ኢትዮጵያ፤ በትግራይ የሰላም ካቴድራል | የፍራንክፈርተር ሩንድሻው (FR) የጀርመን ዕለታዊ ጋዜጣ (ከጀርመንኛው የተተረጎመ)


በአውሮፓ ብዙም የማይታወቅ ነገር አለ፡ እሱም፤ የጀርመን ጎሣዎች ገና ዛፎችንና ኮረብታዎችን ሲያመልኩ በዚህኛው የአፍሪካ ክፍል ግን ክርስትና ተስፋፍቶ ነበር።""ካህኑ ኪዳይ ትንሽ ካሰቡ በኋላ፤ 'እግዚአብሔር የሚቀጣው ግለሰቦችን ብቻ ሳይሆን ማህበረሰቡንም ጭምር ነው ፤ በተለይ ማህበረሰቡ ኃጢአት በሠራ ጊዜ። በትግራይም ያለው ሁኔታ ያ ነው ሲሉ ካህኑ አክለውም ህዝቡ ዋሽተው ሰረቁ፣ ልጃገረዶች በጣም አጭር ቀሚስ ለብሰው ነበር፣ ወጣቶቹም በጣም በፈንጠዝያና በዳንኪራ ይጨፍራሉ።ነገር ግን የኤርትራ ወታደሮች የፈጸሙትን አረመኔያዊ ድርጊት ሰበብ ማቅረብ አይፈልጉምም፤ ዋና አዛዣቸውን ርዕሰ መስተዳድር ኢሳያስ አፈወርቂን “የዲያብሎስ አባት ብሎ ይጠሯቸዋል።"

"ከሰሃራ በስተደቡብ የሚገኘው አንጋፋው የክርስቲያን ገዳም ደብረ ዳሞ በኤርትራ የጦር ጀቶች ቦንብ ተመታ። አማሮች የፈረዳሹም ቅዱስ ቂርቆስ ቤተ ክርስቲያንን አቃጥለዋል በርካታ ቅርሶች ላይ ጉዳት ደርሷል። የኢትዮጵያ ወታደሮች ከአቡነ ታዴዎስ ገዳም ጥንታዊ የብራና ጽሑፎችን ሰርቀዋል፣ በህዳር 2020 ቅድስት የሆነችውን አክሱምን ከተማ በያዙ ጊዜ ከኤርትራ የመጡት ጓዶቻቸው በርካታ ካህናትን ጨምሮ ከ400 በላይ ህይወታቸውን አጥተዋል። የአምልኮ ቦታዎችም በእርስ በርስ ጦርነቱ ተዘርፈዋል።"በትንሹ እስከ ፬፻/ 400 የሚደርሱ አብያተ ክርስቲያናት እና ገዳማት ተጎድተዋል።

"ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በእርስ በርስ ጦርነት ወቅት የተፈጸሙትን ስፍር ቁጥር የሌላቸውን የሰብአዊ መብት ወንጀሎች በማጣራት ላይ ባሉበት ወቅት፣ ለአምልኮ ቦታዎች ጥፋትና ዘረፋ ትኩረት የሚሰጥ የለም ማለት ይቻላል ሲሉ በአዲስ አበባ የፀጥታ ጥናት ተቋም ባልደረባ ታደሰ ሲሚ መተኪያ “እነዚህም የጦር ወንጀሎች ናቸው”ብለዋል።

"ከሃዲዎቹ ክርስቲያኖች በአስደናቂው ተራራማ በሆነው የጋርዓልታ ዓለም ውስጥ እንኳን ሙሉ በሙሉ ደህና ሊሆኑ አይችሉም፡ በመጀመሪያ “በኦርቶዶክስ” ክርስቲያን ባልንጀሮቻቸው ይሰደዱ ነበር፣ በኋላም አዲስ አምልኮ ከነበረውና የእስልምና ነቢይ መሀመድ ተከታዮች ጋር ተፋጠጡ!ለካህኑ፣ አውራጃው ከቅድስት አክሱም ከተማ ጋር፣ የእስራኤላውያን የቃል ኪዳኑ ታቦት በዚያ ይቀመጥ ነበር ተብሎ የሚታሰበው፣ ጥንታውያን ዓለት አብያተ ክርስቲያናት የብራና ጽሑፎች የያዙት የኦርቶዶክስ እምነት ማዕከል ነው፡- “እውነት በዚህ ካልተረፈች፤ ሌላ የትም ልትኖር አትችልም። በመጨረሻ መንገዳችንን ስንጨርስ ንስር በእኛ እና በሁሉን ቻይ እግዚአብሔር አምላክ መካከል ይከባል።
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment