የአርሜኒያ የዘር ማጥፋት መታሰቢያ ቀን ፥ የኛስ ?

✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ

እ.ኤ.አ. 2023 የአርሜኒያ የዘር ማጥፋት መታሰቢያ ቀን ፥ ዛሬ በአርሜኒያ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፻፰/108 ዓመታትን አስቆጥሯል✞

አርመን ወገኖቻችን መታሰቢያውን ላለፉት መቶ ስምንት ዓመታት በየዓመቱ በዚህ ዕለት በትጋት በከፍተኛ ሥነ ስርዓት ያስቡታል። የኛስ? በአክሱም ጽዮናውያን ላይ የተፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ሰለባ የሆኑትን ወገኖቻችንን በሁለት ዓመት ውስጥ ብቻ ረስተን ምንም ነገር ሳናደርግ ልናልፍ ነውን? ይህን ከፈቀድን በዚህ ዓለም መኖር አይገባንም። ለዚህ ኃላፊነቱን መውሰድ የነበረባቸው በቤተ ክህነት ውስጥ ተሰግስገው የገቡትና ዛሬ ፈሪሳውያን መሆናቸውን ያወቅናቸው “አባቶች” ናቸው። አንዳንዶቻችን ግን በጭራሽ አንረሳውም፤ ልንረሳውም አንችልም።

የአርሜኒያ ጀነሳይድ የጀመረው በጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ሚያዝያ 24 ዕለት 1915 ዓ.ም ላይ ሲሆን የአክሱም ኢትዮጵያውያን ደግሞ በጥቅምት ፳፬/24 ዕለት (ቅዱስ ጊዮርጊስ /አቡነ ተክለሐይማኖት)፳፻፲፫/2013 ዓ.ም ነው።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ላይ ዛሬ ከአርሜኒያው የዘር ማጥፋት ወንጀል ያላነሰ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈጸመ ነው። ቱርኮች በአርሜኒያ ወገኖቻችን ያኔ የፈጸሙትን ዛሬ ከጋላ-ኦሮሞ አጋሮቻቸው ጋር ሆነው በተመሳሳይ መልክ በትግራይ ፈጽመውታል፤ ነገ ደግሞ በዐምሓራ ክልል እና በአርሜኒያ ላይ ለመፈጸም በዝግጅት ላይ ናቸው። ቱርኮቹ/የአዘርበጃን አዛሪዎቹ እና ጋላ-ኦሮሞዎቹ እነ ግራኝ የሚጠቀሟቸው የጥላቻ ቃላትም በጣም ተመሳሳይ ናቸው።

በኢትዮጵያ እየተካሄደ ላለው የዘር ማጥፋት ወንጀል ተጠያቂዎቹ የውስጥም የውጭም ቡድኖች፣ ፓርቲዎች፣ ፖለቲከኞች፣ ማሕበረሰቦች፣ ግለሰቦች፣ መገናኛብዙኅኖች ወዘተ በተጠቂው ወገናችን ሞት ላይ በመሳለቅ ላይ ናቸው፣ ተጠያቂነታቸውን ይሸፋፍናሉ፣ ፍትሕ እንዳይሰፍን ሤራዎችን በመጠንሰስ ላይ ናቸው። ሰላም ሳይኖር ሰላም ሰላም እያሉ የወገኖቻችንን መታሰቢያ ለማጥፋት እየተንቀሳቀሱ ያሉትን ህወሓቶችን፣ ሻዕቢያዎችን፣ የአማራ፣ ጋላ-ኦሮሞ እና ኦሮማራ ቡድኖችንና ግለሰቦችን ናቸው።

❖❖❖[ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፮፥፲፫፡፲፭]❖❖❖

ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ስስትን ያስባሉና፥ ከነቢዩም ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉ በተንኰል ያደርጋሉና። የሕዝቤንም ስብራት በጥቂቱ ይፈውሳሉ፤ ሰላም ሳይሆን። ሰላም ሰላም ይላሉ።

ርኩስን ነገር ስለ ሠሩ አፍረዋልንምንም አላፈሩም፥ እፍረትንም አላወቁም፤ ስለዚህ ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ፤ በጐበኘኋቸው ጊዜ ይዋረዳሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።”

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment