✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ለዓመታት ሉሲፈራውያኑ ሉላዊ ልሂቃን ምድርን ከ ፰/8 ቢሊዮን ህዝብ ወደ ፭፻/ 500 ሚሊዮን ብቻ ለማራቆት እቅዳቸውን ሲነግሩን ቆይተዋል። ነገር ግን አብዛኛው ሰው ጆሮውን መሸፈን እና ምንም መጥፎ ነገር እንደሌለ ማስመሰል መርጧል። በኢትዮጵያ ብቻ እስከ ሁለት ሚሊየን ወገኖች በሉሲፈራውያኑ ሤራ በሁለት ዓመት ብቻ ተገድለዋል። አሁንም ዝም ማለታቸው ገና እስከ ሃምሳ ሚሊየንና ከዚያም በላይ ኢትዮጵያውያንን ለማስጨፍጨፍ ፍላጎት እንዳላቸው ይጠቁመናል። እራሳቸውን እንደ አምላክ የሚያዩት አረመኔዎቹ የዓለማችን ፈላጭ ቆራጮች አንዲት የአፍሪካ ሃገር ከግማሽ ሚሊየን የማይበልጡ ነዋሪዎች ብቻ ሊኖራት ይገባል ብለው ያምናሉ/ያሤራሉ። በጣም ያሳዝናል ከኢትዮጵያና ኮንጎ ጎን በሱዳን፣ በሶማሊያ፣ በደቡብ አፍሪካ እና በናይጄሪያ ብዙ የሕዝብ ዕልቂት በቀጣዮቹ ወራትና ዓመታት ይካሄዳሉ። እንደ አለመታደል ሆኖ ለበጎቹ፣ ሁሉም ነገር ደህና እንደሆነ ለማስመሰል የሚጥሩባቸው ቀናት በፍጥነት እያበቁ ነው።
Blogger Comment
Facebook Comment