✍ ዶ/ር መስከረም ለቺሳ ደበላ
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ፡ "ደብተራ" የሚለው ቃል በክፉ እንዳይነሳ፣ "ደብተራ" በሚለው ቃል ዙርያ የትም መድረስ የማይችል ክርክር እየፈጠሩ፡ ደብተራ ኹሉ ቅዱስ እንደኾነ በማስመሰል፡ ዐውደ ነገሥትንና ኮከብ ቆጠራን "ክርስትና" ለማስነሳት ጥረት የሚያደርጉ ጀማሪ ፖለቲከኞች፡ ጥረታቸው በጣም መሥመር ስቶ፡ ዓይኑን አፍጥጦ መምጣቱን እያየን ነው።
ይኽ እንቅስቃሴያቸው፡ "ኢትዮጵያን በቀጣይነት የሚመራት የደብተራ ቡድን ነው" ብሎ የሚያስብ፡ በብሔር ካባ የተጠቀለለ ስውር የኢሉሚናቲ እንቅስቃሴ ውጤት ነው። እነ ደቂቀ እስጢፋም አሉበት።
እውነተኛውና በቅዱስ ያሬድ ትምህርት ላይ የተመሠረተው "ደብተራነት" ምን እንደኾነ፡ ወይም ምን መምሰል እንደነበረበት፡ የጥምቀት ልጅ ኹሉ ያውቀዋል።
የአጋንንት ጎታቾች ጠበቆች፡ ስለእውነተኛ ድብትርና ምንነት፡ ለእኛ ለተዋሕዶ ልጆች ለማስረዳት አትድከሙ። ይልቅ ለራሳችሁ እወቁ! አደጋ ላይ ያላችሁት እናንተ ናችሁ።
ሥውር የፖለቲካ እንቅስቃሴያችሁ ግን፡ በዘርዓ ያዕቆቧ እመቤት፡ በድንግል ማርያም ልጅ ኃያል ክንድ ደቅቆ እንደሚቀር ስገልጽላችሁ፡ በደስታ ነው!!!
ምክንያቱም፡ በየጠበሉ የሚንከራተተው የደብተራዎች ሰለባ የኾነ በሚልየን የሚቆጠር ሕዝብ፡ የሚፈርድ አምላክ አለውና፡ የነርሱ ጠባቂ መልአክ፡ የትም አያደርሳችሁም።
እናንተ የትርጉም ክርክር እያነሳችሁ ልታላግጡ እንደምትሞክሩት አይደለም። "ድብትርና" ተግባሩ ሌላ ከኾነ እጅግ ቆይቷል። ለዚህም፡ ሰማይና ምድር ምሥክር ናቸው።
በቃላት ስንጠቃ ፈጣሪን አምታትቶ መሸወድ በጭራሽ አይቻልም። ለማያውቅሽ ታጠኚ!
አጋንንት ጎታች ደብተራዎችና የነርሱ ጠበቆች በሙሉ፡ ንስሓ ገብታችሁ፡ ወደ ቅዱስ ያሬድ ትምህርት ተመለሱ።
ያኔ፡ አምላክ ምሯችሁ፡ ትክክለኛ ደብተራዎች ለመኾን ትበቁ ይኾናል።
እስከዚያው፡ ምንም አፍ ስለሌላችሁና ምንም ብትናገሩ ስለማያምርባችሁ፡ ዝም በሉ!
በላያችሁ ላይ የባሰ ፍርድ አታከማቹ!
Blogger Comment
Facebook Comment