አትሳቱ ቅድስት ቤተክርስቲያን ፈጽሞ በሳቱ ሰዎች አትወከልም‼️

✍ ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

👉 ሲኖዶስ ተብየው የምንደኞችና የካድሬ ጳጳሳት ጥርቅም ቅድስት ቤተክርስቲያንን እንደማይወክል በተደጋጋሚ ለበርካታ ዓመታት በመጽሔቶች ላይና በድረገጾች ላይ በጻፍኳቸው ጽሑፎች ነግሬያቹህ ነበር‼️

⚠️ "ቤተክርስቲያን አትሳሳትም ቤተክርስቲያን የምትመራው በመንፈስ ቅዱስ ነው!" ከተባለ እንዴት ነው በተሳሳቱ ሰዎች ወይም ቡድኖች ልትወከል የምትችለው⁉️ ⁉️ ⁉️

♦️ከዐሥር ዓመታት በፊት በማኅበረ ቅዱሳን ጥናትና ምርምር ክፍል በተዘጋጀ ጉባኤ ላይ ይሄ ጉዳይ ግራ አጋብቷቸው ተመልክቸ እዚያ ላይ የተናገርኩትን ልንገራቹህ፦

"ፓትርያርክ ወይም ሲኖዶስ ቢሳሳት ወይም የተሳሳተ ውሳኔ ቢያስተላልፍ ያንን ስሕተት የፈጸመችው ቅድስት ቤተክርስቲያን እንደሆነች መቁጠርና ቤተክርስቲያንን ተጠያቂ ማድረግ ፍጹም ስሕተት ነው። ቤተክርስቲያን በተሳሳቱ ሰዎች ወይም ግለሰቦች አትወከልም በጸኑ አባቶች እንጅ። ሲኖዶሱ ያንን ከቤተክርስቲያን አስተምህሮ፣ ቀኖናና ዶግማ የወጣ የተሳሳተ ውሳኔ ሲያሳልፍ አንድና ሁለት አባቶች ያልተስማሙ ወይም የተቃወሙ ካሉ የቤተክርስቲያንን አቋም የሚወክሉት እነሱ ይሆናሉ። የሚታየው ቁጥራቸው ሳይሆን ትክክለኛ አቋማቸው ነው። እንደዚያ ቢሆንማ ጉባኤ ከለባት የተባለውን ከአንዱ ከቅዱስ ዲዮስቆሮስና እሱን ተከትለው ጉባዔውን ጥለው ከወጡት ከግብጽ፣ ከሶርያና ከአርመን ከመጡት ጥቂቶች በስተቀር ምልዓተ ጉባኤው በሙሉ መለካዊ ወይም የንጉሥ ትዕዛዝ ፈጻሚ ሆኖ የብርክልያንና የተወገዘውን የልዮንን ትዕዛዝ በመፈጸም ኑፋቄ የተደነገገበትን የኬልቄዶኑን ጉባኤ መቀበል ነበረብን ልንል ነው። ስለሆነም ወሳኙ ጥራት እንጅ ብዛት አይደለም። ወሳኙ ብዙዎች የሚከተሉት ወይም የመረጡት ስሕተት ሳይሆን ጥቂቶችም ቢሆኑ እነሱ የያዟት ትክክለኝነት ወይም እውነት ናትና። በሌላ በኩል ደግሞ ሲኖዶሱ ያንን ከቤተክርስቲያን አስተምህሮ፣ ቀኖናና ዶግማ የወጣ የተሳሳተ ውሳኔ ሲያሳልፍ ሙሉ ለሙሉ ተስማምቶ ከሆነ ደግሞ የቤተክርስቲያንን አቋም የሚወክለው ከቤተክርስቲያን አስተምህሮ፣ ቀኖናና ዶግማ ጋር የቆሙት በየበረሃው፣ በየዋሻው፣ በየፍርኩታው፣ በየገዳሙ ያሉ መናንያን ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ይሆናሉ እንጅ የተጠለፈው ወይም መለካዊ የሆነውና ከቤተክርስቲያን አስተምህሮ ተቃርኖ የቆመው ሲኖዶስ ተብየው አይሆንም። የቤተክርስቲያንን ታሪክ ስናጠና ይሄንን እውነቱ ይሄ ሆኖ እናገኝዋለን!" ብየ ነበረ በጉባኤው ሐሳብ የሰጠሁት‼️

📌 ከዚያ በኋላ በዚያ መድረክና በተለያዩ መድረኮች እንዳየሁት በርካቶች ይሄ ሐሳብ ተመችቷቸው ሲያንጸባርቁት አስተውያለሁ። አሁን ለምን ለዚህ እጅግ ድፍረት ለተሞላበት የማጭበርበሪያ ንግግራቸው እግዚአብሔር ይቅር ይበላቸውና "ምንም ይሁን ምን ሲኖዶስ ተናገረ ማለት መንፈስ ቅዱስ ተናገረ ማለት ነውና የሲኖዶስን ውሳኔ መቃወም አይቻልም!" እያሉ የተኩሎቹን፣ የምንደኞችን፣ የካድሬዎችን ስሕተት የመንፈስቅዱስ ሥራ ወይም ስሕተት እያስመሰሉ ማምታታት እንዳስፈለጋቸው ሊገባኝ አልቻለም። እንግዲህ ከሃይማኖትህ ይልቅ ሆድህ ሲበልጥብን እንዲህ ያደርጋልና እየተጠነቀቅን‼️

😭 እናም የዚህ "የኦርቶዶክስን አከርካሪ እንዳያንሰራራ አድርጌ ሰብሬዋለሁ!" እያለ የሚፎክረው አሸባሪ አገዛዝ ፍጹም ታማኝ አገልጋይ በሆኑት በእነ አቦይ ማትያስ ከሚመራው ሲኖዶስ ተብየ የካድሬዎችና የምንደኞች ጥርቅም ጋር መንፈሰ እርኩስ እንጅ ፈጽሞ መንፈስ ቅዱስ የለምና ምእመናን ንቁ። ብንናገረው ስንት የሚዘገንን ጉድ አለ መሰላቹህ እሱ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ሸሽጎ እንደያዘው ሸሽጎ ያስወግድልን ብለን ነው ዝም ያልነው‼️

😭 ለማየት ያብቃቹህ ይሄ ጉደኛ ሲኖዶስ ተብየው የአገዛዙ ካድሬዎችና ምንደኞች ቡድን ለርክበ ካህናት ማለትም ለግንቦቱ የሲኖዶስ ጉባዔ እነኝህን "ይቅርታ ጠይቀዋል!" የሚላቸውን ነገር ግን የቤተክርስቲያኗ ሕግ ፍትሕ መንፈሳዊ ክህነታቸውን ላይመለስ የሻረባቸውን የቀድሞ ካህናት ዱርየዎችን ጨምሮ ጳጳሳት አድርጎ ይሾምላቹሃል ጠብቁ‼️


Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment