✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
እ.ኤ.አ. በ1994 ዓ.ም በሩዋንዳ በተካሄደው የዘር ማጥፋት ወደ ቤተክርስትያን ተጠልለው በነበሩ ሁለት ሺህ የሚጠጉ ቱትሲዎች እንዲገደሉ ትእዛዝ በመስጠት የተከሰሰው ፉልጀንስ ካይሸማ የተባለ የቀድሞ ፖሊስ በደቡብ አፍሪካ በቁጥጥር ስር መዋሉን የተባበሩት መንግስታት የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት እና የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ሀሙስ ዕለት አስታወቀ።
ዩናይትድ ስቴትስ ካይሼማ እንዲታሰር ለሚረዳ መረጃ የ፭/5 ሚሊዮን ዶላር (£4 ሚሊዮን) ሽልማት ሰጥታ ነበር።
በጣም ይገርማል፤ ይህን ወንጀለኛ ለመያዝ ሃያ ሁለት ዓመታት ወሰደባቸው? ያውም በደቡብ አፍሪካ ውስጥ? ደህና ፣ ጨርሶ ከሚቀር ዘግይቶ ይሻላል!
አምስት ሚሊየን ዶላር ሽልማት ለመስጠት ፈቃደኛ የነበረችው አሜሪካ ዛሬ ከአንድ ሚሊየን በላይ ክርስቲያን ኢትዮጵያውያንን የጨፈጨፉትን እነ ኢሳያስ አፈወርቂ/አብደላ-ሃሰንን፣ ግራኝ አብዮት አሕመድ ዓሊን፣ ደብረ ጽዮንና አጋሮቻቸውን ትደግፋቸዋለች፣ ከፈጸሙት ወንጀል ነፃ ልታወጣቸውም ትፈልጋለች። ያው እኮ፤ ከሩዋንዳው በከፋ መልክ ከአንድ ሚሊየን በላይ ንጹሐንን በኢትዮጵያ የጨፈጨፉት አውሬዎች በአዲስ አበባ፣ አስመራ እና መቖለ ተንደላቅቀው ይኖራሉ። እነዚህን ወንጀለኞች የአውሮፓ፣ አሜሪካ እና እስያ ባለሥልጣናት ይጎበኟቸዋል፣ ይሸልሟቸዋል። ይህን የዘር ማጥፋት ሁሉም በጋራ አቅደው ጨፍጨፋውን በሥራ ላይ ስላዋሉት አይደለምን?! የተገለባበጠበት ክፉ ዓለም!
Blogger Comment
Facebook Comment