በመቶዎች የሚቆጠሩ የኡጋንዳ የሐይማኖት ኑፋቄ አባላት የምፅዓት ቀንን በመስጋት ወደ ኢትዮጵያ እየተሰደዱ መሆኑ ተሰማ፡፡
የኑፋቄ መሪዎቹ የዓለም መጨረሻ እንደቀረበና ሞትም አካባቢያቸውን እንደሚመታ አሳምኗቸዋል።
በኡጋንዳ ምስራቃዊ ክፍል ውስጥ የሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከቀያቸው ወደ ኢትዮጵያ መሰደዳቸውን የኡጋንዳ ፖሊስ እሁድ እለት አስታወቋል።
ፖሊስ ባደረገው ምርመራ የኑፋቄው አባላት ከአካባቢያቸው ይጀመራል ብለው ካመኑበት የዓለም ፍጻሜ ለማምለጥ ሸሽተዋል ብሏል።
የኑፋቄው አባላት በቅርቡ አካባቢያቸው በሞት እንደሚመታ እና ሁሉም ሰዎች እንደሚሞቱ በመሪዎቹ እንደተነገራቸው ገልፀዋል። ንብረታቸውን ሸጠው ወደ ኢትዮጵያ መሰደዳቸው ተነግሯል፤ ከዚያም ካሉበት በኡጋንዳ ከሚገኙ አንዳንድ ዘመዶቻቸው ጋር እየተነጋገሩ ነው።
"የክርስቶስ ደቀመዛሙርት ቤተክርስቲያን በሚባል የሃይማኖት ኑፋቄ ላይ በኡጋንዳ ምስራቃዊ ሴሬሬ ወረዳ በኦቡሉም መንደር ውስጥ የሚገኘውን የሃይማኖት ክፍል እየመረመርን ነው፤ ምርመራውን የጀመርነው ከየካቲት ወር ጀምሮ ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ መሆናቸውን መረጃ ካገኘን በኋላ ሲሆን እስከ ዛሬ ድረስም ቀጥሏል ሲሉ የአከባቢው ፖሊስ ቃል አቀባይ ኦስካር ኦጌካ ለአናዶሉ ነግረውታል።
በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደሚናገሩት በአመራሮቻቸው እንደተገለጸላቸው ከሆነ፣ ሞት በቅርቡ ወደ አካባቢያቸው እንደሚመጣና የሚድኑበት ቦታ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ እንደሆነ ተናግረዋል። ወደዚያ ሄደው ወንጌልን ማዳረስ እንዳለባቸው ተነግሯቸዋል።
የሄዱት ከሶስት ወረዳዎች ማለትም ሴሬሬ፣ ኩሚ እና ንጎራ የተውጣጡ ናቸው ተብሏል። የአከባቢው መሪ ብሩኖ ኢሴሬ ለአናዶሉ እንደተናገሩት ወደ ኢትዮጵያ የሄዱት የመንደሩ መሪዎች ሳያውቁ ንብረታቸውን ሸጠው ለትራንስፖርት የሚሆን ገንዘብ በማሰባሰብ ነው።
በኡጋንዳ ውስጥ፣ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች በተሳሳተ መንገድ እንዲሞቱ የሚያደርጉ ብዙ ሃይማኖታዊ ቡድኖች እና የአምልኮ ሥርዓቶች አሉ። ከመጋቢት 17 ቀን 2000 ጀምሮ በጆሴፍ ኪብዌቴሬ የሚመራው የአምልኮ ሥርዓት ከ700 በላይ ሰዎች የሞቱበትን አሳዛኝ የእሳት አደጋ አቀነባብሮ ነበር። ኪብዌተር ዓለም በቅርቡ ወደ ፍጻሜው እየመጣች ነው በማለት ተከታዮቹን ሁሉንም ንብረታቸውን እንዲሸጡ ያሳምናቸዋል፡፡ሀብት ንብረታቸውን በእጁ ካሰገባ በኋላ፣ በአምልኮ ስፍራ ውስጥ ቆልፎ አቃጥሏቸዋል፡፡
©አሻም-ቲቪ | የካቲት-27-2015 ዓ.ም
Blogger Comment
Facebook Comment