✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ኑሮ እየከፋ በመምጣቱ ግማሽ ያህሉ የካሊፎርኒያ ነዋሪዎች ግዛቱን ለቀው ለመውጣት እያሰቡ ነው። ኃብታሞችና ታዋቂዎች መውጣት ከጀመሩ አሥር ዓመታትን አስቆጥረዋል፤ አሁን ድኾችም ግዛቱን ለቅቀው ለመውጣት በመዘጋጀት ላይ ናቸው።
ግን ምክኒያታቸው የተጠቀሱት ምክኒያቶች ብቻ አይደሉም። ካሊፎርኒያውያን የሚሰደዱት በታክስ፣ በወንጀል፣ በጡረታ ወዘተ ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም በሰዶም እና ገሞራ እጣ ፈንታ ምክኒያት እንጅ። በውስጣቸው ልክ እንደ ሎጥ ዘመን ካሊፎርኒያን ለቅቀው እንዲወጡ የሚነግራቸው ነገር አለ። ይህ ደግሞ በጎ ነው፤ ቶሎ ወጥተው ቤተሰቦቻቸውን ያድኑ!
እየጨመረ የሚሄደው የውቂያኖስ ውሃ የካሊፎርኒያ ህልምን ያጠጣልን? ሰው ከሚያስበው በላይ ውቅያኖስ ካሊፎርኒያን ሊውጣት እንደሚችል እየተጠቆመ ነው።
ከሁለት ወራት በፊት በፓስፊክ ውቅያኖስ ወለል ላይ የፈሰሰው የውሃ ፍሰት መጠን 9.0 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ “ትልቁን” ሊያቀጣጥል እንደሚችል ሳይንቲስቶች አሳስቧቸዋል እናም ዩናይትድ ስቴትስ እስካሁን ካየቻቸው ጠንካራ የመሬት መንቀጥቀጦች አንዱ የሆነው እና በ ውስጥ የፍርሃት ምንጭ ሆኖ ቆይቷል። የፓስፊክ ሰሜን ምዕራብ ለዓመታት.
እኛም፤ “ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንም ባካችሁ ከሰዶምና ገሞራ ካሊፎርኒያ በቶሎ ውጡ!” ማለት ከጀመርን ቆይተናል። ጆሮ ያለው ይስማ! 'በካሊፎርኒያ ገዳም እንሠራለን' ብለው ለሚያልሙት ግብዞች በጣም አዝናለሁ፤ የመጀመሪያዎቹ መጨረሻ እንደሁኑ እሰጋለሁ። በሰዶም ዜጎች ላይ ተቃውሞቻቸውን በማሰማት ላይ ያሉትን የአረሜኒያ ኦርቶዶክስ ወገኖቻችን የሚያሰሙትን ድምጽ መስማት እንኳን መቻል ነበረባቸው። ግን፤ ደንቁረዋል! ታውረዋል!
❖❖❖[ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ፲፱፥፳፪]❖❖❖
በቶሎ ወደዚያ ሸሽትህ አምልጥ፤ ወደዚያ እስክትደርስ ድረስ ምንም አደርግ ዘንድ አልችልምና። ስለዚህም የዚያች ከተማ ስም ዞዓር ተባለ (ዞዓር ትንሽ ቦታ ማለት ነው)።
Blogger Comment
Facebook Comment