መንበረ ሰላማ | አምስቱ መቅሰፍቶች ስራቸውን ይጀምራሉ፤ በሰዎችና በሰብዓዊ ተቋማት መታመኑን ቶሎ እናቁም

✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ 

መታመናችንን በሰዎችና በሰብዓዊ ተቋማት ላይ ማድረጋችን ምን ያህል አደጋ እንዳለው አላየንምን? አላወቅንምን?

ኢ-አማኒዎቹ ህወሓቶችና ሉሲፈራውያን አጋሮቻቸው በአክሱም ጽዮናውያን ዘንድ መተፋታቸውን እየተረዱ ስለመጡ አሁን 'መንበረ ሰላማ' ብለው ለዘመናት ባዘጋጇቸው ፈሪሳውያን በኩል ብቅ አሉ። አዎ! እነርሱን በይበልጥ የሚያንገበግባቸው የሕዝቡ ስቃይ፣ መራብ፣ መጠማትና መሰደድ ብሎም መጨፍጨፍ ሳይሆን የተቋማት ምስረታ ጉዳይ ነው። አረመኔዎቹ በጅምላ የተቀበሩትን ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ወገኖቼን አካል በግሬደር ቆፍረው በማውጣት በእሳት የማጋየቱ እጅግ በጣም አሰቃቂና መቅሰፍት አምጪ ዲያብሎሳዊ ተግባርማ ለእነዚህ ሕዝቤን እያስገደሉና እየገደሉ'ተጠሪህ ነን' ለሚሉት እርኩስ ፖለቲከኞች፣ ተቋማት፣ መገናኛብዙኅንና ግለሰቦች ምንም አልመሰላቸውም። አንዴም እንኳን በመግለጫ መልክ ወይንም በመገናኛብዙኅን ሰለዚህ ጉዳይ ሲያወሱ አልሰማንም። በሱዳን ስለተሰደዱትም ወገኖቻችንንም ሁኔታ አንዴም ሲያወሩና መረጃ ሲያቀብሉ አይታዩም፣ አይሰሙም። በአክሱም ጽዮን፣ በደብረ ዳሞ፣ በማርያም ደንገላት፣ በውቅሮ ጨርቆስ፣ በደብረ ዓባይ፣ በዛላምበሳ ጨርቆስ ከዚህ በፊት ስለተፈጸሙት ግፎችና ወንጀሎችም ጉዳይ የአንድ ቀን ዜናዎች ጉዳይ ነበር ያደረጓቸው። ዛሬም ገዳማቱና አብያተ ክርስቲያናቱ ምን ዓይነት ሁኔታና ይዞታ ላይ እንደሚገኙ ትንፍሽ አይሉም። ዛሬ እንደምናየው ግን የሕገ-ወጥ የህወሓትን 'መንፈሳዊ' ተቋም ምስረታ በሚመለከት ሁሉም ያለማቋረጥ እየተቀባበሉ በመዘገብና በመለፈፍ ላይ ናቸው። “ህወሓት ተመለሰ!” እያሉን ነው። አዎ! ፓትርያርኩም ደብረ ሲዖል እንደሚሆን አልጠራጠረም። ተቋሙንም ከዓመት በፊት የመሠረቱት እነ ደብረ ሲዖል እና ጌታቸው ረዳ እንደነበሩ በጊዜው ወሬውን ሰምተናል። ያልገደሏቸውን “አባቶችን” ጠርተው ሲያነጋግሯቸው እንደነበር እናስታውሳለን። 

ሰባቱ የመጨረሻ መቅሰፍቶች በግብፃውያን ላይ ወርደው የነበሩትን መቅሰፍቶች የሚያሳዩ መስታወት ናቸው (ኦሪት ዘፀዓት ፯፥፲፩)፡፡ መቅሰፍቶቹ እስራኤላውያንን ሳይነኩ በግብፃውያን ላይ ግዙፍ ጉዳት እንዳደረሱ ሁሉ፤ ከእነዚህ የመጨረሻ መቅሰፍቶች መሃል የመጀመሪያዎቹ አራቱ ፥ እግዚአብሔርን የሚያመልኩ ወገኖችን ዘልለው ለአውሬው የሚሰግዱት ላይ ጉዳት ማድረስ ተቀዳሚ ተግባራቸው ይሆናል፡፡ በግብፅ ላይ የወረዱት መቅሰፍቶች የፈርዖንን ልበ ደንዳናነትና ግብፃውያን ያመልኳቸው የነበሩ አማልክትን ከንቱነት ገልጠው ያሳዩ ነበሩ፡፡

በተመሳሳይ የመጨረሻዎቹም መቅሰፍቶች ለአውሬው የሚሰግዱ ሕዝቦችን ልብ ይበልጥ እንዲደነድን ከማድረጉ በተጨማሪ ባቢሎን ከመለኮታዊው ፍርድ ልትከላከልላቸው የሚያስችል አቅም እንደሌላት የሚገልጥ ይሆናል፡፡ ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ (የዮሐንስ ራዕይ ፲፮፥፩፡፲፩፟)፡፡ እየሆነ ያለው ነገር ምንድን ነው? ክስተቱ የቀረበበት ትዕይንት ምን ይመስላል?

የመጀመሪያዎቹ አራት አምላካዊ ቁጣዎች ወይም መቅሰፍቶች መላውን የምድር ሕዝብ ይመታሉ፡፡ የመጀመሪያው መቅሰፍት የአውሬውን ምልክት በተቀበሉና ለምስሉም በሰገዱ ሰዎች ላይ ክፉኛ የሚያሠቃይ ቁስል እንዲወጣባቸው መንስኤ ይሆናል፡፡ ሁለተኛው እና ሦስተኛው መቅሰፍቶች ደግሞ ባሕሩን፣ ወንዞችንና ምንጮችን ወደ ደም በመቀየር ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳሉ፡፡ የሚጠጣ ውሃ በሌለበት ሁኔታ ዐመጸኛው ሰብዓዊ ዘር መኖር አይችልም፡፡ አራተኛው መቅሰፍት በፀሐይ ላይ ጉዳት ስለሚያደርስ ሰዎች አሁን ከምናየው በከፋ ሊቋቋሙት በማይችሉት ንዳድ ይመታሉ፡፡ በመቅሰፍቶቹ የተነሳ የሚደርሱ ክፉኛ የሚያሠቃዩ ህመሞች፤ ከዐመጻ አስተሳሰባቸው ይመለሱ ዘንድ የሰዎችን ልብ አያለሳልሱም፡፡ ይልቁንም መቅሰፍቶቹን ያወረደውን እግዚአብሔር ይሳደባሉ፣ ይራገማሉም፡፡ አንዳቸውም ቢሆኑ ወደ ንስሐ አልመጡም፡፡

አምስተኛው መቅሰፍት፤ የዮሐንስ ራዕይ ፲፮፥፲፡፲፩) + ኦሪት ዘጸአት ፲፥፳፩፡፳፫) የአውሬውን ዙፋን መምታቱን መመልከት እንችላለን፡፡ እዚህ ላይ ሰይጣን የራሱን ዙፋን ለአውሬው ሰጥቶት እንደ ነበር ልብ ይሏል (የዮሐንስ ራዕይ ፲፫፥፪)፡፡ አሁን ሰይጣን በኃይል የሚቀመጥበት ዙፋን ሳይቀር እነዚያን የሚወርዱ መቅሰፍቶች መቋቋም አልተቻለውም፡፡ ሰዎች ብርቱ ህመም የሚያስከትል ሥቃይ ሲደርስባቸው ባቢሎንን እንደ ጥላ ከለላ ተመልክተው ነበር፡፡ ሆኖም በእግዚአብሔር ላይ ክፉኛ በመታበያቸው እነዚያ የሚወርዱ አሰቃቂ መቅሰፍቶችም እንኳ ልቦቻቸውን መለወጥ አልቻሉም፡፡ አሳዛኝ ክስተት ደርሶ በሥቃይ ውስጥ የምንወድቅበት አጋጣሚ ሊፈጠር ቢችል እንኳ--ስለ እግዚአብሔር ፍቅር እርግጠኞች ሆነንና በእርሱ ታምነን ከጌታ ጋር ያለን ቅርበት እንደ ተጠበቀ መራመድ የምንችለው እንዴት ነው?

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment