ጂቡቲ፣ ጂቡቲ፣ ጂቡቲ...ግዮን፣ ግዮን፣ ግዮን.| የአሜሪካ ጦር በሱዳን


✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ 

የአሜሪካ ጦር በሱዳን ኤምባሲዋ የሚገኙትን አሜሪካውያን ከሃገሪቷ ለማውጣት ዝግጅት እያደረገ ነው!

፲፮/16ሺህ አሜሪካውያን ወጥመድ ውስጥ ገብተዋል ፤ ሶማሊያ 2.0

ጂቡቲ፣ ጂቡቲ፣ ጂቡቲ...ግዮን፣ ግዮን፣ ግዮን...! አሁንስ ገባን ለምን ጂቢቲን ከኢትዮጵያ አስገንጥለው ሁሉም እዚያ የጦር ካምፖችን ለመክፈት እንደፈለጉ? አሁን እንግዲህ የአሜሪካ ጦር ከጂቡቲ ተነስቶ ወደ ሱዳን ያመራል ማለት ነው። በአየር ላይ ለመብረር ደግሞ ትግራይን ማቋረጥ ሊኖርባቸው ነው። ስለዚህ የኦነግ/ብልጽግና፣ ህወሓትና ሻዕቢያ ከሃዲ ወኪሎቻቸውን አስቀድመው “በቃችሁ፣ ለጊዜው ከበቂ በላይ ብዛት ያላቸውን ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖችን ገድላችኋል፤ ጎበዞች! አሁን ግን ወደ ሱዳን ማለፍ ስለሚኖርብን ጦርነቱን ባፋጣኝ አቁሙ!” አሏቸው። አይይይ... ሁሉም የዓረቦችንና የግብጽን ጥቅም ለማስጠበቅ ነው ዛሬም እየሠሩ ያሉት።

ለመሆኑ ባለፈው ዓመት ላይ አዲስ አበባ የሚገኙትን አሜሪካውያን በዚህ መልክ ለማውጣት ለምን ሙከራ አላደረጉም? አዎ! አዲስ አበባን የያዟት የአሜሪካ፣ ብሪታኒያ እና አጋሮቻቸው ኤምባሲዎች ናቸው። አዲስ አበባ ማን መቼና እንዴት መግባት እንዳለበት የሚናገሩት እነርሱው ናቸው። የውጊያውና ተዋናያኑ ቡድኖች መሪዎችም እነርሱ ናቸው። ኤምባሲዎቹ አዲስ አበባ በሰፈሩባቸው ቦታዎች ምድር ስር የራሳቸውን ከተሞች' ቀብረዋል፤ ከእንጦጦ እስከ ሰሜን የተዘረጋውን የተራራ ሰንሰለት በጣም ይፈልጉታል። ባጭሩ፤ ሥራቸውን በሰላም መሥራት ይችሉ ዘንድ ጦርነት ወደ አዲስ አበባ እንዳይገባ፣ ቀደም ሲልም ህወሓቶች በአዲስ አበባ ውጊያ ውስጥ ከመግባት ተቆጥበው ወደ ትግራይ እንዲሄዱ ሲያደርጉ የነበሩትና የሚያደርጉት አሜሪካውያኑና አጋሮቻቸው ናቸው። ሥራቸውን ከጨረሱ በኋላ ግን አዲስ አበባን ልክ እንደ ዛሬዋ ካርቱምና እንደ ትናንትናዋ ሞቃዲሾ የውጊያ ማዕከል እንደሚያደርጓት አያጠራጥርም።

❖❖❖[ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ ፴፩፥፩]❖❖❖

"ስለ እርዳታ ወደ ግብጽ ለሚወርዱ በፈረሶችም ለሚደገፉ፥ ስለ ብዛታቸውም በሰረገሎች፥ እጅግ ብርቱዎችም ስለ ሆኑ በፈረሰኞች ለሚታመኑ፥ ወደ እስራኤልም ቅዱስ ለማይመለከቱ እግዚአብሔርንም ለማይፈልጉ ወዮላቸው!"

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment