበት የሃያልነታችንን ዘውድ አሽቀንጥረን ጥለን የውርደት ካባን ተከናንበናል፡፡ለዚህም ታላቁን ሚና የተጫወቱት የስማዝያ ወገን የሆኑት አይሁዶችና የምስጢር ቡድኖች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ጠላቶቻችንም ዳግም ወደነበርንበት የገዥነት ዙፋን እንዳንመለስ እነዚህን ስድስቱ ምስጢራተ ጥበባትን ከአእምሮዋችን ለመስለብ ብዙ ሴራዎች የሰሩ ሲሆን ወደመጨረሻ በሰፊው እንመለከተዋለን፡፡ ስለዚህ የኢትዮጵያን ትንሳኤ ስናልም ስድስቱ ምስጢራተ ጥበባት አያይዘን ማሰባችን ብሎም ትውልዱን ስለነዚህ ጥበባት ግንዛቤ መፍጠር የመንገዱ ግማሽ መንገድ ነው፡፡ ልብ ይበሉ ጊዜው ደርሷል ኢትዮጵያ ትንሳኤ ቀርቧል ስድስቱ ምስጢራተ ጥበባትና ስድስቱ የክብር እቃዎች መገለጫ ምልክቱም ይህ ነው አንዳንዶቻችን ይህን መነጋገር መጀመራችን . . .
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment