የዘረኝነት ጋኔን | የብሪታኒያው ልዑል ዊሊያም 'የአፍሪካ ህዝብ ቁጥር ማደግ ለዱር አራዊት አደገኛ ነው' ብሏል።

✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ 

ልዑል ዊሊያም በኖቬምበር 2021 በለንደን በተካሄደው የቱስክ ጥበቃ ሽልማት ላይ ንግግር ሲያደርግ፤ “በሰው ልጅ ቁጥር የተነሳ በአፍሪካ የዱር አራዊት እና የዱር ቦታዎች ላይ እየጨመረ ያለው ጫና በዓለም ዙሪያ እንደሚደረገው ሁሉ ለጥበቃ ባለሙያዎች ትልቅ ፈተና ነው። ብሎ ነበር።

የራሳቸውን የዱር አራዊት ከምድረ ገጽ ያጠፏቸው አውሮፓውያን እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ ለብዙ ሺህ ዓመታት ከተፈጥሮ ጋር በስምምነት ለሚኖሩት አፍሪካውያን 'ምክር' የመስጠት ሞራላዊ ልዕልና ሊኖራቸው ይችላልን? በጭራሽ!


 ሥራ ፈቱ ልዑል(የ ፫/3 ልጆች አባት) አምላክን ለመመስል የሚመኝ ሊቅ መሆን አለበት፡-


  • የኤስያ ህዝብ ብዛት፡ 100 በካሬ ኪሎ ሜትር

  •  የአውሮፓ የህዝብ ብዛት፡ 72.9 በካሬ ኪሎ ሜትር

  •  የአፍሪካ የህዝብ ብዛት፡ 36.4 በካሬ ኪሎ ሜትር

ብሪታኒያ በዓለም ላይ በጣም ብዙ ሕዝብ ካላቸው ሀገሮች አንዷ ነች።

ስለ አፍሪካም ሆነ ስለ አፍሪካውያን እና ሕይወታቸው ምንም የማለት የሞራል ልዕልና የሌላቸው ልዑል ዊሊያም ሦስት ልጆች አሏቸው፤ ደግሞ ሚስትየዋ ኬት ሚድልተን ልዑል ዊሊያምን 'እንደ አራተኛ ልጅ' ነው የምትመለከተው። ስለዚህ በእነዚህ 'ራስ ወዳዶች' ራስ አፍሪካውያን እዚህ ብዙ ልጆች እየወለዱ እንደሆነ ግልጽ ነው።

ኤሎን ማስክ(የ፲/10 ልጆች አባት)፤ "በአሁኑ ጊዜ ወደ የህዝብ ቁጥር መቀነስ እያመራን ነው። ይህ ደግሞ በዓለም ላይ በሁሉም ቦታ የሚታይ ነው። አንዳንድ ሰዎች ጥቂት ልጅ መውለድ ለአካባቢው የተሻለ እንደሆነ ያስባሉ፤ ግን ይህ ሙሉ በሙሉ ከንቱነት ነው."

ልዑል ፊሊጶስ (የዊልያም ቅድም ዓያት/የንግሥት ኤልሳቤጥ ባል፤ (፬/4 ልጆች፣ ፰/8 የልጅ ልጆች))፤ "ዳግመኛ ከተወለድኩ፣ እንደ ገዳይ ቫይረስ ሆኜ መመለስ እፈልጋለሁ፣ የሕዝብ ብዛት ቁጥርን ለመቀነስ አስተዋጽኦ ለማበርከት እፈልጋለሁ።"

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment