ባቢሎን አሜሪካ እየወደቀች ነው | ለአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን አምስት ሚሊዮን ዶላር ጉቦ ሰጥቷል የተባለውን የዩክሬኑን ባለ ኃብት

✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ 

ጉድ ነው! ቅሌታሞቹ ሙሰኞች ጆ ባይድን እና ልጃቸው ሃንተር ባይደን ባጠቃላይ እስከ ስምንት ሚሊየን ዶላር ጉቦ መቀበላቸውንና ከለጋሹም ከዩክሬኑ ባለ ኃብት ከ'ሚኮላ ዝሎቸቭስኪ' ጋር የአስራ ሰባት ጊዜ የሚሆን የስልክ ግኑኘንት እንደነበራቸው የሚያጋልጡ መረጃዎች እየወጡ ነው። ታዲያ በእነዚህ መረጃዎች የተደናገጡት ዲሞክራቶችና ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ነገሮችን ሁሉ አፍነዋቸዋል፤ ትኩረቱንም ከዚህ ቅሌት ለማዞር በቀድሞው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ ክስ መሥርተው በፍሎሪዳ ግዛት አሠሯቸው። አብዛኛዎቹ የእነርሱ የሆኑት ሜዲያዎች አሁን በብዛት በትራምፕ ጉዳይ እንጅ ለጆ ባይድን ቅሌት ትኩረት አልሰጡትም። በጣም የሚከብደውና ለእስራት የሚያበቃው ቅሌት የፕሬዚደንት ጆ ባይድን ቅሌት ነው።

ግን እየታዘብን ነው? በዓለም ኃያልና ኃብታም የምትባለዋ አሜሪካ ፕሬዝድነት ከዩክሬን ጉቦ መቀበላቸው ባቢሎን አሜሪካ እየወደቀች መሆኗን ይጠቁመናል። ሌላው የሚያስገርመው ደግሞ ትኩረትን ለማስቀየር ወደ ትራምፕ መዞራቸው ነው። ልክ የሲ.አይ.ኤን ትዕዛዝ ተቀብሎ በእነርሱ ስክሪፕት ኢትዮጵያን በማመስ ላይ ያለው ሌባው ግራኝ አብዮት አሕመድ ዓሊም ተመሳሳይ ብሎም የከፋ ድራማ ነው እየሠራ ያለው።

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment