ልብ ብለህ አድምጥ

- ኢትዮጵያዊነትን በልቡ ያነገሠ  
- ተዋሕዶ ኦርቶዶክስ እምነትን በልቡ ላይ የተከለ
- ሰንደቋን የወደደ ያከበረ 

ማንም ይሁን ማንም የትም ይሁን የት ለኢትዮጵያዊነት ፍቅርና ክብር ያለው

ለተዋሕዶ እምነት ማዳንና እውነተኛነት እምነቷም ትክክል ስለመሆኗ ስለ ቀናነቷ እግዚአብሔርም ዋጋ የከፈለላት መሆኗን በትክክል የተረዳ 

ግራ ቀኝ የማይል 

ምልክቷን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቋን በልቡ የተከለ የለበሳት ማንም ይሁን ማንም ይድናል፡፡

ይሄው እንግዲህ ምስክርነት  እየነገርንህ ነው፡፡

ዛሬ በየበረሃው አሁን ይህንን ሥርዓት እንጥላለን ብለው ብዙ ሰዎች ተንቀሳቅሰውበታል፡፡ በውጭም በአገር ውስጥም በምንም አንዳንድ ጊዜ ይደንቀኛል ሳያቸው  ባንዲራዋን ለብሰው በየበረሃው መሳሪያቸውን ይዘው አንግበው ከዚህ መንግሥት ጋራ እፋለማለሁ ብለው የሚወጡ የሚወርዱ፦ አትጠራጠር እንደ እነዚህ ዓይነት ሰዎች እኮ ተስፋ ያደረጉት ማንን እንደሆነ አውቀሃል??      ኢትዮጵያዊነታቸውን ነው፡፡

ተስፋ ያደረጉት እኮ እግዚአብሔርን ነው፡፡

ተስፋ ያደረጉት ተዋሕዶ ኦርቶዶክስ  እምነትን ነው ፡፡

እምነትን ነው የጨበጡት ፡፡

ተስፋ ያደረጉትና የለበሱት ከልባቸውም አልፈው በላያቸው  አንገታቸው ላይ የጠመጠሙት የኢትዮጵያን ባንዲራ ሰንደቋን ነው፡፡ አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን ነው፡፡

ያሸንፋሉ አትጠራጠር፡፡

እግዚአብሔርን ይዞ የማያሸንፍ አለ?

ምልክቱን እግዚአብሔር ያከበረውን ሰንደቅ አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን የቃል ኪዳን ምልክቱን የያዘ አያሸንፍም ብለህ ታስባለህ? ያሸንፋል፡፡

ኢትዮጵያዊነትን ልብሱ እና ሀብቱ ያደረገ የሚወዳት ያሸንፋል፡፡ ምን ትጠራጠራለህ ቢሰዋ እኮ በሰማዕትነት  በክብር በእግዚአብሔር እጅ ነው የሚሄደው በክብር መጣህ ልጄ ተሰዋህ ለእውነት ና የኔ ልጅ ብሎ ነው በክብር የሚቀበለው ፡፡

⚡️ ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
መግለጫ እና የሉቃስ ወንጌል ትምህርት 
ክፍል -11  ክፍል 2(ለ) ከደቂቃ 40--42 ደቂቃ ድረስ ካለው ትምህርት ላይ  የተወሰደ፡፡
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment