✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ሐምሌ ፯/7 ቀን ሥላሴ በአባታችን አብርሐም ቤት የተገለፀበት በዓል፣ መታሰቢያ ነው፡፡ የሠራዊት ጌታ እንደ ሰዶምና ገሞራ እንዳንጠፋ ዘርን አስቀረልን።
ግብዞቹ የግራኝ መጋቢዎች 'ገዳም እንሠራበታለን' ከሚሉባት ካሊፎርኒያ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ነዋሪዎቿ ለቅቀው በመውጣት ላይ መሆናቸውን ልብ እንበል።
❖❖❖[ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ፲፱]❖❖❖
፳፪ በቶሎ ወደዚያ ሸሽትህ አምልጥ፤ ወደዚያ እስክትደርስ ድረስ ምንም አደርግ ዘንድ አልችልምና። ስለዚህም የዚያች ከተማ ስም ዞዓር ተባለ።
፳፫ ሎጥ ወደ ዞዓር በገባ ጊዜ ፀሐይ በምድር ላይ ወጣች።
፳፬ እግዚአብሔርም በሰዶምና በገሞራ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ከሰማይ እሳትና ዲን አዘነበ፤
፳፭ እነዚያንም ከተሞች፥ በዙሪያቸው ያለውንም ሁሉ፥ በከተሞቹም የሚኖሩትን ሁሉ፥ የምድሩንም ቡቃያ ሁሉ ገለበጠ።
፳፮ የሎጥም ሚስት ወደ ኋላዋ ተመለከተች፥ የጨው ሐውልትም ሆነች።
፳፯ አብርሃምም በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ ወደ ነበረበት ስፍራ ለመሄድ ማልዶ ተነሣ፤
፳፰ ወደ ሰዶምና ወደ ገሞራ በዚያች አገር ወዳለውም ምድር ሁሉ ተመለከተ፤ እነሆም የአገሪቱ ጢስ እንደ እቶን ጢስ ሲነሣ አየ።
፳፱ እግዚአብሔርም እነዚያን የአገር ከተሞች ባጠፋ ጊዜ አብርሃምን አሰበው፤ ሎጥ ተቀምጦበት የነበረውንም ከተማ ባጠፋ ጊዜ ከዚያ ጥፋት መካከል ሎጥን አወጣው።
MASS EXODUS: Nearly HALF of Californians Are Considering Leaving the State
የጅምላ ስደት ከካሊፎርኒያ፡- ኑሮ እየከፋ በመምጣቱ ግማሽ ያህሉ የካሊፎርኒያ ነዋሪዎች ግዛቱን ለቀው ለመውጣት እያሰቡ ነው።
ዶክተር ዘበነ! እኔ ደግሞ 'አህያውን' ትንሽ በዱላ ይገስጹት ይሆን ብዬ ነበር። ከዚህ በፊት ሕዝበ ክርስቲያኑ የአውሬውን ክትባት ይከተብ ዘንድ ወተውተው ስንቱን በከንቱ አስከተቡት። እግዚኦ! አሁን ደግሞ፤ ልክ ቅዱሳን መላእክት ሎጥን ከሰዶም አውጥተው፥ “ወደዚያ ሸሽተህ አምልጥ፤” እንደ አሉት፡ እርስዎም ሕዝበ ክርስቲያኑን ከሰዶምና ገሞራ ካሊፎርኒያ አምልጥ! እንደማለት ለፋሺስቱ ኦሮሞ አገዛዝ ድሮን መግዢያ ዶላር የሚሰበስበውን ቀልደኛ ለመደገፍ ብቅ አሉ። ያውም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች በረሃብና በጥይት በሚረግፉት በዚህ ወቅት። እግዚኦ! እስኪ በአክሱም ጽዮን ባለማህተቡን ኦርቶዶክስ ጽዮናዊ በማስረብ ላይ እና ሬሳ በማቃጠል ላይ ስላሉት አረመኔ አሕዘብ ዲያብሎሳዊ ተግባር ይተንፍሱ!
የእስማኤላዊ ገጽታ ያለውንና የመሐመድ ጋኔን ያረፈበትን “ኮሜዲያን እሸቱ” በዚህ ለሀገራችንና ለክርስቲያኑ ሕዝባችን እጅግ በጣም አሳዛኝና አስለቃሽ በሆነ ዘመን እስኪ ይህ ኮሜዲያን እሸቱ የተባለው አጭበርባሪ እንዴት እንደሚፈነድቅ፣ እንደሚገለፍጥና አጋንንታዊ ገጽታውን እንዴት እንደሚያሳይ ዓይን ያለው ይመልከት።
በዚህ ዘመን የሚፈነድቁትና ያለማቋረጥ ገንዘብ ገንዘብ ገንዘብ የሚፈልጉ የሚሉት አሕዛብ የዋቄዮ-አላህ ባሪያዎች፣ ፕሮቴስታንቶች እንዲሁም በመቐለ እና አዲስ አበባ ቤተክህነት ውስጥ የተሰገሰጉት ተሐድሶዎች ብቻ ናቸው። የክርስቶስ ቤተሰብ ዛሬ አይታየም፣ አይሰማም፣ እያነባ ነውና። ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው ይለናል ቅዱስ ቃሉ።
ጊዜው የሚያዘናጋ፣ የሚያዘልል፣ የሚያስፈነጭ የሚያስጨበጭብ ጊዜ አይደለም ፥ ለጸሎት የምንነቃበት ጊዜ እንጂ ሕዝብ ሲያምጽ፣ ኃጢዓት ሲበዛ፣ ጽዋ ሲሞላ እምቢ ለሚል እግዚአብሔርን ለሚገዳደር በተናጠል ይቀጣል።
[መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ ፫፥፩፡፰]
"ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው፤ ከሰማይ በታች ለሚከናወነው ለማንኛውም ነገር ወቅት አለው፤ ለመወለድ ጊዜ አለው፤ ለመሞትም ጊዜ አለው፤ ለመትከል ጊዜ አለው፤ ለመንቀልም ጊዜ አለው፤ ለመግደል ጊዜ አለው፤ ለማዳንም ጊዜ አለው፤ ለማፍረስ ጊዜ አለው፤ ለመገንባትም ጊዜ አለው፤ ለማልቀስ ጊዜ አለው፤ ለመሣቅም ጊዜ አለው፤ ለሐዘን ጊዜ አለው፤ ለጭፈራም ጊዜ አለው፤ ድንጋይ ለመጣል ጊዜ አለው፤ ድንጋይ ለመሰብሰብም ጊዜ አለው፤ ለመተቃቀፍ ጊዜ አለው፤ ለመለያየትም ጊዜ አለው፤ ለመፈለግ ጊዜ አለው፤ ለመተው ጊዜ አለው፤ ለማስቀመጥ ጊዜ አለው፤ አውጥቶ ለመጣልም ጊዜ አለው፤ ለመቅደድ ጊዜ አለው፤ ለመስፋትም ጊዜ አለው፤ ለዝምታ ጊዜ አለው፤ ለመናገርም ጊዜ አለው፤ ለመውደድ ጊዜ አለው፤ ለመጥላትም ጊዜ አለው፤ ለጦርነት ጊዜ አለው፤ ለሰላምም ጊዜ አለው።"
አልተነገረንም እንዳይሉ። የቀጥታ ስርጭት ወይንም 'LIVE'የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል ሲገለበጥ 'EVIL' – 'DEVIL'የሚለውን ይሰጠናል። በኢንተርኔት፣ በተለይ በቀጥታ ስርጭት እራሳቸውን በምስል የሚያሳዩና መልእክቶቻቸውንም በድምጽ የሚያቀርቡ ሁሉ፣ እንደበፊቱ ሬዲዮ አደገኛ ባልሆነ የአየር ሞገድ ላይ ስለማይገኙ ለብዙ ፈተና እንደሚጋለጡ ከብዙ ዓመታት ጀምሬ ሳስጠነቅቅ ነበር። እኔ በምስልና በድምጽ በቀጥታ የማልመጣበት ምክኒያት ይህን ፈተና መጋፈጥ ስለማልሻ መሆኑንም ጠቁሜያለሁ። ለነገሩማ ሥራየ ነው።
'ሳዲቅ አፍጋን' የተባለው ፈላስፋና የሒሳብ ሊቅ (ከሳምንት በፊት በአፍጋኒስታን ታሊባኖች ታግቷል) የቱርኩን የመሬት መንቀጥቀጥ ተንብዩአል የተባለለት ሰው፣ በመጭው ሰኞ ሐምሌ ፲ / ጁላይ 17/ አስራ ሰባት ዓለምን የሚቀይር ክስተት ይከሰታል ብሏል። ቀኑን መናገሩ እንዳላምነው አድርጎኛል፤ ሆኖም በሰሜን ሀገሮች፣ ሙቀት በጣም የሚጨምርበት፣ ፀሐይዋም ከጠነከረች ኢንተርኔት የሚቋረጥበት ጊዜ ሩቅ አይደለም።
❖ ቅዱስ ዮሐንስ በራዕዩ ”ዲያቢሎስ ጥቂት ዘመን እንዳለው አውቆ በታላቅ ቁጣ ወደ እናንተ ወርዷልና” ብሎ ስለነገረን ወደ ሕይወታችን በቅናት ቁጣ እየመጣ የሚያመሰቃቅለንን፣ ግራ የሚያጋባንን፣ የሚያባክነንን፣ የእኛ የሆነውን የሚነጥቀንን ዲያቢሎስ በሰይፈ ሥላሴ ጸሎት ልናርቀው እና ልንርቀው ይገባል። [ራዕ. ፲፪÷፲፪]
የሰይፈ ሥላሴ ጸሎት ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቀን!
Blogger Comment
Facebook Comment