መድኃኔ ዓለም | እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ

✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ 

ጥንተ ስቅለት ፥ መጋቢት ፳፯/27፣ ፴፬/34 ዓ.ም.✞

የዛሬ አንድ ሺሕ ዘጠኝ መቶ ሰባ አምስት ዓመት በዕለተ ዓርብ መጋቢት ፳፯/27 ቀን ፴፬/34 ዓመተ ምሕረት (፶፻፭፻፴፬/5534 ዓመተ ዓለም) የክብር ባለቤት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዓለም ድኅነት በሥጋ የተሰቀለበት ዕለት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ እንደተጻፈው፡ “ከስድስት ሰዓት ጀምሮም እስከ ዘጠኝ ሰዓት ዓለም ሁሉ ጨለማ ሆነ”[ማቴዎስ ፳፯፥፵፭] ፈጣሪዋ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ ባየችው ጊዜ ፀሐይ ጨለመች። እርሱም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም የነሣትን ለባዊት ነባቢት የሆነች ነፍሱን ከሥጋው ለያት። ሐዋርያጴጥሮስ በሥጋ ምውት ሲሆን በመለኮት ሕያው ነው እንዳለ፤ ነፍሱ ከመለኮት ሳትለይ ከሥጋ ተለየች፤ በዚያ ጊዜ ሥጋ ከመለኮት ሳይለይ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ ነበር። እንዲሁም ነፍስ ከመለኮት ጋር አንድ ሁና እሥረኞች ነፍሳትን ትፈታቸው ዘንድ ወደ ሲኦል ወረደች፡፡ [፩ ጴጥሮስ ፫፥፲፰፲፱]

እርሱ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ ያለ ልዑለ ባሕርይ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ በጌትነቱ ዙፋን ተቀምጦ ያለ፣ ለእርሱም ምስጋና የክብር ክብር ገንዘቡ የሆነ ራሡን ሰውቶ ያዳነን የመንግሥቱን ደጆች በፈሳሽ ደሙ የከፈተልን ለእርሱ ስግደት አምልኮት ይገባዋል።

ለዘለዓለሙ የመስቀሉም በረከት በላያችን ይደር፤ አሜን።

(የመጋቢት ፳፯ ቀን ስንክሳር )

❖❖❖[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፺፩]❖❖❖

  • ፩ እግዚአብሔርን ማመስገን መልካም ነው፥ ልዑል ሆይ፥ ለስምህም ዝማሬ ማቅረብ፤
  • ፪ በማለዳ ምሕረትን፥ በሌሊትም እውነትህን ማውራት
  • ፫ አሥር አውታር ባለው በበገና፥ ከምስጋና ጋርም በመሰንቆ።
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment