ጌታችንና የ33 ቁጥር ምስጥር


✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ 

33 ምልክት፡ ዳማር ሃምሊን ለጆ ባይደን እንደገና መጫወት እንደሚችል እንደሚያስብ ነገረው

የክርስቶስ ተቃዋሚው ዲያብሎስ መኮረጅ፣ መስረቅና ማታለል በጣም ይወዳልና፤ ከአምላካችን ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብዙ ነገሮችን ወስዶ በመጠቀም ብዙዎችን በማሳት ላይ ይገኛል። ከዚህም አንዱ ሉሲፈራውያኑ ነፃ ግንበኞች መጠቀም የሚወዱትን 33/፴፫ ቍጥርን ነው።

ጌታችን ሥጋው ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት በከርሠ መቃብር ሲቆይ በአካል ነፍስ ወደ ሲዖል ሄዶ በግዞት የነበሩ ነፍሳትን (አዳምን ከነልጆቹ) ወደ ቀደመ ቦታቸው ከመለሰ በኋላ ቅድስት ነፍሱንና ቅዱስ ሥጋውን በፈቃዱ አዋሕዶ ቅዳሜ ማታ ለእሑድ አጥቢያ ከሌሊቱ በ6/፮ ሠዓት ተነሳ። መለኮት ግን (ሳይከፈል) ከነፍስ ጋር በሲዖል፤ ከሥጋ (በመቃብር) ጋር አልተለየም። ጌታችን በአካለ ነፍስ በሲዖል የቆየው (ዓርብ ከቀኑ 9/ ፱ ሠዓት እስከ ቅዳሜ 6/፮ ሠዓት) ለ32/፴፪ ሠዓታት ያህል ነው። ጌታችን በሥጋው 33/፴፫ ዓመታት በምድር፤ ነፍሱ ከሥጋው እስከተዋሃደችበትና እስከተነሳበት ጊዜ 33/፴፫ ሠዓታት በሲዖል መቆየቱን እንረዳለን።

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment