✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ሩሲያዊ ሰዓሊ አንድሬ ሩብሌቭ የተሳለውና የ፮፻/ 600 ዓመት ዕድሜ ያለው ይህ ድንቅ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የቅድስት ሥላሴ ሥዕል በሩሲያ በጣም ከሚከበሩትና ከሚወደዱት ቅዱሳት ሥዕሎች መካከል አንዱ ነው።
እ.አ.አ በ1929 ዓ.ም ፀረ-ኦሮቶዶክስ የነበሩት ከሃዲዎቹ ኢ-አማኒያውኑ እነ ቭላዲሚር ሌኒንና ጆሴፍ ስታሊን ሃይማኖትን ለማጥፋት፣ የሃይማኖትና መንፈሳዊ ሕይወት መገለጫዎችን እንደ ባህልና ሥነ ጥበብ ለመቁጠር ሲሉ ይህን የቅድስት ሥላሴ ሥዕል ከቤተ ክርስቲያን ወደ ቤተ መዘክር እንዲዘዋወር አድርገውት ነበር።
የእኛዎቹ ትውልድ ፀረ-ኦርቶዶክስ ከሃዲዎችና አጥፊዎች ልክ ያኔ እነ ሌኒን እና ስታሊን ሲሰሩት የነበሩትን እኩይ ስራ ነው ዛሬ በመስራት ላይ የሚገኙት። ሻዕብያዎች፣ ህወሓቶች፣ ኦነግ-ብልጽግናዎች፣ ብአዴኖችና አጋሮቻቸው ዛሬ፤
- ዓብያተ ክርስቲያናትን፣ ገዳማትንና ቤተ መዘክሮችን ይዘርፋሉ፣ ያፈርሳሉ፣ ያቃጥላሉ
- የዘረፏቸውን ቅርሶች ለባዕዳውያኑ አሳልፈው ይሰጣሉ፣ በኢቤይና አማዞን ይሸጣሉ
- ክርስቲያናዊ በዓላቱንና ሥርዓቶቻቸውን የባሕላዊ መገለጫዎች ብቻ ሆነው እንዲቀሩ ይፈልጋሉ
- ምዕመናንን መግደል፣ መድፈር፣ ማኮላሸትና ማሳደድ እንዲሁም ወጣቱና ሕፃናቱ የባዕዳውያኑ አሕዛብ፣ ኢ-አማኒያን፣ ፕሮቴስታንት እና ግብረ-ሰዶማውያን ባሕል፣ አለባበስ፣ አስተምህሮ፣ ልሳን እና ባሕርይ ሰለባዎች እንዲሆኑ ይሻሉ/ ይሠራሉ
- ሕዝበ ክርስቲያኑን ለመቆጣጠርና ለማሰር ከከሃዲዎቹ ኢ-አማኒያን የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ትስስር ያላቸውን 'ቤተ ክህነቶች' ይመሠርታሉ ያስተዋውቃሉ። ዛሬ የኤርትራ ቤተክህነት፣ የአዲስ አበባ ቤተ ክህነት፣ የትግራይ ቤተ ክህነት፣ የአማራ ቤተክህነት፣ የኦሮሞ ቤተክህነት' ተብየዎቹ ከሃዲዎች የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በጭራሽ የማይወክሉ የወንጀለኞች ስብስቦች ናቸው።
እነዚህ ቤተ ክህነቶች ሻዕብያን፣ ህወሓትን፣ ብአዴንን፣ ኦነግ/ብልጽግናን የሚወክሉ የሉሲፈራውያኑ ጭፍሮች ናቸው። ዛሬ ከምንጊዜውም በላይ አባት በሚያስፈልግበት ዘመን አባቶች የጠፉበት አንዱ ምክኒያት እነዚህ እየተሰቃየ ያለውን ሕዝብ ካባቸውን አውልቀው ሌት ተቀን ሊደጉትና ሊረዱት ሲገባቸው፣ ገና እንባችን ሳይደርቅ ስለድርጅታዊ መዋቀር በይበልጥ ተቆርቁረው መግለጫ ለመስጠት ካሜራ ፊት ለመቅረብ መወሰናቸው ነው። ይህ እጅግ የሚያሳዝንና የሚያስቆጣ ሁኔታ ነው። ለመላው ዓለም ጠቃሚና አስፈላጊ ሊሆኑ የሚችሉ የሃይማኖት አባቶች ከሃገራችን ኢትዮጵያ መፍለቅ ነበረባቸው። ግን አለመታደል ሆኖ ግን ይህ ትውልድ እንደ ሩሲያ ካሉ ሃገሮች ልምድና ታሪካዊ ስህተት መማር ሲገባው እንደው ከሆነ እንኳን እራሱ ከሚሠራው ስህተት ብቻ ለመማር የሚፈልግ ሰነፍ ትውልድ ነው።
እነ ፕሬዚደንት ፑቲን ያለፈው ኢ-አማኒ ትውልድ ከሠራው ስህተት ተምረው ቅዱሳት ሥዕሎችን ለምልጃ ወደራሳቸው ያቀርባሉ፣ እነ ኢሳያስ አፈቆርኪ፣ ግራኝ አሕመድ፣ ደብረ ሲዖልና ጌታቸው ረዳ ግን በትዕቢትና እብሪት ተወጥረው፤ መንፈሳዊ ሕይወት አልባ፣ ከቤተ ክርስቲያን የራቁ፣ ቅዱሳኑን፣ ቅዱሳቱን እንዲሁም ሕዝቡን ሁሉ የሚንቁ፣ ያን ሁሉ ክርስቲያን ጨፍጭፈውና አስጨፍጭፈው ለጸጸት፣ ለይቅርታና ለንሰሐ ለአንዲት ሰከንድ እንኳን ለመዘጋጀት የምይሹና የማይተጉ ናቸው።
Blogger Comment
Facebook Comment